Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member+
Posts: 5071
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

የ20ኛና 21ኛ ክ/ዘመኑ ኤርትራዊ ታጋይ ተሰዋ! በቃላቱ ሲዘከር - ኣልኣሚን መሓመድ ሰዒድ

Post by Meleket » 16 Nov 2021, 09:18

ቀድመው ለኤርትራ ነጻነት ትግል በአካል ወደ ትግሉ ሜዳ በማቅናት በወኔና በቁርጠኝነት የነጻነት ትግሉን ከተቀላቀሉት ታጋዮች ይመደባል። ይህ ከነባር ኤርትራዊያን ታጋዮች መካከል አንዱ የሆነው አገሩን በቦለቲካና በዲፕሎማሲ ያቅሙን ያህል አገልግሏል። በቅርቡ በ74 ዓመት ዕድሜውም ኤርትራዉያንን ለማንቃት ወደ ሳውዲ ኣረብያ አቅንቶ ሳውዲ ኣረብያ ውስጥ በህመም ተሰውቷል። ለትግል የተሰለፈውም ከሳውዲ አረብያ እንደሆነ ይነገራል። ባመነበት ዓላማ በ20ኛዉና 21ኛዉ ክ/ዘመን ለኤርትራ ነጻነት ሲል የታገለው ኤርትራዊ ታጋይ ኣልኣሚን መሓመድ ስዒድ ይባላል። ለቤተሰቡ መጽናናቱን እየተመኘን እግረ መንገዳችንንም ለቅምሻ ያህል ከታሪክ ማህደር ፈልቅቀን ከዚህ ኤርትራዊ ታጋይ ኣንዳንድ ቃላቶችን እንጠቅሳለን፡-

የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ግጭትን ለመለኮስ ህወሓት ማለትም ወያኔ ትግራይ የመጀመሪያውን ሴራ ስትሸርብና የጦርነት እሳት ለማቀጣጠል ክብሪት ስትጭር፡ አልኣሚን የነበረውን ሁኔታ በሚያንጸባርቅ መልኩ ወያኔ ትግራይን ዕርቃኗን ሲያወጣ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኛ በሰጠው ትንተና አዝናኝ በሆነ መልኩ እንዲህ ብሎ ነበር፦

ኣልኣሚን መሓመድ ስዒድ በ2021 ለአገር ውስጥ ጋዜጠኛ እንዲህ ብሏል wrote: “ወያኔ ትግራዮች ከትግራይ ተሻግረው በምሥራቃዊው የኤርትራ ክፍል ዓድምሩግ የተባለች የኛን ቀዬ በማንኣለብኝነት ሲያዙ “ለምን ያለሥፍራችሁ ገባችሁ?” ብለን በጨዋ ደንብ ብንጠይቃቸው፡ ወታደራዊ ስልጠና የወሰድንበት ቦታ ነው ብለው ድርቅ ኣሉ። ስልጠና ለስልጠናማ ሰሜን ኤርትራ ጫፍ ሳህል ውስጥም ብሌቃትና ዓራግ ላይ ወዘተ ላይ ጭምር አሰልጥነናችሁ የለ፡ በዚህ እሳቤና ስሌትማ ዓዲምሩግ ብቻ ሳትሆን ብሌቃትም ዓራግም የኛ ናቸው ልትሉን ነው ማለት ነው?” ኣልናቸው።

አልኣሚን መሓመድ ስዒድ ታጋይና የቦለቲካ ሰው ብቻ ኣልነበረም፡ ከመትረየስና ከታንክ ባለፈ ሁኔታ በቦለቲካው ትግል የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደረገ ታሪክን በብዕሩ በመሰነድ ግሩም ተልእኾዉን የተወጣ ጸሓፊም ነበር። “ሰውራ ኤርትራ” የተሰኘች መጸሐፉን በ1994 ለንባብ ኣብቅቷል። ብዙ ያልተጻፈለትን “መንካዕ” ስለተባለው በነጻነት ትግሉ ወቅት ስለነበረ ‘ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴም’ አልኣሚን ኣመለካከቱን በመጸሓፉ እንዲህ ኣስፍሮ ነበር።

ኣልኣሚን መሓመድ ስዒድ ብ 1994 ዝደረሳ መጸሓፍ ‘ሰውራ ኤርትራ’ከምዚ ይብል wrote: “ክልቲኡ ወገናት ህ.ሓ. ካብ ዝሰምር ወርሒ ኣብ ዘይመልእ ግዜ ብሽም “መንካዕ” ዝፍለጥ ብኣብ ካልኣይ ወገን ህ.ሓ. ዝነበሩ ባእታታት ዝተወልዐ ሓደ የማናዊ ኣዕናዊ ምንቅስቓስ ተቐልቀለ። ዕላማ ናይ’ዚ ምንቅስቓስ እዚ፡ ኣብ ውሽጢ ህዝባዊ ሓይልታት ሓርነት ኤርትራ “ዲሞክራሲ የለን” ብዝብል ጭርሖ ተጋደልቲ ኣንጻር መሪሕነት ንምልዕዓል ኢዩ ነይሩ።

ኣብ ወርሒ ሚያዝያ 1973 ዝተመዘዘት ሽማግለ መጽናዕቲ ብዝዓደመቶ ኣባላት ሓጋጊ ኣካል ዝተረኽብሉን ኣኼባ፡ ኣብ ዕለት 3 ጥቅምቲ 1973 ተኻይዱ። ሓደ ካብ’ቶም ቀንዲ ባእታታት መንካዕ፡ ሙሴ ተስፋሚካኤል ዝተባህለ፡ አብ ውሽጢ ህዝባዊ ሓይልታት ሓርነት ኤርትራ ሓቀኛ ዲሞክራሲ የለን ዝብል ጉዳይ ኣልዒሉ። ውልቀ-ምልካዊ ኣተሓሳስባ ክቕጽለሉ ዝኽእል ዕድል’ዩ ዝፈጥር ዘሎ ከኣ በለ። (ወዘተ) እናበለ ኣልኣሚን መሓመድ ስዒድ ምስክርነቱ ሂቡ’ሎ። (ገጽ-49)

ግርድፍ ትርጉም
ኣልኣሚን መሓመድ ስዒድ በ1994 ‘ሰውራ ኤርትራ’ በሚል ርእስ ባስነበበን መጸሓፉ በገጽ 49 እንዲህ ይላል wrote: ሁለቱም የህዝባዊ ግንባር ክፍሎች ተጣምረው አንድ እንደሆኑ ወር ባልሞላ ግዜ፡ “መንካዕ” በሚል ስም የታወቀው በሁለተኛዋ የህዝባዊ ግንባር ክፍል ውስጥ በነበሩ አካሎች፡ አንድ የቀኝ አፍራሽ እንቅስቃሴ ታየ። የዚህ እንቅስቃሴ ኣላማ፡ በህዝባዊዉ የኤርትራ ነጻነት ኃይሎች ውስጥ “ዲሞክራሲ የለም” የሚል መፈክር በማንሳት ታጋዮች ከመሪዎች አንጻር እንዲነሳሱ መገፋፋት ነበር።

በወርሃ ሚያዝያ 1973 የተሰየመችው የጥናት ኮሚቴ ባቀረበችው ግብዣ መሰረት፡ ሕግ ኣርቃቂ ኣካሎች የተገኙበት ስብሰባ ጥቅምት 1973 ተካሄደ። ከመንካዕ ዋንኛ ኣካሎች ኣንዱ፡ ሙሴ ተስፋሚካኤል የተባለ፡ በኤርትራ ህዝባዊ ነጻነት ኃይሎች ውስጥ እውነተኛ ዲሞክራሲ የለም የሚል ጉዳይን አነሳ። አምባገነናዊ አስተሳሰብ ሊቀጥልበት የሚችል ዕድል ነው እየተፈጠረ ያለው። (ወዘተ)

በማለት ካዛሬ 48 ዓመታት በፊት የተከናወነን፡ የኤርትራ ህዝብ የትግል ታሪክ ውስጥ አንድ ሁነኛ ምዕራፍን፡ በብዕሩ ለተተኪው ትውልድ ያመነበትን አመለካከት ያቀረበ ታጋይ ነው አልኣሚን መሓመድ ሰዒድ።

ታጋይ ሙሴ ተስፋሚካኤል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን በማቋረጥ የኤርትራ ህዝብ ትግልን በአፍላ ዕድሜያቸው ከተቀላቀሉ “ዲሞክራሲያዊ ኣመለካከት” ነበራቸው ከሚባሉ ወጣት ታጋዮች አንዱ እንደነበር ይነገርለታል።

በኤርትራ ነጻነት ዋዜማ ታጋይ ኣልኣሚን መሓመድ ስዒድ ከደርጉ ጋር ይደረጉ በነበሩ ድርድሮች ኤርትራን ወክሎ የተደራደረ ዲፕሎማት ነበር።

ታጋይ ኣልኣሚን መሓመድ ሰዒድ በሰላም ዕረፍ!

ታጋይ ሙሴ ተስፋሚካኤል በሰላም ዕረፍ!

ለቤተሰቦቻችሁና ለትግል ኣጋሮቻችሁ ለኤርትራ ህዝብም ጭምር ጽናትና መጽናናት!