Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42789
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ወንጪ ሃይቅ፣ ምድረ ገነት የዉበት ጥግ

Post by Horus » 31 Aug 2021, 11:43

የእንሰቱ ስር = አሚቾ = እውታ
የመቁረጫው ጎራዴ ሚመስለው = ሰንዳ
የሚፋቀው ኮባ = ቀስላ
የሴቶቹ ደቦ = ዉሳቻ
መፋቂያ ጠፍጣፋ ቦርድ = ዋታ
መቀጥቀጫው የበሬ ትከሻ አጥንት = አጋት
የእንሰት ተክል = ተጋን (ጋርደን)
ትናንሽ የእንሰት ችግኞች = ሱማ
የሱማ ረድፍ = ማራ
የቅጠሉ ጀርባ አጥንት = ትምቦሽላ
የደረቀ ቀስላ = ኮባ
በጣም የደረቀ ኮባ (ማገዶ) = ቆቀሳ
ክሪም ኦፍ እንሰት = አጥሚት
ቆጮ = እኩሳ
የቆጮ ቂጣ = ጉንስ
በጣም ለስላሳ ስስ የቆጮ ቂጣ = አልበበጫት

.... የያለ ይቀላጥል !!
Last edited by Horus on 03 Sep 2021, 11:03, edited 2 times in total.

Tadiyalehu
Member
Posts: 675
Joined: 29 Jul 2014, 09:53

Re: ወንጪ (ምንጭ) ሃይቅ፣ ምድረ ገነት የዉበት ጥግ

Post by Tadiyalehu » 31 Aug 2021, 16:29

Horus
እኔ ጉራጌ ነኝ በእናቴ። የእናቴ አባት ሀገር ቡዒ ፣ ክርስትና የተነሣበት ደብሩም ምድረከብድ አቦ እንደሚባል ተነግሮኛል።
የእናቴ አባት እና ወንድሞቹ ከጣልያን ዘመን በፊት ወደ ኦሮሚያ መጥተው የእርሻ መሬት በመግዛት መኖር ከጀመሩ በኋላ ከቱለማው የገላን ኦሮሞ የአባቴ አባት ጋር ተገናኙ። ጉርብትናቸው በልጆቻቸው መጋባት ወደ ዝምድና ተቀየረ። እኔም በዚሁ መሠረት ከቱለማው ጀሃን ገላን እና ከጉራጌ ተወለድኩ።
ሁለቱም የምኮራባቸው ጨዋዎች ክርስቲያኖች ጠንካራ አርሷደሮች እና ጀግኖች ናቸው። እኔ የሁለቱም ስለሆንኩ የጉራጌንም የኦሮሞንም ሀገር ጠንቅቄ አውቃለሁ። ታሪኩንም እንደዝያዉ።
በዬት አባክ አቋርጠህና አጠጋግተህ ነው የቱለማን ወንጪ የጉራጌ ያደረግከው???

Horus
Senior Member+
Posts: 42789
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ወንጪ (ምንጭ) ሃይቅ፣ ምድረ ገነት የዉበት ጥግ

Post by Horus » 31 Aug 2021, 21:12

ታድያለሁ፣
ታዲያ ኩሩ ኦርቶዶሽ የገላንና ክስትኔ ድብልቅ ጨዋ ከሆንክ የታባክ የሚለውን የባለጌ ቃል ማን አስተማረህ? ለማንኛውም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ? ገላን የት አገር (አካባቢ) ነው አገርህ? ሁለተኛ፣ ወንጪ የሚለው ስም ምን ማለት እንደ ሆነ ታቃለህ? ሶስተኛ ፣ እናንተ ባገራችሁ እንሰት ተክላችሁ ቆጮ ነው ወይ የምትበሉት በባህላችሁ እዚያ ገላን አገራችሁ? ሰላም

Tadiyalehu
Member
Posts: 675
Joined: 29 Jul 2014, 09:53

Re: ወንጪ (ምንጭ) ሃይቅ፣ ምድረ ገነት የዉበት ጥግ

Post by Tadiyalehu » 01 Sep 2021, 02:42

Horus
ለስድቡ ይቅርታ! ይስተካከላል። ለጠየከኝ ጥያቄ ፦
ገላን ማለት ከቱለማ ጎሣዎች ታላቁ ሲሆን 6 ንዑስ ጎሣዎች አሉት። በዚሁ መሠረት ጀሃን ገላን ይባላል-ትርጉሙ ስድስቱ ገላኖች ማለት ነው። የኔ አያት የዘር ሀረግ ከ6ቱ ገላኖች የመጀመርያው ወይም ታላቁ #ኩራ ጃርሶ ይመዘዛል። በቅርቡ አዲስ አበባ "ለሚ - ኩራ" የሚባል አዲስ ክፍለከተማ ተመሥርቷል። (ቅድም አያቶቻችንን ለማሰብ!) የዚህ ክፍለከተማ ስያሜ የኤካውን ታላቅ "ለሚ" እና የገላኑን ታላቅ "ኩራ" በጋራ ለማሰብ ለሚ ኩራ ተባለ። ለሚ ኩራ ከኤካ aka የካ እና ቦሌ ክፍለከተሞች መንደሮች ተቀንሰው ስለተመሠረተ ነው ሁለቱን የቱለማ ንዑስ ጎሣዎች ለማሰብ ስማቸውን አጣምሮ መሠየም ያስፈለገው።
የገላን ነባር መኖርያ ከአሁኑ ማዕከላዊ አዲስ አበባ ይጀምርና በስተ ደቡብ እስከ አደኣ ምድር ቢሻኖፍቱ ወይም ቢሾፍቱ (aka ደብረዘይት ) ድረስ ይዘረጋል።
ይሁን እንጂ ሁለቱ አያቶቼ የተገናኙት የገላኑም የጉራጌውም ምድር ላይ ሣይሆን አርሲ ክፍለ ሀገር ነው። ሁለቱም አያቶቼ በተለያየ ምክንያት ነው ከጣልያን ወረራ በፊት ወደ አርሲ ክፍለሀገር የተጓዙት እና ከአሠላ በስተምዕራብ ቅርብ ርቀት ላይ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ደማ ሴራ ከምትባል የአርሲ ባላባት ላይ በገንዘባቸው ገዝተው ማረስ የጀመሩት። እስከ ደርግ መግብያ ድረስ የገላኑም የጉራጌውም አያቶቼ ቤተሰቦች እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ጋሻ ለም የእርሻ መሬት ነበራቸው። ዃላ ደርግ ሁለቱንም ቀምቶ በቤተሰብ ቁጥር ልክ አከፋፈላቸው እና እንደማንኛውም ሰው በቤተሰብ ቁጥር ከደርግ የተሰጣቸውን መሬት እያረሱ ኖሩ። መሬቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተወራረሰ አሁንም ድረስ አለ። እነኚህ ሁለት የቱለማ ገላን እና የጉራጌ ቤተሰቦች ጎረቤት ብቻ ሆነው ለዘመናት አልኖሩም። ልጆቻቸውም ተጋብተዋል። ከጉራጌ ቤተሰብ የተወለደችው እናቴ እና ከገላን ቤተሰብ የተወለደው አባቴ የተጋቡት እና እኔን ጨምሮ 8ልጆች የወለዱት በዚሁ interaction መሠረት ነው። አያቶቼ በሰፈሩበት የአርሲ አከባቢ ጠንካራ ገበሬ ብቻም አልነበሩም ፤ ለአከባቢው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መመሥረት ፣ ለወርሃዊ የጽዋ ማኅበር መመሥረት ወዘተ ምክንያት ነበሩ።
ሌላው እንሰትን በተመለከተ ለጠየከው ጥያቄ፤ በአርሲ ሠፋፊ እርሻዎች ላይ በስፋት የሚመረተው ስንዴ ፣ ጤፍ ፣ ገብስ ፣ ባቄላ ፣ አተር ወዘተ ነው እንጂ እንሰት ብዙም ኣይዘወተርም። (አያቶቼም እንደ አከባቢው በአከባቢው የተለመደውን አዝዕርት ብቻ ነበር የሚዘሩት)።
Last edited by Tadiyalehu on 01 Sep 2021, 15:51, edited 1 time in total.


Horus
Senior Member+
Posts: 42789
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ወንጪ (ምንጭ) ሃይቅ፣ ምድረ ገነት የዉበት ጥግ

Post by Horus » 01 Sep 2021, 17:12

ታዲያለሁ፣
ለመልስህ አመሰናለሁ፤ በአሁኑ ሰዓት ወደ ታሪክ ለመመለስ ጥሩ ግዜ አይደለም እንጂ ብዙ እንወያይ ነበር። የነገርከኝ ትክክል ነው ። አሰላ ብዙ ክስታኔዎች አሉ። እኔ በልጅነቴ አሰላ የጉራጌ አገር ይመስለኝ ነበር ። ለምን ካለክ በየበአሉ ከአሰላ የሚመጡ ዘመዶች ነበሩ ። የእኔ ዘርማንዘሮች ምደረ ከብዶች፣ ክስታኔዎች ናቸው ። ዛሬ ተበትነው ጢያም ዋጮም ኬላም አሉ። ስለ ገላን ሕዝብ እጅግ ጥንታዊ ግንድ ሌላ ግዜ እናንሳው ። ስለ አድአና አዳዲ አካባቢ ያልከም ትክክል ነው ። ኩራ ብቻ ሳይሆን ጉራ ገላን የሚባል አገርም አለ። ይህ አንተ ወደ ምስራቅና ደቡብ ምስራቅ አዲሳባ ነው ያለሀው። ወንጪ ያለው በወሊሶ፣ጨቦ፣ በቾ ምዕራብና ደቡብ መዕራብ ነው።

Tadiyalehu
Member
Posts: 675
Joined: 29 Jul 2014, 09:53

Re: ወንጪ (ምንጭ) ሃይቅ፣ ምድረ ገነት የዉበት ጥግ

Post by Tadiyalehu » 01 Sep 2021, 17:29

እሺ ወገኔ Horus! አመሠግናለሁ።
እንግዲህ አንተም ክስታኔ ከሆንክ የአያቴ ዘመድ ልትሆን ትችላለህ ። ወደፊት የአያታችንን የትውልድ ሀገር እና ክርስትና የተነሣበትን ደብር (ምድረከብድ አቦን) ለመጎብኘት ለእናታችን ቃል ገብተናል። ያኔ እንገናኝ ይሆናል።
ሠላም ሁንልኝ ወገኔ!

Horus
Senior Member+
Posts: 42789
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ወንጪ (ምንጭ) ሃይቅ፣ ምድረ ገነት የዉበት ጥግ

Post by Horus » 01 Sep 2021, 18:14

ታድያለሁ
በጣም ጥሩ፣ እናታችሁ በጣም ነው ሚደሰቱት! ምድረ ከብድ ማለት በክስታኔኛ ቅዱስ ምድር ወይም ሆሊ ላንድ ማለት ነው ። እዚህ የተቀበሩ ቅዱስ አቦ (ገብረ መንፈስ ቅዱስ) ግብጻዊ አባት ነበሩ ። ምድረ ከብድ አቦን፣ ዝቋላ አቦን፣ አዳዲ ማሪያን ያሰሩት በ1460 ዓ/ም ነበር ። ረጅም ረጅም ታሪክ ያለው ቦታ ነው ። ይህው ያለፈው መጋቢት አቦ በዓል!




Tadiyalehu
Member
Posts: 675
Joined: 29 Jul 2014, 09:53

Re: ወንጪ (ምንጭ) ሃይቅ፣ ምድረ ገነት የዉበት ጥግ

Post by Tadiyalehu » 01 Sep 2021, 18:38

አመሠግናለሁ ወገኔ Horus!
ሠላም ሁንልኝ ።

Horus
Senior Member+
Posts: 42789
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ወንጪ (ምንጭ) ሃይቅ፣ ምድረ ገነት የዉበት ጥግ

Post by Horus » 03 Sep 2021, 04:04

የቆጮ ቆሎ (ሮስትድ ቆጮ) = እርግፎን

Post Reply