Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"I have been misquoted by Ethiopian News Agency" Military Analysit

Post by sarcasm » 03 Jan 2022, 13:18




አሜሪካ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያላት አቋም በአፍሪካ ቀንድ የምትከተለው የውጭ ፖሊሲ የተሳሳተ መሆኑን ያመላከተ ነው


ታህሳስ 25 ቀን 2014 (ኢዜአ)አሜሪካ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያላት አቋም በአፍሪካ ቀንድ የምትከተለው የውጭ ፖሊሲ የተሳሳተ መሆኑን ያመላከተ ነው ሲሉ ፓኪስታናዊው የጂኦ-ፖለቲካል ተንታኝ ሳጂድ ናደም ተናገሩ።

የጂኦ-ፖለቲካል ተንታኙ ሳጂድ ናደም ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያ ለምስራቅ አፍሪካ ሠላምና ደኅንነት መረጋገጥ ወሳኝ አገር ናት ብለዋል።
ይሁንና አሁን በሥልጣን ላይ ያለው የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የያዘው አቋም ይህንን የኢትዮጵያን ሚና የዘነጋ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም ኢትዮጵያ በአካባቢው ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ ከአሜሪካ ጋር በአጋርነት ለበርካታ ዓመታት ያከናወነቻቸውን ሥራዎች ከግምታ አለማስገባቱን ጠቁመዋል።
አሜሪካ በኢትዮጵያ ጉዳይ አድሏዊነትና ወገንተኝነት የተሞላበት አካሄድ እየተከተለች መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ተገቢና ትክክለኛ ያልሆነ አቋም መሆኑን ነው ያስረዱት።
በዚህም አሜሪካ የበርካታ ዓመታት አጋር የሆነችውን ኢትዮጵያን ማጣቷን አብራርተዋል፡፡
አሜሪካ ጥቅሟ እስከተከበረ ድረስ ለዴሞክራሲና ለሰብዓዊ መብት ግድ የላትም ያሉት ተንታኙ አሁንም በአፍሪካ ቀንድ በተለይም በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የምትገባው ለጥቅሟ መሆኑን አስረድተዋል።
በመሆኑም አሜሪካ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንድትገባ እድል መፈጠር የለበትም ብለዋል።
አፍሪካ ኅብረትና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን /ኢጋድ/ የመሰሉ ተቋማት ምዕራባዊያን አፍሪካን በሚመለከት የሚያራምዱትን የተሳሳተ አቋም እንዲቀይሩ ሊሰሩ ይገባል ነው ያሉት።
አሸባሪው የሕወሓት ቡድንም ካሁን በኋላ ኢትዮጵያን የሚመራበት እድል ከሽፏል፤ተመልሶ ወደ ሥልጣን መምጣት አይችልም፤ሕዝቡን ቡድኑን አይቀበለውም ብለዋል።
የአፍሪካ አገራት የሚገጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል አቅም በመፍጠርና ዴሞክራሲያዊ አህጉር በመገንባት የውጭ ጣልቃ ገብነትን እድልን ማጥበብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
Please wait, video is loading...