Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
ethiopianunity
Senior Member
Posts: 10972
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

ለምን ኢትዮዽያ ከሊብያ፣ሲሪይ ወዘተ በተለይ ከየመን ምሳሌ ኣልወሰደችም?

Post by ethiopianunity » 18 Nov 2021, 03:23

ኣሜሪካ እንደምናውቀው ለመጉዳት የሚፈልጉትን ኣገር ነገር ይፈልጋሉ ኣስቀድመው። ይህን ኣይተነዋል በጃፓን ጥቃት። ዛሬ ደሞ ካስታጠቁት ግብረኣበሮቻቸው ጋር ኢትዮዽያን የሚያጠቁ ነጻውጪዎች ጥቃቱን ይፈጽሙላቸዋል። ግን ለምንድን ነው ከተጠቁት ኣገራት ኢትዮዽያ ትምህርት ያልወሰደችው? ለምሳሌ ኣረብ ኣገራት በህዝብ ብዛትና በሩስያ ቻይና መሳርያ በመመካት፣ ኣሜሪካንን በግልጽ ኣወገዙ፣ ለሱም ዋጋ ከፈሉ። የኢቶዽያ ህዝብና ያሁኑ መንግስት በሚያማክሯቸው ቡድኖች ተሸውደው ኣሜሪካንን ኣወገዙ። እንደምናውቀው፣ ንጉስ መሪዎቻችን ኣገርን በመጠበቅ ስኬታማ የሆኑት ጦርነት ቢደርስባቸውም፣ ህዝቦቹና ንጉሶቹ ኣቤቱታ ለኣለም ህዝብና ኣገራት ኣቅርበዋል በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ጦርነት ላይ እንኳን እየሆኑ።

ስለዚህ መንግስትም ሆነ ህዝብ ራሱን ይፈትሽ ባይ ነኝ። በማንኛውም ምክኛት እንደ ዶሮ መገነጣጠል ማለት ኣይደለም ለኢትዮዽያ ህዝብ፣ ነጻውጪዎች እንዋጋላችሗለን ለሚሉት ህዝብ እንኳን እየጨረሧቸው ነው። የኣፍሪካ ቀንድንና ኣፍሪካን ህብረትን ኣንዱ የውጭ ባለሞያ እንዳለው በቅርብ ቀን ምድረበዳ የማድረግ ኣላማ ነው ምናልባት ከኤርትራ በስተቀር። እውነትም እንዳለው ኣላማው የኢሉምናቲ እቅድ እርስ በርስ ማጨራረስ። እውነትም ካልጠበቁትና ከሚጠሉት የክርስትና እርስ በርስ መጨራረስ በ ኢትዮዽያ ውስጥ ትልቅ ስኬታማ ነው።

ነፃነት በነፃ የሚሰጥ ኣይደለም።