በዚህ በኑሮ ውድነት አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የሚያስከፍለው የብር መጠን የትየለሌ ሆኖ ሳለ: ተማሪዎች ተመዝግበው ብራቸውን ከፍለው መማር ካልፈለጉ ብራቸው ሊመለስላቸው ይገባል::
ዩኒቨርሲቲው ግን ብር አንዴ ከገባ ማንም ብር ልጠይቅ አይገባም ብሏል:: 120 ብር ምናምን ቢሆን እሺ ይባላል:: ብዙ ሺ ብር ከሆነ ዩኒቨርሲቲው በልቶ ዝም ሊል ነው? ሕግ ባለበት ዓለም ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል::
ዘመናዊ ዘዴንካ ለመከተላቸው ብሩ ቶሎ ለከፋዩ እንዲመለስ ማረግ :አይፈልጉም: የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ችግሩ በየግዜው የሚያወጣው ሕግ ነው::
አሁን የሰማሁት: አንድ ሰው ለመማር አመልክቶ ይፈቀድለትና የመማርያ ብሩን/ tuition fee እና መመዝገብያ ብር ይከፍልና ለመመዝገብ ይሄዳል:: ለመመዝገብ ሲሄድ በሰልፍ መጨናነቅ ሙሉ ቀኑን ቢጠብቅ ሳይሳካለት ይቀራል:: ከዛም በቅጣት መመዝገብ ስለምትችል ከሳምንት በህዋላ ና ይባላል:: ግን ልጁ እንዳጋጣሚ ሆኖ በሥራ ምክንያት ክላስ መገኘት አልቻለም:: ዩኒቨርሲቲው ደሞ ክላስ መገኘት ግዴታ እንደሆነ ነው የሚደነግገው:: ምናልባትም እንዲህ ክላስ መቅረቱ የማይቀር ከሆነ መጨረሻው ስለማያምር: ልጁ refund እንዲደረግለት ለመጠየቅ ለወራት ተመላልሷል:::: refund request form መሙላት አለብህ ስለተባለ : refund request form የተባለውን ከየት ያግኝ? ሁሉም ባለማወቃቸው ልጁ እንዲሁ ሲመላለስ ከርሞ መጨረሻ የርቀት ትምህርት ቢሮ እንደሚገኝ ተነገረው::
ችግሩ አሁን መጣ :: በዚህ ግዜ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፋይናንስ አዲስ ሕግ ያወጣል::
ምንም አይነት refund request አንቀበልም: ምንም ብር ካዝናችን የገባ አይመለስም ብሎ አረፈው:: እና ምን ይሁን? ልጁ ምን ያርግ? ወደ 15 ሺ ብር ገደል ይግባ?
ሁሉንም አካል ቢያነጋግር አዲስ ሕግ ወጥቷል አሉ:: እና ልጁ "ሕጉ አሁን አይደል ወይ የወጣው ለምን እኛ ከላይ ይተገበራል?" ቢል ሕግ ሕግ ነው ብለውታል::
ቢያንስ ቢያንስ ሕጉ አሁን እንደመውጣቱ ከሚቀጥለው ሰሚስተር በህዋላ የሚመጣውን እንጂ በዚህ ሰሚስተር እና በፊት የነበረውን ሊያጠቃልል አይገባም ነበር:: ይህ አንባገነንነት ነው::
ዩኒቨርስቲውም የሰውን ብር ወስዶ አልመልስም ማለት ምን ያህ ይስኬዳል?
ውጭ አገርም እንዲህ የሚባል ነገር የለም::
እና የሚመለከተው አካል መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል:: መንግስትም ይሄን ነገር ቢያየው ጥሩ ነው::