Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
ethiopianunity
Senior Member
Posts: 10970
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

ያሁኑ መንግስት ፈተና

Post by ethiopianunity » 02 Nov 2021, 14:52

ህዋሃት ሲገባ መጀመርያ ዋና ኣላማው ዘርን ብሄርን ኣላማ ኣድርጎ ነው። ኢትዮጵያን ለማዳከም ከፋፍሎ የቆየበት ምክኛት ኣገሪቱን ለማፍረስ ነው በመጨረሳው ሰኣት የሚፍለገውን መሬትናን ኣባይን በመውሰድ። የሚመርጣቸው ጎሳዎች ህዋሃት ኣገሩን እስከያዘ ድረስ ለመምራት የማይገዳደሩትን ማህበረሰብን ነው፣ ለምሳሌ ደሳለኝ ሃማርያምን ከወላይታ ነው ኣናሳ ብሄረሰብ። በመጨረሳት ሰኣት ግን ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ኣክራሪ ለሆነው ለኦነግ ነው ኣገሩን ኣሳልፎ የሚሰጠው ትግራይን ካስገነጠለ በሗላ። ለዚህም ነው ከኦነግ ጋር ተባብረው የሚሰሩት። ለውጥ ሲመጣ የተመረጡት ለማ መገርሳና ኣብይ ነበሩ። ግን ማን ነው የመለመላቸው፧ እንዴት ነው ኣቋማቸውስ፧ ኢሃድግ ውስጥ ያሉት ምናልባት ያቃሉ እነጂ ማንም የሚያውቅ የለም።

ህዝብ ነበር ንቅናቄውን የጀመረው። ጫፍ የደረሰ ኣገር በንቅናቄ ብቻ ቢቀጥል ኣደጋ ነበር ብዬ ኣምናለሁ ለምን ከንቅናቄው እኩል ህዝብ በሚያውቀው በሚተማመንበት መሪ መዘጋጀት ነበረበት። የኣብይና የለማ መሪነት በጎ ሊሆን ይችላል ዋናው ነገሩ ማን ነው እነሱን እጩ ያደረጋቸው ነው መልሱ፧ በዚህ ክፉ ዘመን ጊዜ በግርግር ረብሻና ንቅናቄ ነው ሁልጊዜ ኣደገኛ መሪዎች ሹልክ ብለው የሚገቡት። ለወደፊቱ የሚሰሩት ያ እንዲመረጡ ላደረገው ሃይል እንጂ ተኣማኒነት ለህዝብ ላይኖረው ይችላል። መራጩ ሃይል መሪውን በሗላ እንደሚፈልገው ያሸከረክረዋል። ለዚህ ነው ኣቶ ደሳለኝ ሃማርያም ምንም ማድረግ ያልቻሉት የመሰለኝ ለዚህም ነው ከኣናሳ ማህበረሰብ በደንብ ተመልምለው ስልጣን ያገኙት ለህዋሃት እንዲያገለግሉ እንጂ ለህዝብ ኣልነበረም። ለምን ይህ ያልኩበት ምክኛት ኣሁንም ኢትዮጵያ ህዝብ በሚተማመንበት፣ ህዝብን ኣንድ ማድረግ የሚችል መሪ ካለ ፍርሃትና ስጋት ላገሪቱ የሚያሰጋውን ኣስቀድሞ ማድረግ ኣለበት። ለምሳሌ ዶር ኣብይ በጎ ቢያስብም የመረጡት ሃይሎች በተለይ በዘር የተተበተቡና ከውጭ ጎረቤት ኣገር ጭምርም ከሆኑ በፍፁም ለኣገርና ለህዝብ መስራት ኣይችልም። መሪው እርግጥ ምክር መውሰድ ይችላል የአራሱንም የሕዝብም ሃሳቦችንና ምክሮችን በመሰብሰብ፣ ለኣገሩ ውሳኔም ሁነ ፈላጭ ቆራጭነት በህዝብ ነው መሆን ያለበት ዶር ኣብይ ውሳኔውን ያስተጋባሉ ማለት ነው።

ለምሳሌ ኣሁንም እንደ ኣቶ ደሳለኝ ምናልባት ከኣናሳ ብሄረሰብ ከሆኑ ኣሁንም ለመረጧቸው ኣገልጋይ እንጂ ለማህረሰብ ኣይሆንም ለምን የመረጠው ሃይል ኣናሳ ማህበረሰቡን በማስፈራራት፣ ግዙፍ ማህበረሰብን ለምሳሌ ኦሮሞን ኣማራን እናስነሳብሃለን በማለት እነሱ እንደፈለጉ ያሽከረክሩታል የፈለጉትን በጅ ኣዙር ኢትዮጵያን ይገዛሉ። ለዚህም ነው ኣገርን በዘር መከፋፈል የሚጠቅማቸው።

ባልተከፋፈለ፣ ኣንድ በሆነ ኣገር ኣናሳም ሆነ ግዙፍ ከሆነ መሪ ቢፈጠር ካለ ህገ መንግስት እንኳ መምራት ይችላል በትክክል ምክኛቱም ያ የነበረ የማህበራዊ የተፈጥሮ ትሥሥር ስላለ። በተለይም ከጤናማ ህገ መንግስት ጋር ሲሆን ኣገሪቱ በሰላም በኢኮኖሚ በማህበራዊ የበለጠ ትዳብራለች።

ለዚህም ነው ወይ ፪፯ ኣመት ጭቆና ህዝቡ ሰልችቶት ቶሎ በሰላም ካለ ትግስት ለውጥ የሚፈልገው ወይም በስውር ኣሁን ዶር ኣብይን መንግስት ልክ እንደ ኣቶ ደሳለኝ ቀዳሚ መሆን የሚገባውን ሰላም ማረጋጋት ሲገባ ይባስ ተብሎ፥ ኣደጋ ሊያመጡ ከሚችሉ ኦነጎቸ ያለምንም ጥርጣሬ እንዲገቡና ሰላማዊውን የኦሮሞን ህዝብ በዘረኝነት ያነሳሱትና ኣገሩቱ የበለጠ እንድትከፋፈል የሆነው። ህዋህትን መቀሌ ያገባው እኮ የ ኢትዮጵያ ወጣቶች በየክፍለ ሃገራቸው ኣንድ ሆነው ቄሮ ፋኖ ዘርማ ናቸው። ምንም ክፍፍልም የለም ነበር በዛን ጊዜ የቄሮ ወጣቶቸ ወደ ባህር ዳር ሄደዋል ፋኖን ለመርዳት እምቦጭ ለመንቀል። ምን ሆነ ዛሬ፧ ኦሮምያ ክ ሃገር ኦነጎች ከገቡ በሗላ ተቆልፏል። የማይፈለገው ማህበረሰብ በ ኦነግና በ ህዋሃት እየተገደለ ነው። ኦነጎችም የ ኦርሞያን ህልም እውን ለማድረግ በመጨረሻው ሰኣት ይመስላል። ህልሙን እውን ለማድረግ በለውጡም ሆነ ባሁኑ መንግስት ውስጥ እንዳለ ግልፅ ነው። ሌላው ጉዳይ ህዋሃት ላይ በየ ክሃገሩ የሚኖሩና በተለይ ኣደጋ ሊያስከትል በሚችሉበት ብዛት ያላቸው በኣዲስ ኣበባና በወሎ ውዘተ ባሉ ቦታዎች ቅድሚያ ሆኖ መሰራት ነበረበት። ለዚህም ምክኛቱ ላይ እንደጠቀስኩት መሪ ማከናወና በሚያስፈልገው ወቅት ምናልባት እያልሰራ ያለው። ለምሳሌ ህዋህት ኣባሎቸ እስከ ዛሬ ድረስ ኣደገኛ ቦታ ውስጥ ተሰግስገዋል ኣሁን እውነታው ሲረጋገጥ መሯሯጥ ነው ኣስቀድሞ ባለመዘጋጀት።

ይህ የሚጠቅም ትችት ነው ብዬ ኣስባለሁ ያሁኑ መንግስት ውደ ትክክል መንገድ እንዲራመድ።