Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42805
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የምዕራብ የድህነት (የልመና) ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ውስጥ ያጋጠመው ፈተና

Post by Horus » 04 Oct 2021, 18:29

አሜሪካና አውሮፓ የራሳቸውን ገበሬ ለመደጎም መላ አፍሪካን በለማኝነት አይዲዮሎጂ አደንዝዘው ተመድ በሚባል መሳሪያቸውና ወፍ አራሽ ቅጥረኛ ቴክኖክራቶች አሽከርነት ያፍሪካ (ለምሳሌ የትግሬ ሰዎች) ህዝቦች ራሳቸው ሰርተው፣ ጥረው፣ ግረው ፣ለፍተው ፣ በላባቸው አንዳይብሉ የበሰበሰ ስንዴና ሩዝ በነጻ እያደሉ አንድ ሙሉ አገር፣ አንድ ሙሉ ህዝብ ክብሩን ገፈው ሳይኮሎጂውን ደምስሰው ለማኝ አድርገው ይገዛሉ፣ ይቆጣጠራሉ፣ ያዛሉ ፣ ያዋርዳሉ። አሁን ኢትዮጵያ ይህን ብሄራዊ ወርደት፣ ስድብና የኢኮኖኢና የስነ ልቡና ጦርነት እምቢ የሚል መሪ ስናገኝ በግድ ካልለመናችሁ ብሎ በጦር የሚያስገድድ ተመድ እየሆነ ነው።

ይህን አጸያፊ የልመና ባህል፣ ይህን ቆሻሻ የተመጽዋችነት ካልቸር በሰርቶ በልነት፣ በራስ መጋቢነት፣ በራስ ቻይነት ክቡር ካልቸር ለመተካት በግድ አቢይ ያደረገውን አይነት የድህነት ኢንዱስትሪና የለማኝነት አይዲዮሎጂ ከስሩ የሚነቅል እርንጃ ሙሉ ድጋፍ መስጠት አለብን ። የትግሬ ወጣት ሰርቶ ወላጆቹን መጦር ሲገባው ያሜርካ ስንዴ በመሰፈርና ያማራ ሊጥ በመዝረፍ ሰው ሊሆን አይችልም። አንድ ቀን ትግሬ ከዚህ ውርደት ነቅቶ ወደ ሰላሙና ሰብ ዓዊ ክብሩ ተመልሶ ሰርቶ መብላት መጀመር አለበት ። ከኢትዮጵያ ጋራ ሺ አመት ሊዋጋ ይችላል፣ ግን የሱን ችግር በፍጹም አይፈታውም ። ፈረንጅ 500 ትራክ ሙሉ ስንዴ በቀኑ እየሰጠው በሰላም ሰርቶ መብላትን የረሳ ሕዝብ መጨረሻው ውርደትና ወድቀት ነው ። ትግሬ ኢትዮጵያን በመውጋት የህልውና ችግሩን በፍጹም አይፈታም
የተመዱ ጉቴሬስ የገባበት መቀመቅ ይህ ነው ። የትግሬን ችግር የሚፈታው ነገ ወደ እርሻን ስራ የሚመለሰው ወጣት እንጂ የተመድን እጅ የሚጠብቀው ዉሸታም የነጻነት ተዋጊ አይደለም ። ለማኝ ሰው ሆነ ህዝብ በፍጹም ነጻ ሊሆን አይችልም። የነጻነት መጀመሪያ ራስን መቻል ነው!