Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
ethioscience
Member
Posts: 4102
Joined: 01 Nov 2019, 17:37

ኔትወርክ ተለቋል‼️ ደሴ በወገን ሃይል ቁጥጥር ሥር መሆኗ ቀጥሏል❗️ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች‼

Post by ethioscience » 30 Oct 2021, 15:08

ኔትወርክ ተለቋል‼️

እንደገለጽነው በወገን ጦር ስትራቴጂካዊ የጦር ኦፐሬሽን ምክንያት ደሴ፣ኮምቦልቻና አካባቢው ተቋርጦ የነበረው ኔትወርክ ኦፐሬሽኖችኑ በስኬት ተጠናቆ አሁን ተለቋል‼️

ደሴ በወገን ሃይል ቁጥጥር ሥር መሆኗ ቀጥሏል❗️

የደሴ ነዋሪ ወደ ቤቱ ገብቶ አርፎ እንዲቀመጥ የተላለፈው ጥብቅ መመሪያ መተግበሩን ተከትሎ አስቀድሞ ደሴ ላይ ድሩን ያደራው የወንበዴው የጥፋት አደረጃጀት የቴሌን ኔትወርክ በመጠቀም ለጠላት ሃይል የወገንን ወታደራዊ ነቃነቄ፣ አሰላለፍ እንዲሁም ሌሎች ወታደራዊ መረጃዎችን አሳልፎ ከመስጠት ባሻገር የድምጽ (Voice Services) እንዲሁም የመልዕክት አገልግሎት (SMS Services) በመጠቀም ውዥንበር እየፈጠረ በመሆኑ አገልግሎቱ ለጊዜው እንዲቋረጥ ሆኗል! በከተማዋ እና በከተማዋ ዙሪያ የተከናወነው ልዩ ዘመቻ በመጠናቀቁ ኔትወርክ ተለቋል !!

ጠላት ጭር ያሉ የደሴ ጎዳናዎችን ፎቶ ለጥፎ “ደሴ በ TDF እጅ ገባች” የሚል ድቤ የሚደበድበው ከላይ እንደነገርኳችሁ ከተማዋ ውስጥ የመሸገው የወንበዴው የጥፋት አደረጃጀት እየፈጠረ ያለውን መሰናክል ለመመከት ሁሉም የከተማዋ ነዋሪ ወደ ቤቱ እንዲገባ በተላለፈው ጥብቅ መመሪያ የተየሳ ብቻ ነው!!
ከተማዋን ለመዝረፍ ተክለፍልፎ የመጣውን ወራሪ ሀይልና መደምሰስ የተቻለ ሲሆን በከተማዋ ከሚገኙ ቅጥረኞን መለየት ችለናል ። በዚህ አጋጣሚ ማን የወገን ሃይል ነው? ማንስ የጠላት ቅጥረኛ ነው? የሚለውን በትክክል ለይተን መዝግበን መያዝ ችለናል !

በዚህ መሠረት የጠላትን ጣቶች የሚቆርጡ ቀጣይ ኦፐሬሽኖችን ለመከወን የሚያስችል ስንቅ ተገኝቷል

🔥
ኢትዮጵያ ታሸንፋለች‼




Post Reply