የነመሳይ ምክር ሰምታችሁ ተጋሩ ላይ እጃቹሁን የምታነሱ ኣፋቹሁን የምትከፍቱ 2 ሃቆችን ልንገራቹህ፦ 1, ሲቪል ተጋሩን በመግደል በማስር የሚቀየር ወታደራዊ ነገር የለም። 2, አንለቃቹሁም!
ኣንለቃቹሁም
ኣብይና የወንጀል ተባባሪዎቹ በባህርዳሩ የፍፃሜ ስብሰባ ላይ የሚከተለውን የኑዛዜና የጭካኔ ሃሳብ ሰንደዋል፡፡
«ሕወሃት የጀመረውን ሀገር የማውደምና የማፍረስ ተልዕኮ በመደበኛ ወታደራዊ አደረጃጀት ብቻ መቀልበስና መቅበር አይቻልም። መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በማነቃነቅና ባለቤት በማድረግ የአገርን ህልውና ከሁሉ አቀፍ ጥቃት መከላከል ያስፈልጋል፡፡»
ይህ ምን ማለት ነው?
1.መከላከያ፣ የኣማራና የሁሉም ክልል ልዩ ሃይሎች፣ ፋኖ ምሊሻ፣ የኢሳያስ ጦር፣ የቱርክ ድሮን፡ የሶማልያ እግረኛ ብናሰልፍም ቅሉ ትግራይ ዱቄት ኣድርጋናለች። ተሸንፈናል! ደቀናል። ተስፋ የለንም፡፡ ባጭሩ ትግራይ ትስዕር! እያሉ ነው፡፡
2. የኢትዮጵያ ህዝብ የዘር ማጥፋት ኣጀንዳችን በምንፈልገው መጠን እንዲፈፀም የዘር ማጥፋት ስራውን ወደ ህዝብ ኣውትሶርስ (out source) አድርገን የዘር ማጥፋት ኣጀንዳው ባለቤትነቱ ከኛ ወደ ህዝቡ ይተላለፍ ነው እያሉ ያሉት፡፡ "የኛና የህዝቡ ፀሎት ተለያይቷል፡፡ ኣልተግባብቶም!" ከሚል ቁጭት የሚመነጭ የዘር ማጥፋት ኣጀንዳን ባለቤትነት የማዛወር ጥሪ ነች፡፡
3. እኛና የውጭ ወራሪዎች ስላልቻልን፣ ሚስኪን የጦብያ ህዝብ ሆይ! መድፍ፣ ጀትና ሄሊኮፕተር፣ ድሮን፣ ቢኤም፣ ዶሽካ፣ብሬን፣ ስናይፐርና የማይታየው የዳንኤል ክስረት ሃይል ይዘን ያልቻልነውን የትግራይ ሃይል፤ በርበሬ፣ ገጀራ፣ ወንጭፍ፣ ጩቤ እና ሚጥሚጣ ታጥቀህ ግጠምልኝ፡፡ ጁንታ ይዛኝ በዘር ማጥፋት ወንጀል ከሳ ከምድረገፅ ልታጠፋኝ ስለሆነ፤ መላዉን የትግራይ ህዝብ በማጥፋት ኣድነኝ ነው እያሉ ያሉት፡፡
ይህንን ተከትሎም እነ መሳይ መኮነን፥ የኣብኑ ጋሻው መርሻ እና የስርዓቱ ኣክቲቪስቶች "ሁሉም ትግራዋይ ወደ ማጎርያ ካምፕ ተወስደው ፈጣን እርምጃ ይወሰድባቸው" ማለት ጀምረዋል፡፡ በተበላ እቁብ ተሰፋ የሚያደርጉ መኖራቸው ችግር የለውም፡፡ ሂወታቹሁን የምትፈልጉ ግን እራሳቹሁን ከወንጀልና ከወንጀለኞች ኣርቁ፡፡ መቃብር ኣፋፍ ላይ የደረሰን የወንጀለኞች ስብስብ ለማዳን ተጋሩ ላይ እጃቹሁን የምታነሱ፥ ኣፋቹሁን የምትከፍቱ ዘር ኣጥፊዎች ሁለት ሃቆችን በርግጠኝነት ልንገራቹህ፦
ኣንደኛ፡ ሲቪል ተጋሩን በመግደል፥ በማስር ወይም በመበደል የሚቀየር ወታደራዊ ነገር የለም፡፡ ኣብይና ስብስቡ መጠገን በማይችልበት ደረጃ ተደቁሰዋል፡፡
ሁለተኛ፡ ወደ ኣራቱም ኣቅጣጫ ብትሄዱ፥ ወደ ወጭ ኣገር ብትሸሹ፥ እናታቹህ ቀሚስ ስር ብትደበቁም ኣንለቃቹሁም፡፡ እደግመዋለሁ፤
ኣንለቃቹሁም!
Please wait, video is loading...