Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ኢትዮ ቴሌኮም በጦርነቱ ሳቢያ በሦስት ወራት 1.9 ቢሊዮን ብር ገቢ ማጣቱ ታወቀ - Reporter

Post by sarcasm » 15 Nov 2021, 17:26

ኢትዮ ቴሌኮም በጦርነቱ ሳቢያ በሦስት ወራት 1.9 ቢሊዮን ብር ገቢ ማጣቱ ታወቀ
14 November 2021
በጋዜጣዉ ሪፓርተር
ሳፋሪ ኮም ከኢትዮ ቴሌኮም መሠረተ ልማት ለመከራየት ድርድር ላይ ነው

በአሸናፊ እንዳለ

ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 ዓ.ም. የመጀመርያ ሦስት ወራት ውስጥ 1.9 ቢሊዮን ብር ገቢ ማጣቱን ገለጸ፡፡ በዚህም ምክንያት የ2014 የመጀመርያ ሩብ ዓመት ዕቅዱ ከ15.4 ቢሊዮን ገቢ በ12 ከመቶ መውረዱን ሪፖርተር አረጋግጧል፡፡

ድርጅቱ የሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርቱን ለገንዘብ ሚኒስቴርና ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች ኤጀንሲ በሒልተን ሆቴል ያቀረበ ሲሆን፣ አጠቃላይ ትርፉ 5.9 ቢሊዮን ብር ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህም ለሩብ ዓመቱ ካቀደው 4.8 ቢሊዮን ብር በ1.1 ቢሊዮን ብር በልጧል፡፡

‹‹አገልግሎታችን በሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ፣ ሙሉ ትግራይና ከፊል አፋር ውስጥ ተቋርጧል፡፡ ይህም ሆኖ ለማድረግ የቻልነው ሰላማዊ በሆኑት የአገሪቱ ክፍሎች አገልግሎታችን በማብዛትና ጠንከረን በመሥራትና በሰሜን ያጋጠመንን የገቢ መውረድ ለማካካስ የቻልነው፡፡ በአጠቃላይ ካለበት መቀዛቀዝ አንፃር 88 በመቶ ዕቅዳችንን ማሳካት ትልቅ አፈጻጸም ነው፤›› በማለት ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የኢትዮ ቴሌኮም ማኔጅመንት አመራር ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በሩብ ዓመቱ የቴሌ ብር ደንበኛ ቁጥር ከ9.8 ሚሊዮን ወደ 10 ሚሊዮን አድጎ 2.1 ቢሊዮን ብር ግብይት የተደረገ ቢሆንም፣ ትርፍ ማስገኘት እንዳልተጀመረ ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

Continue reading https://www.ethiopianreporter.com/article/23742