አዳነች አቤቤም ጩጬውም እንደነገሩን ትግራይ ብትገነጥልና ብትሄድ ደስታቸውን አይችሉትም። ታዲያ ለምንድነው የምትዋጉት? እስኪ አሁን ትግራይ ከፈለገች መሄድ ትችላለች እያሉ የድሃ ልጅን ውጣና "አገርን ሊያፈርስ የመጣን ጠላት ተዋጋ" ብሎ ነገር ምንድነው?
ሌላውስ ክልልና ብሄር እየተነሳ ቢሄድና ቢገነጠል ታዲያ ምን ገዷችሁ ነው?
የምትዋጉበት በቂ ምክንያት የላችሁም ስንል በምክንያት ነው። ምክንያት አላችሁ ከተባለም፤የድሃን ልጅ ውጣና በመቶ ሺዎች እለቅልኝ የምትሉት :-
1. ባለፉት 30 ዓመታት የተፈጠረውን የህዝብ ሃብት የትግራይን ልሂቅ ገለል አድርጎ ለመቀራመት የምትችሉ ስለሚመስላችሁ ( ባለፉት 3 ዓመታት ከውድመት የቀረውን)
2. የትግራይ ህዝብ በመሃል ከተማና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያፈራውን ሃብት በጦርነትና በግጭት ስም መዝረፍ (ፋሽስቶች በአይሁዶች ላይ ሲፈጽሙት እንደነበረው)
3. እስካሁን ከፈጸማችሁት ወንጀል የድሃ ልጅንና ገበሬን ጭዳ በማድረግ ከተጠያቂነት የምትድኑ ስለሚመስላችሁ (ቢቻል ለኢሳያስና ሻዕቢያም ጠበቆች ለመሆን)
4. የጦርነት ላይ ሽንፈትን በግል ወስዶ ፤ ካላሸነፍኩ ነገ ይህ ጦርነት መሰደቢያ ይሆነኛል በሚል የፈሪ በቀል የሚብከነከን ማንነት ስላላችሁ ( ንግስናው በ7 ዓመቱ የተነገረለትን ሰው እንዲህ ማዋረድና በዓለም ፊት የህጻናት ተረት ላይ ያለ ገጸባህሪ አድርጎ መስቀረት ተገቢ ነው?)
ሌላ ምን ምክንያት አላችሁ? ምንም።
Please wait, video is loading...