Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
AbebeB
Member+
Posts: 7694
Joined: 15 Oct 2016, 10:31

አባይ ሚድያ ከቴዲ በኃላ ለመጀመርያ ጊዜ ከእውነት ጋር እየተገናኘ ነው፡፡ ቴዲ እያለ ብዙ የሰመረላቸው ነበር ግን አሁን ያ ርቆአቸው አለ፡፡

Post by AbebeB » 22 Aug 2021, 09:30

የአሜሪካ አሁናዊ ፍላጎት ግልጽ ነው፡፡ ኑር ጀባም በጣም ግልጽ አድርጎ ባይናገርም ጉዳዩን አግኝቶታል፡፡ በአብይ ላይ የአሜሪካ ጫና ግልጽ ምክንያት ይህ ነው፡፡ ቄሮ በሀገር ውስጥ ትግልና አሜሪካ (ህማማቶ) በዲፕሎሚሲው ረድተንህ ስልጣን ላይ እንድትመጣ አድርገንህ ግን ከአማራ ጋር ተባብረህ የሽግግሩን አቅጣጫ መጥለፍ አትችልም፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ እንዳትበተን ስልጣን ልቀቅ የሚል መልዕክት ነው፡፡ አሜሪካ ህወሀት ከስልጣን እንዲወገድ ከረዳች በኃላ እንደገና በዋና መፍትሔነት እንዲያዩ የተገደዱት ከዚህ አንጻር ነው፡፡