Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Hellen
- Member
- Posts: 246
- Joined: 09 Oct 2019, 11:06
Post
by Hellen » 06 Nov 2021, 00:33
ህወሃት ከአማራና ከአፋር ክልል ሙሉ ለሙሉ ካልወጣና እያካሄደ ያለውን ሁከት እና ጥቃት ሙሉ ለሙሉ ካላቆመ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ምንም ዓይነት ድርድር ሊካሄድ እንደማይችል ሁለት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት ዛሬ ለአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርና ለውጭ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ህወሃት ትጥቁን ፈትቶ ወደ ትግራይ ካልተመለሰ ድርድር እንደማይኖር የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል!
የኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስቴር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ቃል አቀባይ ቢልለኔ ስዩም ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት ዛሬ ለአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርና ለዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች በኢንተርኔት ላይ በተደረገ ውይይት በሰጡት መግለጫ፤ ህወሃት በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ጥቃት ለማድረስ እያሴረ መሆኑ ተጨባጭ የደህንነት መረጃ እንደደረሳቸው ገልፀዋል።
የጤና ክፍል
ጠቃሚ የጤና ትምህርት
የልብ ድካም መንስኤዎችና መከላከያ ወሳኝ መንገዶች። ለጥንቃቄ መታየት ያለበት። መፍትሄዉ በእጃችን ነዉ:: ለማየት ሊንኩን ወይም ምስሉን ይጫኑ