ደረቅ እንጀራ 11 ብር ፣ እንቁላል 7:50 ገባ። ለምግብ ዘይት መጠቀም የቅንጦት መገለጫ ሆነ። አንድ ዶላር ከመቶ ብር በምን አንሳለው አለ። በየሰፈሩ ሟች በዛ። ድንኳን ማፍረሱ ቀርቶ ፣ ማንሸራተት ወግ ሆነ። በአየር ፋንታ ስጋትን ስበን ፣ ብሶት መተንፈስ ጀመርን። በሰላም ወጥቶ መመለስ አንደኛ ዕጣ ሎተሪ የማግኘት ያህል ታኣምር ሆነብን።
ሱዳን እንኳን በአቅሟ ተዳፈረችን። ተከፋፍለን እጃችን ከፈጣሪ ይልቅ ወደ አሜሪካና ወደ ሩሲያ ዘረጋን። እሴቶቻችን ጠፉ። ቅርሶቻችን ፈራረሱ።
እርስ በእርሳችን ተናናቅን። መተማመን እንደ ስኳር ጠፋ። ነፍፍፍፍ ስደተኞች በሰላም ከሚኖሩባት ሳውዲ ለገፍ ተባረሩ። ከሀገር በህገወጥ መንገድ የወጡ ስደተኞችም ባህር ውስጥ ሰምጠው ሞቱ። ይሄም አልበቃ ሲለን ቢገባን ብሎ ፣ መጪውን ጨለማ ሊያመላክተን በጠራራ ቀን ፈጣሪም በጉም እንዳይንተያይ ጋረደን። ፀባችን የጨለማ ፣ ሲነጋ የምናፍርበት መሆኑን አመላከተን። አጥተነው የማናውቀው የሩጫ የበላይነታችን እያየነው ከእጃችን ወጣ። ለእርግማን ስናጨበጭብ ፣ እጆቻችንን ዘርግተን 'አሚን' ስንል ፣ የተባረክንበትን በሙሉ ተነጠቅን። ከጦርነቱ በኋላ መሆን ያለበት ቀርቶ ፣ ሊሆን የማይገባው በሙሉ ሆነ። ቴዲ አፍሮ እንኳን የክብር ዶክትሬት ተሰጠው
እና ይሄን ሁሉ እያየንም አይበቃንም ወይ ?
መጪው ጊዜያችን አያስፈራንም ወይ ?
Please wait, video is loading...