Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

tolcha
Member
Posts: 3585
Joined: 27 Feb 2013, 16:51

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by tolcha » 11 Dec 2021, 13:37

Horus wrote:
11 Dec 2021, 09:53
Tebedda, ante Gim Gurage; yalewun “fact” siletenagerechi, lemin qixihin asakekkehi! Gurage wusxi endeziya ayinet neger bideregi yihene 999x gize “psycho” honeh neber. Wosatta Lebba!!!

Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by Ejersa » 11 Dec 2021, 13:44

ቆሻሻ ትግሬ እናትህና አንተ ተበዱ! ትንሽ አይቀጥጥህም ስትሳደብ፣ በል አፍህን ካልሰበሰብክ እህትህንም እንደግምልሃለን፣ ለማኝ ትግሬ!!!
tolcha wrote:
11 Dec 2021, 13:37
Horus wrote:
11 Dec 2021, 09:53
Tebedda, ante Gim Gurage; yalewun “fact” siletenagerechi, lemin qixihin asakekkehi! Gurage wusxi endeziya ayinet neger bideregi yihene 999x gize “psycho” honeh neber. Wosatta Lebba!!!
Last edited by Ejersa on 11 Dec 2021, 13:47, edited 1 time in total.

Abdisa
Member+
Posts: 6271
Joined: 25 Apr 2010, 19:14

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by Abdisa » 11 Dec 2021, 13:46

Lock her up, and throw away the key!

Misraq
Senior Member
Posts: 17864
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by Misraq » 11 Dec 2021, 13:55

ይህች የሕወሃት ሽንት ጨርቅ ድሮ ነበር መታሰር የነበረባት።

For the record, she was saying "this is a war between Tigray and Abiy. Amhara shouldn't be concerned"

She is no different to all banda's working for TPLF for a cheap $$.

Horus
Senior Member+
Posts: 42869
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by Horus » 11 Dec 2021, 15:09

ወገኖች፣
ከፈለጋችሁ ይች ሴት አባይ ሚዲያ ላይ ታደርግ የነበረውን መቀባጥር ስሙት ። ሴትዮዋ አቢይን መቃወም የጀመረሽው ገና አቢይና ኢሳይያስ መስማማት ሲጀምሩ ነው። ያን መሰል ቅዋሜዋ ከምን እንደ መነጨ ባላውቅም ትልቅ ቅሬታዋ ኤርትራና ኢትዮጵያ መስማማት ላይ ነው ። ከትግሬ ባንዳ ጋራ ምን ት ስ ስር እንዳላት አላውቅም ፣ ግ ን እልም ያልቸው ት ዕብተኛ አፏ ባለጌ ፈረንጆች ቢች የሚሏቸው አይነት ሴት ነው። በሷ የተነሳ አባይ ሚዲያን ማየት አቁሜ ነበር ! የሆነ ፕሮብሌም ያላት ሴት ነች! አሁን ቃሊቲ ትንሽ ግዜ ወስዳ ጥሞና ታድርግ!

ያ ቶልቻ የሚባል ቆሻሻ የንግዴ ልጅ ቢናደድ በጣም ነው የሚገባኝ!! ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል አሉ እነድሬ!!!

Tadiyalehu
Member
Posts: 675
Joined: 29 Jul 2014, 09:53

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by Tadiyalehu » 11 Dec 2021, 15:17

እቺ አዛባ ቃሊቲ እራሱ አይገባትም።
በደህና ሽመል አከርካሪዋን አዛቡልኝ!

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 13257
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by DefendTheTruth » 11 Dec 2021, 15:21

Another big fan of that media (Abay media) is eden of this forum, could she also go out of her steps for today and explain the relationship between the two, TPLF and Abay Media?

ethiopianunity
Senior Member
Posts: 10979
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by ethiopianunity » 11 Dec 2021, 19:40

የህዋሃት ኣፍ ቀላጤ ከሆነች ቅጣት ታግኝ ግን ገና ከህዋሃት ጭቆና ወተን ደሞ በሻብያ ሌላ ኣገር የሚገዛ ኢትዮዽያን በመቆጣጠር ሊተካ የሚችል ነው። የሻብያ ሙሉ በሙሉ ጣልቃ መግባት የሚደግፉ ኢትዮጵያውያን ልክ የኢሃፓ ሁለተኛ ዙር ኣገር ከደት እንዳረገ ነው የሚቆጠረው። ሻብይ ከውጭ ሃይል ኣጋሮቹ ምን ኣላማ እንዳለው ኣይታወቅም። የኢትዮዽያን ኣስፈላጊ ከሚባሉት ዲፕሎማሲ ኢትዮጵያ ሳትሆን ሻብያ ነው የሚወክለው ለምን?

Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by Assegid S. » 11 Dec 2021, 19:53

መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው
Hello Horus - thanks for the post; but I have a question for you here:

ኢትዮዽያዊ ዜጋ "ፀረ አብይ" ስለሆነ ብቻ መታሰር አለበት ብለህ በእርግጥ ታምናለህ? አብይ ማለት እኔ እስከሚገባኝ የሰው ስም እንጂ የእውነት የወል መጠሪያ አይደለም። ሰው መታሰርም ሆነ መጠላት ያለበት ፀረ እውነት ሲሆን እንጂ ፀረ ግለሰብ ስለሆነ መሆን የለበትም። የኣንድን ግለሰብ (መሪ) አስተሳሰብ መልካም ካልሆነ መቃወም ሀጢያት ሆኖ ያስኮንናል (ያሳስራል)? በእኔ እምነት፣ ኣንድ ሰው መሪን ስለተቃወመና በአመራሩ ስላልተስማማ መታሰር የለበትም ባይ ነኝ። አብይ አምላክ አይደለም። ይህንን ስል ኣንዳንዶች "ሰው ፀረ አምላክም ቢሆን መታሰረ አይኖርበትም" የሚል እምነት ይዘው እንደሚነሱም አምናለሁ።

Like I said, አብይ ሰው እንጂ አምላክ አይደለም፣ አብይ ከብዙዎች ሳይንሳዊ ወይንም መለኮታዊ እምነቶች መካከል ኣንዱን መርጦ የሚከተል እንጂ በራሱ እምነት አይደለም። አብይ የኣንድ ኢትዮዽያዊ ግለሰብ ስም እንጂ የኢትዮዽያዊ ማህበረሰብ የጋራ መጠሪያ አይደለም። ስለዚህ መአዛ መሐመድ "ቀንደኛ ፀረ አብይ" ስለሆነች ትታሰር የሚለው inductive argument ፈፅሞ አግባብ አይደለም።

ዛሬ ላይ የሁላችንም እናት የሆነችው ሀገር በገደል ኣፋፍ ላይ እየተጓዘች በመሆኗ ተጭማሪ የተቃውሞ ሽክም በመሆን ሚዛኗን ላለማዛባት እንጂ፥ እመነኝ ... ነገ ከነገ ወዲያ ሀገራችን ግራ ቀኝ ለመጓተት የሚያስችላት ደልዳላ ሜዳ ላይ ስትደርስ ኣንድ አይደለም በሚልዮን የሚቆጠር ፀረ አብይ ይኖራል። ምክንያቱም ግለሰቡ እንደ መሪ (እረኛ) ህዝብን በሚገባው መጠን አልተከላከሉም። ትላንትና ነገሮች በእንጭጩ ሳሉ ይቀጩ ብለን ስንጮህ ... "ኮሽ ባለ ቁጥር አትደንግጡ" እያሉ ሲያላግጡብን፥ ይኸው ዛሬ ኮሽታው ከነጎድጓድም በላይ ሆኖ በየሶሻል ሚዲያው ምስኪን ኢትዮጵያዊ ወንድምና እህቶቻችን ከቅጠል በበዛ መልኩ ሲረግፍ እያየን ከመደንገጥም በላይ እየሰቀጠጠን ነው። መዓዛ መሐመድ በምትቃወመውና እንድትታሰር በሚጠየቅባት ግለሰብ ቸልተኝነትና ራስ ወዳድነት ... ቀላል የማይባል ህይወት አጥተናል፣ እያጣንም ነው። ለተቃውሞዋ ቃሏ ቃሊቲን መመኘት አግባብ አይደለም።

Horus
Senior Member+
Posts: 42869
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by Horus » 11 Dec 2021, 20:41

አሰግድ አሁን ያልከው ሁሉ ሮማንቲሲዝም ይባላል። እውነት ወንዝ ወርደህ እንደ እንጉዳይ የምትለቅመው ፍሬ አይደለም ። እውነት ማለት እምነት ነው፤ እምነት ማለት ውሳኔ ማለት ነው! ሰዎች ስለፈለጉት ወስነው የሚከተሉት ሃሳብ ነው። እኔ ስለ እውነት ምንነት ኮግኒቲቭ ቲኦሪ ውስጥ ብዙ ማለት አልሻም።

በመሰረቱ የራስክን ጥያቄ እራስህ መልሰሃዋል ። መዓዛ አቢይን የምትቃወመው አቢይ አህመንድ አንድ ግለሰብ ስለሆነ አይደለም፣ በኢትዮጵያ መሪነቱ ነው። እንደ አገር መሪ በአመራሩ ላይ ቅዋሜ ካላት ልክ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሚያደርጉት መሰረት ትቃወማለች የተሻለ መሪ ከሆነችና የተሻለ ሃሳብ ካላት ። እኔ እስከ ሰማዋት ድረስ እንደ ነዝናዥ ባል ወይም ሚስት ስትነጫነጭ እንጂ ይህ ነው የሚባል ለመሪነት የሚበቃ ሃሳብ እንኳ በራስ ቅሏ ውስጥ የለም ! አለ የምትል ከሆነ መጥቀስ ትችላለህ!

እውነቱ ዛሬ ምን እንደ ሆነ ልጠቁምህ! ኢትዮጵያ የምትባል እጅግ ድንቅ የሆነች ታሪክዊ የአለም ቅርስ የሆነች አገር ውስጥ የሚኖሩና ህይታቸው ከሷ ህልውና ጋር የተሳሰረ 120 ሚሊዮን ሰዎች አሉ። ይህ ህዝብ አንድ አገር የሚባል ድርጅት አቋቁም ያን የሚመራ ስራ አሲኪያጅ አቢይ የሚባል መሪ አስቀምጦ ሌት ተቀን ከብዙ አይነት ችግር ጋር እየታገለ አንድ ግዙፍ ለሆነ አላማ ለኢትዮጵያ አላማ እየለፋ ነው ። ይህ ነው ዛሬ አሁን በዚህ በእኛ ዘመን ፊታችን ላይ ያለው እውነት፣ እምነት፣ ውሳኔ፣ አላማና ግብ!!! እውነት የሰው ልጆች ህይወታቸውን ሊመሩበት የፈጠሩት እምነትና መመሪያ ነው እንጂ የማንም አላዋቂ ከሰማየ ሰማያት በማጂክ ተገልጾለት እየወጣ የሚለፈልፈው ምናብ ልብ ወለደ አይደለም!

ያንተ ጋዜጠኛ ተብዬ መአዛ ምን ታውቃለች? ከአቢይ በላይ ምን እውቀት አላት? ስለ አገር አመራር ሆነ አገር ጥበቃ ሆነ አገር ግምባታ ምን ታቃለች? ምድረ አጉል ጋዜጠኛ በየቀኑ ያለእውቀት በመለፍለፍ ህይወታቸው ስለሚባክን ማንበቢያ፣ ማሰቢያ፣ መማሪያ ግዜ እንኳን የላቸውም። በባዶ አንጎላቸው እየተነሱ በየቀኑ ስለሁሉም ነገር ኤክስፐርት ምስለው በመለፍለፍ ህዝብ የሚያዶነቁሩ ምላሳሞች ናቸው ።

ስለዚህ የኢትዮጵያን ጉዳይ በተመለከተ ለእኛ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ያለው እውነት የእኛ ውሳኔ፣ የእኛ እምነት የማንም ግለሰብ ቅዠት ማመንዠክ ሳይሆን ኢትዮጵያ እንደ አንድ ህዝብ እንደ አንድ አገር ያነሳችውም አላማ መተግበር ነው ። ያን ለማድረግ ደሞ አንድ ሕዝብ መሪ አለው ። ዐቢይ ዛሬ የኢትዮጵያ ምልክት እንጂ የአቶ አህመድ አሊ ልጅ የሚባል ግለሰብ አይደለም። እንደ መዓዛ ያሉ አላዋቂ ወይ ድብቅ ተላላኪዎች የማይገባቻው ይህ ነው ። መዐዛ ምትመራው አንድም አላማ የላትም ስራዋ የራሱዋን አለትምህርት የተከማቸው የሃስብ ቅራቅምቦ በየቀኑ በሚዲያ በመለፍለፍ ልጇን ምታሳድግ እናት ናት ። ትልቅ ችግሯም ያላት ትዕቢትና ምላሰ ስድነት ነው።

ይብቃኝ!

eden
Senior Member
Posts: 10141
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by eden » 11 Dec 2021, 22:18

ጋዜጠኛን ከማሰር፣ ለምን ሃሳቡን በሃሳብ ለመምታት አይቻልም? ህዝቡን ሁሉንም ሃሳብ ሰምቶ የሚበጀውን ይከተላል። ካሰርክ ግን፣ ሃሳብ ህዝብ ዘንድ እንዳይደርስ ሆነ ማለት ነው።

የብልፅግና ሃሳብ ስህተት ቢሆን፣ ማን ያርመዋል? ካሰርክ እንዳትተች፣ እንዳትታረም፣ እንዳትሻሻልክ ሆነ ማለት ነው። ይህ ለብልፅግናም አይበጅም።

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by TGAA » 11 Dec 2021, 22:43

መአዛ መሀመድ ትርፍ የምትናገረው ነገር ሊኖር ይችላል ፤በተለይ የአብይን ሰብአዊ መብት ላይ ያለውን አቋም እጅግ አክርራ ተከራክራለች ፤ በዚህ አቋሟ ግን የአብይን አጠቃላይ ከወያኔ የባሰ ጸረ አማራ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ መድረስዋ ግን ትንሽ ጥግ የያዘ አመለካከት ነው፤ ነገር ግን እንደ እውነተኛ ጋዜጠኛ የሰብአዊ ጥሰት፤ ጅምላ ጭፍጨፍ የደረሰባቸውን አካባቢዎች ባላሰለሰ ግዜ ሄዳ ተመልክታለች ፤ የሰብአዊ ጥሰት የደረሰባቸውን ሰዎች ቃለ መጠየቅ አድርጋልቸ፤ እዚህ ከምንተቻት ሰዎች በበለጠ ፤ በቂ ኢንፍሮሜሽን በየቀኑ የሚደርሳት ሰው ነች ፤ የህብረተሰቡም ቁስል እዚህ ካለን ሰዎች በበለጠ የሚሰማት ሰው ነች ፤ ስለዚህ እርሷን ለማጥቃት የግዴታ ጅጊ መግባት የለብንም ፤ ድምዳሜዎን ፤ ላንስማማበት እንችላለን ፤ አንዳንዴ የተወሳሰቡ እውነታዎችን በደንብ አፍታታ ማየት አልቻለች ይሆናል ፤ ነገር ግን የተነሳቸበት እውነታ እንኳን ሴት የልጆች እናት ፤ እንኳን ሴት የሴቶች መታገት ምን እንደሆነ ግንዛቤ ያላት ይቅርና ፤ ማናችንም ለሰው መብት እንታገላለን የምንል ሰዎች በመናደድ የማይገባ ድምዳሜ ውስጥ እንገባለን፤ ስለዚህ አስረናት የእስር ቤቱን ቁልፍ እንወርውር የሚል አስተሳሰብ ስሜታዊና ሚዛናዊንት ይጎድለዋል ፡፡

Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by Wedi » 11 Dec 2021, 22:51

ታምራት ነገራ እና ማዕዛ መሐመድ የመሳሰሉ ምርጥ ኢትዮጵያውያንን ማሰር የአብይ አህመድ የመሸነፍ ምልክት ነው!! እጅግ ያሳፍራል!!
በህጻኑ ንጉስ አብይ አህመድ አስተሳሰብ በቃ እሱን ያላሞገሰና እና እንደ ፈጣሪ ያላመለኩ ሁሉ የኢትዮጵያ ጠላት!! ማፈርያ ነገር ነው!!

Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by Assegid S. » 12 Dec 2021, 00:05

Horus; ለመልስህ ማመስገን እፈልጋለሁ።

ጋዜጠኛዋ ጠቅላይ ሚንስትሩን የምትቃወመው ግለሰብ ስለሆነ አይደለም፥ እኔም እንደዛ አላልኩም። መሪ ስለሆነና አመራሩም እሱዋን ጨምሮ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ግለሰቦች የዕለት ተዕለት ህይወት ላይ በክፉም ይሁን በበጎ ጐኑ ተፅዕኖ ስለሚኖረው ነው። እንደ ኣንድ ዜጋ በእራሷም ይሁን (አንት እንዳልከው ልጅ ካላት) በልጇ የወደፊት ህይወት ላይ ወሳኝ ሚና ያለውን ሰው ለመቃወም ደግሞ ግዴታ የፖለቲካ ፓርቲ መመስረት ወይንም የፖለቲካ ፓርቲ ኣባል መሆን አይጠበቅባትም። በነገራችን ላይ ለምን "ያንተ ጋዜጠኛ ተብዬ" ስትል የእኔ ጋዜጠኛ እንዳደረካት ባላውቅም አገላለፁ ግን ፈገግ አድርጓኛል።

ለመሪነት የሚያበቃ ዕውቀት በትምህርትና በልምድ እንጂ በትውልድ ወይንም ደግሞ በተፈጥሮ የሚገኝ ችሮታ ነው ብዬ አላምንም። እኔ ብቻ ሳልሆን ጠቅላይ ሚንስትሩም እንደዛ እንደማይምኑ ... ለዚህ ቦታም የበቁት በዕድል እንደሆነ ከራሳቸው አንደበት እንደሰማሁ እርግጠኛ ነኝ። ስለሆነም ጋዜጠኛዋ የትምህርቱንም ሆነ የልምዱን ዕድል ብታገኝ ለመሪነት ታንሳለች የሚል እምነት የለኝም። ያ ባይሆን ኑሮማ መሰረታዊው የዜጎች የመምረጥና የመመረጥ መብት ለኣንዳንዶች በመምረጥ ብቻ ይገድብ ነበር።

የሆኖ ሆኖ ግን ጋዜጠኛዋ አንተ እንደሳልካት በራስ ቅሏ ውስጥ ምንም የሌለ ግለሰብ እንዳልሆነች አንተም ትታሰር ስትል መስክረህላታል። ምክንያቱም ስጋት ያልሆነን አካል ወይንም ግለሰብን ገለል ማድረግ ተለምዷዊ አካሄድ አይደለምና። በእርግጥም፦ አንተ እንዳልከው ... ጠቅላይ ሚንስትሩ ዛሬ "የኢትዮዽያ ምልክት እንጂ የአቶ አህመድ አሊ ልጅ አይደሉም"። ስለዚህም ጋዜጠኛዋ እንደ ኢትዮዽያዊነቷ ግለሰቡ የሚሰጡዋት ምልክት ካልተስማማት መቃወም ጠቅላይ ሚንስትር አብይ የሚሰጡዋት ሳይሆን አላህ አስቀድሞ የሰጣት ... ሊያሳሰራትም ሆነ ሊያሳፍራት የማይገባ ሰብዓዊ መብቷ ነው።

በተረፈ ... ለመልስህ አሁንም በድጋሚ አመሰግናለሁ። አንተ እንዳልከው ከዚህ በላይ ብዙ መሔዱ ከንቱ ድካም መስሎ ይታየኛል።

Educator
Member
Posts: 2370
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by Educator » 12 Dec 2021, 00:11

Ditto.
Wedi wrote:
11 Dec 2021, 22:51
ታምራት ነገራ እና ማዕዛ መሐመድ የመሳሰሉ ምርጥ ኢትዮጵያውያንን ማሰር የአብይ አህመድ የመሸነፍ ምልክት ነው!! እጅግ ያሳፍራል!!
በህጻኑ ንጉስ አብይ አህመድ አስተሳሰብ በቃ እሱን ያላሞገሰና እና እንደ ፈጣሪ ያላመለኩ ሁሉ የኢትዮጵያ ጠላት!! ማፈርያ ነገር ነው!!

Horus
Senior Member+
Posts: 42869
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by Horus » 12 Dec 2021, 01:09

TGAA
በምንም መለኪያ አቢይ አህመድ ሆነ ብሎ ለፖለቲካም ሆነ ለሌላ ጥቅም ስብዓዊ መብት ጣሰ፣ ሴት ደፈረ፣ ተማሪ አገደ፣ ንብረት ዘረፈ፣ አገር ሸጠ የሚል መረጃ ካለ ይቀረብ! ከዚያ ውጭ የማንም አክራሪ የዘር ፖለቲኛ ግዜው ከሚጠይቀው አማለካከት ውጭ ጻዲቅ ለመሆን መጣር እኔ ሮማቲሲዝም ብዬዋለሁ። ባለፈው 3 አመት በኢትዮጵያ የተፈጸሙ ግፎች ሁሉ የተደረገውና የተቀናበረው በትግሬ ዘር ፖለቲከኞች እና ኦሮሞ ዘር ፖለቲከኞች ነው። አቢይ እነዚህን ሁሉ ሊቁቋም አለመቻሉ ዛሬም፣ አሁን ከትግሬ፣ ሸኔና አሜሪካ ጋር የሚደረገው ጦርነት ምስክር ነው ። ታዲያ ከዚህ ትግሬ ለፈጠረው መከራ ለምንድን ነው አቢይ የሚቀጠቀጠው? ደግሜ ለበለው፣ መዓዛ ምን ተግባራዊ ሊሆን የሚችል መፍትሄ ነው ያቀረበችው?
Last edited by Horus on 12 Dec 2021, 22:24, edited 2 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42869
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by Horus » 12 Dec 2021, 01:37

አሰግድ
እኔም አንድ ሁለት ነገር ብዬ ነገሩን በዚያ እንተወው። መአዛ ጋዜጠኛ አይደለችም አልኩኝ እንጂ ተቃዋሚ ፖለቲክኛ አይደልችም አላልኩም ። አንድን ፖለቲከኛ የሚነዳው ሞቲቬሽን እና አንድ ጋዜጠኛን የሚነዳው ፍላጎት የተለያዩ ናቸው ። የጋዜጠኛ አላማ እንደ ማንኛውም ኮሚኒኬሽን ስራ አራት አላማዎች አሉት፤ እነሱም አዳማጩን ማነሣሳት (ሞቲቬት ማድረግ)፣ ማስተማር፣ መረጃ መስጠት (ኢንፎርም ማድረግ) ወይም ማዝናናት ናቸው ። ይህ የማንኛውም ኮሚኒኬሽን ተግባር ነው ። ጋዜጠኛ ጋዜጠኛ የሚያሰኘው አንድን የተፈጠረ ነገር ምንድን ነው፣ ማን አደረገው፣ ለምን አደረገው (ለምን ሆነ)፣ መቼ ሆነ፣ የት ቦታ ሆነ ብሎ በማየት ወይም የሰማንውን በሌላ ማረጋጫ ዘዴ መስርቶ ፋክት፣ ሃቅ ለሰሚውና አንባቢው በማቅረብ ከዚህ ፋክት የሚወጣውን ትርጉምና መዘዝ ለአዳማጩ መተው ነው ። ይህ ጋዜጠኛነት ይባላል። ከዚህ ባለፈ አንድ ጋዜጠኛ ነኝ ብሎ የሚመላለስ ሰው የራሱን እውነት፣ የራሱን እምነት፣ የራሱን ውሳኔ፣ የራሱን አቋም ተቀባይነት እንዲያገኝ፣ የሌላው እንዲወድቅ የሚያነሳሳ፣ የሚያስተምር፣ ወዘተ ፖለቲከኛ ይባላል። ልዩነቱ ይህ ነው። ፖለቲካን የሚነዱት ፍላጎቶች ስልጣን፣ ገንዘብ፣ ዝናና ክብሮ ይባላሉ ። ለዚህ ነው የተቃዋሚ ፓርቲ ብትሆን ያምርባታል ያልኩት! በቃ! አቢይ ለተፈጸሙ ግፎች ተጠያቂ ነው የምትል ከሆነ አቢይ ምን አይነት ግፍ እንደሰራ፣ ለምን፣ መቼ እና የት ቦያ በአይኗ በመመስከር ወይም የሰማችውን አቢይ ለመፈጸሙ ፋክት ካላቀረበች በተቀር የራሷን እምነት፣ ፍላጎት፣ የራሱን እውነት ነው በጋዜጠኛነት ስም የምሰብከው ማለት ነው።

ለምን እንደ ታሰረች እኔ የገባኝ ዛሬ ያለነው ባስቸኳይ ግዜ አዋጅ ስር ነው። አንድም ሰው ይህን ሲያነሳ አላየሁም።

ሰላም ክረም

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by TGAA » 12 Dec 2021, 03:31

Horus wrote:
12 Dec 2021, 01:09
TGAA
በምንም መለኪያ አቢይ አህመድ ሆነ ብሎ ለፖለቲካም ሆነ ለሌላ ጥቅም ስብዓዊ መብት ጣሰ፣ ሴት ደፈረ፣ ተማሪ አገደ፣ ንብረት ዘረፈ፣ አገር ሸጠ የሚል መረጃ ካለ ይቀብ! ከዚያ ውጭ የማንም አክራሪ የዘር ፖለቲኛ ግዜው ከሚጠይቀው አማለካከት ውጭ ጻዲቅ ለመሆን መጣር እኔ ሮማቲሲዝም ብዬዋለሁ። ባለፈው 3 አመት በኢትዮጵያ የተፈጸሙ ግፎች ሁሉ የተደረገውና የተቀናበረው በትግሬ ዘር ፖለቲከኞች እና ኦሮሞ ዘር ፖለቲከኞች ነው። አቢይ እነዚህን ሁሉ ሊቁቋም አለመቻሉ ዛሬም፣ አሁን ከትግሬ፣ ሸኔና አሜሪካ ጋር የሚደረገው ጦርነት ምስክር ነው ። ታዲያ ከዚህ ትግሬ ለፈጠረው መከራ ለምንድን ነው አቢይ የሚቀጠቀጠው? ደግሜ ለበለው፣ መዓዛ ምን ተግባራዊ ሊሆን የሚችል መፍትሄ ነው ያቀረበችው?
Horus,
የመሪን ድክመት መጠቆም ማለት ተራ ወንጀለኛ ነው ብሎ መክሰስ አይደለም፡ ግን እንደመሪ ሰብአዊ መብቶች በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ቦታ፤ ተመሳሳይ የህብረተሰብ ሲጠቃ ጠንከር ያለ አቋምን አለማሳወቅ ፤ ስርአት ህግን በተለያዩ በሚገኙ የመንግስት መዋቅሮች ይህ አቋም እንድስርጥ ማድረግ የማይቻል ነገር አይደለም ፤ ወያኔ እጅ በዚህ ሁሉ ወንጀል ስላለበት የሰው ሰቆቃን ምንጣፍ ስር አይደበቅ ፤ ቅድምያ ይሰጠው ማለት "አክራሪ የዘር ፖለቲኛ "ግዜው ከሚጠይቀው አማለካከት ውጭ "ጻዲቅ "ለመሆን መጣር እኔ "ሮማቲሲዝም"ብብ ብዬዋለሁ" በሳቱ እየተለበለቡ ላሉት ኢትዮጵያዊና ስለስቆቃቸው የሚቆምላቸው ፤ የሚከላከላቸው፤ የሚሰራውን ግፍ የሚያወግዝላቸው መሪ ነው የሚፍልጉት እንጂ ስለስቆቃቸው ምክንያት የሚደረድርልቸውን ሰው አይደሉም ፤ ዘረኛ አክራሪ እና የመሰለ ቅጽል መጠቀሙ ግልጽ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ላንተ የሰው ስቃይ አብስትራክት ነው ፤ ለሚኖሩት ፤ ለሚሞቱት ፤ ለሚፈናቀሉት የሚከፍሉት አንድና ብቸዋን ህይወታቸውን ነው ፤ አቋምህን ግልጽ ስላደረክ ፤ በዚህ ላይ ብዙ የውይይት ጉዞ ማድረግ ስለማንችል ፤ በዚሁ ብንቋጨው መልካም ነው፡፡

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: መአዛ መሃመድ፣ ቀንደኛ ጸረ አቢይ! ቦታዋ ቃሊቲ ነው

Post by Guest1 » 12 Dec 2021, 05:04

ስውዪው ሆረስ
ዲሞክራሲ እያሉ የመናገር መብት መክልከል?

አቢይ ደስ የሚል ነገር አለው። ቀና አሳቢና ጥሩ ተናጋሪም ነው። ባይገርምህ አቢይን የሚወዱት ግን እናቶች ብቻ ቢባል ስህተት አይሆንም። እናቶች የጦርነትን ክፋት ስለሚያውቁ፤ ልጆቻቸው የሚጎዱበት፤ እነሱም የሚንገላቱበት፤ ተደፍረው የሚዋረዱበት (tearing up) አገርም የሚታጣበት እንደሆን ስለሚረዱ። ምናልባት ምናልባት አቢይ ስለዘመተ ወዲህ ሰራዊቱ ለጊዜውም ቢሆን በሱ ደስተኛ ሊሆን ይችላል።

የሚያሳዝነው አሁን አቢይ ከእናቶች በስተቀር ወዳጅ የለውም። ለምን? በርህራሄ ሁሉንም ለማስደሰት በመሞክር አገርን መምራት ስለማይቻል። የመሃለኛነት አቋም የሚያመጣው ጣጣ መጨረሻ ላይ መሪው በሁሉም የተጠላ ይሆናል። ለላው አቢይ አፍቃሪዎች ያልተረዱት አገር የምትበተነው በሁለት መንገድ ነው ፤ በጦርነት ወይም ከመንግስት። ለምን አቢይ ይተቻል የሚሉት ስህተታቸው እዝህ ላይ ነው።

ከውጭ ሆነን ውስጥ ያለውን ማየት እየሞከርን መለፍለፍ እንችላለን። እዚያ አገር ላይ ሆነው ኑሮውን ኖረውት የሚተቹትን አፍ ለማዘጋት መጣር አስተዛዛቢ ከመሆኑም በላይ የመናገር መብት መከልከል አገርን/መንግስትን እንደሚጎዳ አለመረዳት ነው።

ኢትዮን ፈጣሪ ይጠብቅ

ሊንኩን አላዳመጥኩም። ስድብ ስለሚበዛበትም ፖስት የተደረገውን አላነበብኩም!

Post Reply