Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42785
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Abiy Ahmed Rising: The Battle For The Soul of Ethiopia

Post by Horus » 19 Aug 2021, 22:22

አንድ ሁለት ግዜ አቢይን የቱርክ አባት ከሚባለው ከማል አታቱርክ ጋር አመሳስዬዋለሁ ። ብዙ ግዜ ግን የኢትዮጵያ ታላቁ ንጉስ ምኒልክ ጋር ነው የማመሳስለው፣ አቢይ አህመድን። ለምን?

ከመስከረም 30 2014 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብዙ የፖለቲካ ለውጦች እናያለን።

በእኔ እምነት የኢትዮጵያ የውጭ ሁኔታ በእጅጉ ይለወጣል ፣ የውስጥ ፖሊቲካችንም ብዙ ይለወጣል ።

አንድ፣ አቢይ ሕጋዊ መንግስት ያቆማል፤

ሁለት፣ አሁን አገር ለማዳን ከመንግስት ጋር የቆመው ተፎካካሪም ሆነ ተቃዋሚ መሰረቱ በሰፋ የአንድነት መንግስት ስር ይሰባሰባል ። ለሚቀጥለው 5 አመት ኢትዮጵያ የብሄራዊ አንድነት፣ የሰላምና የልማት ግዜ ትፈልጋለች ። አቢይ ይህን የnational unity government ሳይውል ሳያድር ማቋቋም ይገባዋል፣

ሶስት፣ ያሜሪካና አውሮፓ ግፊት ይቀዘቅዛል ምክንያቱም አሁን ባሉበት ከገፉ ኢትዮጵያ ያላት ምርጫ አይደለም ከቱርክ፣ ከኢራን ጋር ትወዳጃለች፤ ምዕራብ የአፍሪካ ቀንድ አይደለም ከአፍሪካ ሊባረሩ ይችላሉ ።

አራር፣ ይህ የውጭ ግፊት መብረድ ሲጀምር አቢይ የውስጥ ሪፎርሞችን ተራ በተራ ለህዝቡ ማቅረብ አለበት፤ ምሳሌ የአገሪቱ ስርዓት ከፓርላማ ወደ ፕሬዚዳንት መለወጥ፣ ሕገ መንግስቱን፣ ፌዴራል እስቴቶች ባህሪ የመሳሰሉት፣

አምስት፣ አቢይ ሳይሽኮረመም የታላቁ ምኒልክን ፈለግ በመከተል ታልቅ ኢትዮጵያ፣ ጠንካራ የአፍሪካ አንድነት ሰርዓት የአውሮፓ አንድነትን የሚገዳደር ባለ አንድ ገበያና ባለ አንድ ገንዘብ አፍሪካን መምራት ይገባዋል።

ከቱርኩ ኤርዶሃን ጋር ያላቸው መመሳሰልና ቱርክና ኢትዮጵያ ያላቸው ጂኦፖለቲካዊ ተመሳሳነት ያስገርማል ። ስለዚህ አቢይ በግልጽ ፖፑሊስት ሕዝባዊ ኢትዮጵያዊ መንፈስና ግጽታ ያለው ፖለቲካ አውጆ ኢትዮጵያን አንድ የሆነች ዘመናዊ ጠንካራ አገር የማድረጉን ሚሽን በይፋ መቀበል አለበት !
Last edited by Horus on 19 Aug 2021, 23:06, edited 3 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42785
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Abiy Ahmed Rising: The Battle For The Soul of Ethiopia

Post by Horus » 19 Aug 2021, 22:56

የኢትዮጵያ ብሎክ
ሩሲያ
ቻይና
ቱርክ
ኢራን



Horus
Senior Member+
Posts: 42785
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Abiy Ahmed Rising: The Battle For The Soul of Ethiopia

Post by Horus » 19 Aug 2021, 23:12


Horus
Senior Member+
Posts: 42785
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Abiy Ahmed Rising: The Battle For The Soul of Ethiopia

Post by Horus » 19 Aug 2021, 23:23

የኢራን ድሮኖች፣ ይህ ለቅሻሻው ባንዳ ዎያኔ አይደለም ። ይህ ለሱዳን፣ ለግብጽ ነው !

Horus
Senior Member+
Posts: 42785
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Abiy Ahmed Rising: The Battle For The Soul of Ethiopia

Post by Horus » 19 Aug 2021, 23:59


Post Reply