Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 13068
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Shocking: የአማራ ሚድያ ኮርፖሬሽን የህንድ ፊልም መሥራት ጀመረ

Post by Thomas H » 18 Aug 2021, 22:02

ይሄ ትርክት ደንበኛ የህንድ ፊልም ይወጣዋል

በክምር ድንጋይ አንድ የአማራ ጀግና 11 የአሸባሪው ትህነግ ታጣቂዎችን ደመሰሰ።
ነገሩ እንዲህ ነው ፦
የአሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ታጣቂዎች በክምር ድንጋይ ከተማ ወደ አንድ ግለሰብ ቤት በመሄድ ለማጥቃትና ለመዝረፍ ተዘጋጁ። ታጣቂዎች ግለሰቡ ቤት ደረሱ።
ይህንን ቀድሞ የተረዳው ግለሰብም በጥበብና በብልሃት የመጡትን የአሸባሪውን ቡድን ታጣቂዎች አዘናጋቸው።
ሊያጠቁትና ሊዘርፉት እንደመጡ የተረዳው ይህ ግለሰብ ያለውን መሣሪያ በመጠቀም በቤቱ የተሰበሰቡትን 11 የአሸባሪውን ትህነግ ታጣቂዎች እንዳልሆኑ በማድረግ ጀግንነቱን አሳይቷል።
አሁን ላይም ይህ ጀግና ቀሪ የአሸባሪውን ቡድን አባላትን እያሳደደ ይገኛል።
ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ክብርንና ማንነትን ማስጠበቅ የሚቻለው ይህንን አይነት ቆራጥነት በጠላት በመፈጸም ነው።
የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ ቀለመወርቅ ምህረቴ እንደዚህ አይነት ቁርጠኝነት ካለ ጠላት በየትኛውም አካባቢ ለእንቅስቃሴ እንዳይመቸው ማድረግ ይቻላል ብለዋል፡፡
አሚኮ


ከዚህ በተጨማሪ ይሄ የአማራ ጀግና የተወረወረበትን ቦንብ ከአየር ላይ ቀልቦ መልሶ ወርውሮ ጁንታው ላይ ብዙ ጉዳት አድርሷል::

Thomas H
Senior Member
Posts: 13068
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Re: Shocking: የአማራ ሚድያ ኮርፖሬሽን የህንድ ፊልም መሥራት ጀመረ

Post by Thomas H » 18 Aug 2021, 22:42

የአማራ ቴሌቪዝንም ተመሳሳይ ትርክቱን የባንግላዴሽ ፊልም ሠርቶበታል

ከድል ዜናዎች ውስጥ፣ ትኩረታችንን የሳበው የክምር ድንጋዩ ጀግና ታሪክ ነው።
ክምር ድንጊያ ከተማ ውስጥ: 11 የጁንታው ወራሪ አባላት በግለሰቡ ቤት ገብተው፣ ሚስቱን ያለ ፍላጎቷ ምግብ ሰርታ እንድታበላቸው ያስገድዳሉ። ጀግናው ባሏም ምንም እንዳልተፈጠረ ሁኖ፣ "በይ ችግር የለውም ተነሽና ስሪላቸው" ብሏት፣ ከጓሮ እንጨት ሊያቀርብላት ይነሳል። ባልየው ወደ ጓሮ ዘወር ዘወር ብሎ ዙሪያውን ቃኘና፣ 11ዱ አሸባሪዎች ብቻቸውን መሆናቸው አረጋግጦ፣ የማገዶ እንጨቱን ይዞ ይመለሳል። ይሄን ተግባሩን የተመለከቱት ነፍሰ-በላዎች፣ ሰውየውን አምነውት ዘና ብለው ምግቡን መጠበቅ ይጀምራሉ።
ይሄኔ በመሃል ለሚስቱ እቃ ለማምጣት በሚመስል መልኩ፣ ወደ ጓዳው የገባው ጀግና፣ ምኝታ ቤቱ ተቀባብሎ የተቀመጠ ክላሹን ይዞ ተመልሶ፣ ለ11ዱም ሚገባቸውን ሰቷቸው፣ እሱም ሚስቱም ላይ ምንም ጉዳት ሳይደርስ ተርፈዋል።
ይሄ ጀግና 11ሙሉ ትጥቅ ማርኮ፣ ለዘር ማንዘሩም አስታጥቋል።
ይሄን ጀግና የአማራ ቴሌቭዥንም ትልቅ እውቅና እየሰጠው ይገኛል።

Post Reply