==================================
በስሜን ኢትዮጵያ የሚደረገውን ጦርነት መቃወም የህይወተ ዘመነ Mission አድርግያለሁ:: ምክንያቱም በተደጋጋሚ እንደተናገርኩኝ በህይወት ዘመነ እነሆ ሶስት ዘግናኝ, አላስፈላጊ እና ኢፍትሀዊ ጦርነቶችን አይቻለሁ:: በእነዚህ ጦርነቶች በርካታ የክፍል ጎደኞቼን, ጉሮበቶቼን እና የእድሜ እኩዮች የሚሆኑኝን ወጣቶችን አጥቻለሁ::
ታዳያ ዛሬም አብይ አህመድ ከብር ሸለቆ ማስልጠኛ በአግባብ ስልጠና እንኳን ወስደው ያልጨረሱትን ወጣች "አስመርቅያለሁ" በማለት ለጦርነት ሊማግዳቸው ተነስቶአል:: ባለፉት ሳምንታት በትግራይ የነበረው ኃይል ሙሉ በሙሉ ሲመታ ዛሬ ሌሎችን ለማገዶ እያቀረበ ነው::በዚህ ማስልጠኛ ውስጥ ልጆች ያላችሁ, ዘመዶች የሆናችሁ, ጎሮበቶች የሆናችሁ, እነዚህን ልጆች ከሞት ተደጉ:: በተለይ ደግሞ የኦሮሞ ልጆች; ለሃምሳ አመት ልጆቻችንን ገብረናል; በማይመለከተን ጦርነት; አሁን በቃ:: ይህ አዙሪት ማቆም አለበት:: ለኦሮሚያ ልዩ ኃይል, ለኦሮሚያ ፖሊስ አባላት, በመከላከያ ስራዊት ውስጥ ላላቹ የኦሮሞ ተወላጆች በሙሉ; ከህዝባቹ ከኦሮሞ ህዝብ ጎን የምትቆሙበት ጊዜ አሁን ነው:: የትግራይ ጦርነት ሲጀመር ይህ ጦርነት አይመለከታችሁን ስል ነበር::ራሳችሁን የምታድኑበት የመጨረሻው እድል አሁን ነው::
ቄስ ተመስገን

Please wait, video is loading...