የተፈጸመው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት (የደ/ጎንደር ዞን ከሚገኙ አራት ወረዳዎች መካከል (ማለትም ላይ ጋይንት፤ ጉና በጌምድር፤ ፋርጣ እና እስቴ)።
- በትግራይ ወራሪ ሀይል 34 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል፡፡
- በትግራይ ወራሪ ሀይል ከ24 በላይ በሆኑ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ለሞት ሊደርግ የሚችል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
- በትግራይ ወራሪ ሀይል በበርካታ ሰላማዊ ሴቶች እና ሃፃናት ላይ የአስገድዶ መድፈል ወንጀል ተፈጽሟል፡፡
- የትግራይ ወራሪ ሀይል በከፈተው ጦርነት ቁጥራቸው ከ65,000 በበላይ ዜጎች ከመኖርያ ቀያቸው ተፈናቀው ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል።
- የትግራይ ወራሪ ሀይል በ1 ሆስፒታል፣ በ13 ጤና ጣቢዎች፣ በ31 ጤና ኬላዎችና በ2 ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤቶች በድምሩ በ47 የጤና ተቋማት ሊይ ዝርፊያና በመፈጸም ተቁማቱን አቅድሟቸዋል። በዚህም የሆስፒታል እና የጤና ጣቢያ አምቡሊንስ፣ የህክምና መሳሪያዎችና መድሃኒቶች፣ እንዲሁም የቢሮ እቃዎች በወራሪው ሃይሉ ተጭነው የተወሰዱ ሲሆን ሌሎች ለጭነት የማይመቹ የህክምና ቁሳቁሶችን ደግሞ ከጥቅም ውጭ እንዱሆኑ አድርጓል፡፡
ሙሉ ዝርዝር ሪፖርቱን ከዚህ በታች ያንብቡ!!