Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 37256
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

Somali Kilil President Mustafa Is In Dji-Booty & Said:Africans Should Unite Against Terrorist-Tplf !!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 13 Dec 2021, 11:52

Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/
21m ·
"አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያ የከፈተው ጦርነት ቀጠናውን ለማተራመስ በመሆኑ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት በጋራ ሊመክቱ ይገባል" - ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ
************************
(ኢ ፕ ድ )
ወራሪውና አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያ የከፈተው ጦርነት ቀጠናውን ለማተራመስ የተነሳ ና አላማው ያደረገ በመሆኑ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት በጋራ ሊመክቱ ይገባል ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ተናገሩ።
በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራው የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ልዑክ፤ ሄሪቴጅ ኢንስቲትዩት በተባለው አለም አቀፍ የጥናትና ምርምር ተቋም አማካኝነት በየአመቱ የሚያዘጋጀው መድረክ ላይ ለመሳተፍ ጅቡቲ ገብተዋል።
መድረኩ በዋናነት በምስራቅ አፍሪካ ወቅታዊ የሆኑ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና በቀጠናው ውህደት ላይ ትኩረቱ አድርጓል።
የዘንድሮው መድረክ በጅቡቲ አስተናጋጅነት ከተለያዩ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የተውጣጡ እውቅ ምሁራን ፅሁፎች አቅርበው ውይይት ተደርጓል።
በመድረኩ ላይ በኢትዮጵያ ያለው ነባራዊ ሁኔታና በቀጠናው ያለው አንደምታ የተዳሰሰ ሲሆን፣ በርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ወራሪውና አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያ የከፈተው ወረራ ቀጠናውን ለማተራመስ የተነሳ ስለሆነ የቀንዱ ሀገራት በጋራ ሊመክቱ ይገባል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማንኛውም ሀገር ላይ ጣልቃገብነት እንዳይኖርና አሸባሪው ህወሓት በምስራቅ አፍሪካ ያደርግ የነበረውን ጣልቃ ገብነትና የማተራመስ ስትራቴጂን ተከላክለው መልካም የሆነ ጉርብትና በሀገራት መካከል እንዲኖር አድርገዋል ብለዋል አቶ ሙስጠፌ።
የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የኢትዮጵያውያን ብቻ ነው በማለት የኢትዮጵያን ድምፅ አሰምተዋል።
በመድረኩ የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ባደረጉት ንግግር የከፈቱት ሲሆን፣ የጂቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ አሊ፣ የጂቡቲ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ኢልያስ ሙሳ፣ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ የፕላን ሚኒስትር ጀማል አህመድ፣ የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ፣ የኬንያ ሪፐብሊክ የቀድሞ የጁብሊ ፓርቲ መሪና የፓርላማ አባል አደን ዱኣሌ መገኘታቸውን ከሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አካባቢህን ጠብቅ‼
ወደ ግንባር ዝመት‼
ሠራዊቱን ደግፍ‼
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን ‼
ዩቲዩብ 👇
https://youtube.com/channel/UCoH2CVwWn9suWP7q0u2L7MA
ቴሌግራም 👇
https://t.me/ethpress
ትዊተር 👇
https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ 👇
https://www.press.et/