Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የአማራ ክልላዊ መንግስት ወደ ኦሮሚያ የሚያደርገውን መስፋፋት የኦሮሞ ወጣቶችና ምሁራን ተቃወሙ (Oromia Media Network)

Post by sarcasm » 19 Jul 2021, 16:50

የአማራ ክልላዊ መንግስት ወደ ኦሮሚያ የሚያደርገውን መስፋፋት የኦሮሞ ወጣቶችና ምሁራን ተቃወሙ።

የተቃውሞው መነሻ በምስራቅ ሸዋ ዞን ፋንታሌ ወረደ በኩል የኦሮሚያ መሬት ተወሮ በአማራ ክልል አስተዳደር ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ስር እንደሆነ ተደርጎ በአካባቢው ታፔላ በመቆሙ ነው።


በተለያዩ የአለም ሀገራትና በኦሮሚያና የሚገኙ የኦሮሞ ወጣቶችና ምሁራን የተቃውሞ ድምጻቸውን በማሰማት የመስፋፋትና የመሬት ወረራውን አውገዘዋል።
ለአብነት የህግ ባለሙያው ዶክተር ሄኖክ ጋቢሳ “የአማራ ሚሊሻ የኦሮሞን መሬት በጉልበት በመዝረፍ የአማራን ክልል እያስፋፋ ይገኛል ብሏል።

አብይ አህመድ እና ሽመልስ አብዲሳ፣ በኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ ስም የኦሮሞ ልጆች ያልተገባ መስዋእትነት እንዲከፍሉ እና የአማራ ክልል ርስቴ የሚለውን መሬት ለማስመለስ የሚያደርገውን ዘመቻ እንዲቀላቀሉ እያደረጉ ያሉትን ጥረት ተችቷል።

የኦሮሞን መሬት በመዝረፍ የአማራ ክልልን የማስፋፋት ዘመቻ እቅድ ተይዞለት እየተሰራ ያለ ፕሮጀክት መሆኑን የኦሮሞ ተወላጆች ይናገራሉ። ይህንን እቅድ ለማሳካትም የኦሮሞን መሬት ከመዝረፍ በተጨማሪ የኦሮሞን ማንነት ማጥፋት አንዱ የዘመቻው አካል ነው በማለት ይቃወማሉ።


በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የኦሮሞ ተወላጆች ይህንን ሀሳባቸውን ለማጠናከር በቅርቡ በአማራ ክልል “ኦሮሙማ ይውደም” በሚል ሰልፍ መወጣቱን እና በዚያው ቀን ከባንክ ጀምሮ በክልሉ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች ንብረት ላይ የደረሰውን ውድመት በማሳያነት ጠቅሰዋል።

ከኦሮሚያ ክልል ተወስዶ ወደ አማራ ክልል የተካተተው የኦሮሚያ መሬት ባስቸኳይ እንዲመለስ የኦሮሞ ወጣቶችና ምሁራን አሳስበዋል።



Please wait, video is loading...