Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42875
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የአሜሪካ ኩርፊያ ኢትዮጵያን ጠቀማት እንጂ አልጎዳትም

Post by Horus » 28 Dec 2021, 12:08

ለምን?

ኢትዮጵያ ለ100 አመት ካሜሪካ ጋራ ስትሞዳሞድ አንድ ያተረፈችው ነገር የለም፤ ከ100 አመት በኋላ ዛሬም የሷ ስንዴ ለማኝ ነን! ኢትዮጵያ ተርባም ቢሆን በራሷ ሰርታ ያላትን በልታ የማደር ፍጹም ሰባዊ፣ ፍጹም ነጻዊና ቆራጥ ሰው መሆን አለባት ። ያሜሪካ ኩርፊያ የኢትዮጵያ ሳይኮሎጂያዊ ነጻነት መንሳኤ ነው ። ነጻ ለመሆን መራብ አለብን! ስንራብ ሰርተን እንበላለን! ሰርተን እንፈጥራለን? ያን ስናደርግ ነው ክብርም እኩልነትም የምናገኘው! ነጻነት ሃይል ነው!

ኢትዮጵያ የአሜርካ ምግብ ተረጂነት እስካላስወገች ድረስ ነጻ አገር፣ ነጻ ሕዝብ ነን ማለት ታሪካዊ እንጂ የዛሬ እውነታ ሊሆን አይችልም! የኢትዮጵያ ሕዝብ ወጥቶ በሰልፍ ከፈረንጆች እጅ ስንዴና ቦቆሎ መመጽወት እምቢ የሚለው መችሄ ነው? በዚህ አይነት የተራዶ ስንዴ ላይ እየተዋረድን እስከ መቼ እምደ ሙሉ ነጻ ሕዝብ በመምሰል በአለም ፊት የምንቆመው?

ስለዚህ አሜሪካና አውሮፓ እስከነ ምጽዋታቸው በተዉን ኢትዮጵያ እራሷን መቻል ትማር ነበር፣ ትማራለች! ስንት አበሻ ይህን መሰል ሳይኮሎጂ ላይ ደርሷል?

እኛ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ የትግሬ ባንዳዎችና ያሜሪካ የጅ አዙር ቁጥጥር የፈጠሩልንን እድል ማበላሸት የለብንም ። የጎሳ ፖለቲካና ምናምን ወድያ ወርውረን ባገርና ውጭ ያለ ሕዝባችን አንድ አድርገን በራሳችን ጉልበትና ሃብት ታላቋ ኢትዮጵያ ለመገንባት በር ተከፍቶልናል! ባስቸኳይ ሰተት እንግባበት፤ በሚሊታሪም፣ በፖለቲካም፣ በኢኮኖሚም፣ በካልቸርም!!!

ሆረስ ነኝ


Fiyameta
Senior Member+
Posts: 21746
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: የአሜሪካ ኩርፊያ ኢትዮጵያን ጠቀማት እንጂ አልጎዳትም

Post by Fiyameta » 28 Dec 2021, 13:41

In Eritrea there's an old saying that goes like, "coughing strengthens your core muscles." And I remember my president quoting this age-old adage during one of his speeches to remind us that, people don't grow when things are easy, but only when they face challenges; and the bigger the challenge, the bigger the opportunity to reinvent themselves. Every cloud has a silver lining.

Horus
Senior Member+
Posts: 42875
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአሜሪካ ኩርፊያ ኢትዮጵያን ጠቀማት እንጂ አልጎዳትም

Post by Horus » 28 Dec 2021, 15:37

Fiyameta wrote:
28 Dec 2021, 13:41
In Eritrea there's an old saying that goes like, "coughing strengthens your core muscles." And I remember my president quoting this age-old adage during one of his speeches to remind us that, people don't grow when things are easy, but only when they face challenges; and the bigger the challenge, the bigger the opportunity to reinvent themselves. Every cloud has a silver lining.
Fiyameta,
This is true not only of human behavior; it is in fact a fundamental physical law (principle) now known as Constructal Law. The principle simply states that in nature and human society, everything moves against constraints and each constraint (challenge) compels or motivates the moving organism to seek a new path of flow; and by this process natures designs itself.

ሁሉ ነገር ለመንቀሳቀስ (ችግሩን ለመፍታት) ሲሞክር ሌላ ነገር ጋር (ገደብ፣ ድምበር) ጋር ይጋጫል፤ መሰናክል ያጋጥመናል ። ይህን ኮንስትሬይንት ለማለፍ ብለን ነው ይህን ሁሉ ክህሎት፣ ዘዴ፣ ብቃት፣ ፈጠራ በማድረግ ኢቮሉሽንና ሪቮሉሽን የምናደርገው ። ትልቁ ችግር ይህን መርህ፣ ይህን የፍጥረት ህግ ነጋ ጠባ መተግበር አለመቻላችን ነው ።

ስለዚህ የአሜርካ እርዳታ ማቆም፣ መተናኮል ወዘተ ህዝባችን ወደ እድገትና ስልጣኔ በሚያደርገው ጉዞ ላይ የመጣ መሰናክል፣ገደብ፣ ኮንስትሬይንት ነው። ይህን ገደብ ለማለፍ ስንጥር ነው የበለጠ ጠንካራ፣ ጥበበኛ፣ ሃያል የምንሆነው ።

ethiopianunity
Senior Member
Posts: 10979
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: የአሜሪካ ኩርፊያ ኢትዮጵያን ጠቀማት እንጂ አልጎዳትም

Post by ethiopianunity » 28 Dec 2021, 19:37

ኣልስማማም ያልከው ኢትዮዽያ ካሜሪካ ያተረፈችው ነገር የለም። ኢሉሚናቲ ኬኔዲን ከገደሉ በሗላ የውጭ ጉዳይ ህጋቸው ተቀየረ በኪሲንጀር ናዚው። ኣሜሪካ ዘላቂ ጥቅም እንጂ ዘላቂ ወዳጅ የላትም የሚል ህግ ኣወጡ። ኣሜሪካ የኢትዮዽያን ዐየር መንገድ ለማቋቋም ረድታለች። ዕንግሊዝ የጣልያን ጦር ከኢትዮዽያ ከውጣ በሗላ ኢትዮዽያን ለመቆጣጠር ፈልጋ ነበር ነገር ግን በኣጼ ሃስላሴ ዲፕሎማሲ ስኬታማ ምክኛት ለፕረዚደንት ሩዝቨልት ኣቤቱታ ሲያቀርቡ፣ ዕንግሊዝ ጨርቋን ጠቅልላ ጦሯን ጠቅላል ወጣች። ዛሬ ኣክርሯል

ጥሩ ቪዲዮ

Dibu
Member
Posts: 7
Joined: 26 Dec 2021, 01:58

Re: የአሜሪካ ኩርፊያ ኢትዮጵያን ጠቀማት እንጂ አልጎዳትም

Post by Dibu » 28 Dec 2021, 20:06

Stop the rhetoric and focus on the diplomatic work.
Right now the diplomacy performance of the Ethiopian government is not competitive.

Not sure why my comments are not posted. Several constructive and debtable ideas er supressed. It is possible the Woyannies control this website.

Horus
Senior Member+
Posts: 42875
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአሜሪካ ኩርፊያ ኢትዮጵያን ጠቀማት እንጂ አልጎዳትም

Post by Horus » 28 Dec 2021, 21:58

ethiopianunity wrote:
28 Dec 2021, 19:37
ኣልስማማም ያልከው ኢትዮዽያ ካሜሪካ ያተረፈችው ነገር የለም። ኢሉሚናቲ ኬኔዲን ከገደሉ በሗላ የውጭ ጉዳይ ህጋቸው ተቀየረ በኪሲንጀር ናዚው። ኣሜሪካ ዘላቂ ጥቅም እንጂ ዘላቂ ወዳጅ የላትም የሚል ህግ ኣወጡ። ኣሜሪካ የኢትዮዽያን ዐየር መንገድ ለማቋቋም ረድታለች። ዕንግሊዝ የጣልያን ጦር ከኢትዮዽያ ከውጣ በሗላ ኢትዮዽያን ለመቆጣጠር ፈልጋ ነበር ነገር ግን በኣጼ ሃስላሴ ዲፕሎማሲ ስኬታማ ምክኛት ለፕረዚደንት ሩዝቨልት ኣቤቱታ ሲያቀርቡ፣ ዕንግሊዝ ጨርቋን ጠቅልላ ጦሯን ጠቅላል ወጣች። ዛሬ ኣክርሯል

ጥሩ ቪዲዮ
ሎጂኩ አንተ አንዳልከው ሳይሆን ከ2ኛው አለም ጦረነት በኋላ አሜሪካ የበላይ ለመሆን ቅኝ ግዛት ስርዓት (አሮጌው ኮሎኒያል እዝ) በአዲሱ እጃዙር (ኒዎኮሎኒ) ለመተካት ስትታገል የድሮ ያውሮፓ ቅኝ ገዦችን ተፎካከረች እንጂ አሜርካ አንድም ግዜ ኢትዮጵያ ታላቅ አገር እንድትሆን ፈልጋም፣ ገልጻም፣ ረድታም አታቅም ፣ ያም ስለሆነ ነው ይሀው እስከ ዛሬ በበሬ የምናርሰው ። ከ100 አመት በኋላ ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካነት ማደግ ሳይሆን ኢትዮጵያ ሁሉ ወደ አሜሪካ እንዲሰደድ የካልቸር ወረራና የሳይኮሎጂ እጥበት ነው ያደረገችው ። ዛሬ አበሻ ሁሉ አገሩን አሰልጥኖ ሰው ለመሆን ሳይሆን ምኞቱ እርሻውን ሸጦ አሜሪካ በመምጣት ታክሲ ነጂና ካሸር ሆኖ መኖር ነው የሚመኘው። ይህ የካልቸርና የሳይኮሎጂ ኢምፔሪያሊዝም ማለት ነው።

Post Reply