Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
ethioscience
- Member
- Posts: 4102
- Joined: 01 Nov 2019, 17:37
Post
by ethioscience » 17 Nov 2021, 05:29
ሰበር ዜና
#Ethiopia : ወረይሉ በደቡብ ወሎ ከሸዋ በስተ ሰሜን የምትገኝ ከተማ ናት።ወረይሉን ተቆጣጥሮ ወደፊት የመግፋት ፍላጎት ያለው የህወሃት የሽብር ቡድን በዚህ ግንባር ሁለት ክፍለ ጦሮችን በማሰለፍ ትናንትና እና ከትናንት ወዲያ መጠነ ሰፊ ውጊያ ለማድረግ ሞክሯል፡፡
ይሁንና ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከአካባቢው ታጣቂ፣ ሚኒሻና ፋኖ ጋር በቅንጅት በቡድኑ ላይ በከፈቱት የማጥቃት እርምጃ የጠላት ሀይል ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል፡፡በዚህም በርካታ የቡድኑ ታጣቂ ሀይሎች ሲደመሰሱ፤ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሀይል ቁስለኛና ምርኮኛ መሆኑን በስፍራው የሚገኙ የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡
የመረጃ ምንጮቻችን በጃማ ሆስፒታል ክትትልና እንክብካቤ እየተደረገላቸው ካሉት በርካታ የጁንታው ቁስለኞችና ምርኮኞች መካከል በካሜራቸው ካስቀሩት የጥቂቶችን ምስል በማስረጃነት አስደገፍው በመላክ፤ በዚህ ግንባር አሸባሪው ቡድን እስትራቴጂካዊ ፍላጎቱን ለማሳካት በተደጋጋሚ ወረራና ጥቃት ቢፈፅምም፤ በዋናነት ሀገር ወዳዱ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ብርቱ ክንዱን በማሳረፍ በተደጋጋሚ ሽንፈቱን እንዲጋት እያደረገው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በዚህ ግንባር እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት ከሰጡት ቁስለኞችና ምርኮኞች መካከል አብዛኞቹ እድሚያቸው ከ20 ዓመት በታች የሆኑና አዛውንቶችም ጭምር እንደሚገኙበት ምንጮቻቸን ገልጸዋል
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
-
Wedi
- Member+
- Posts: 8649
- Joined: 29 Jan 2020, 21:44
Post
by Wedi » 17 Nov 2021, 06:44