Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4617
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

ምርጥ ሙዝ አገራችን ላይ ማየት ካቆምን ከአምስት ወር በላይ ሆነን!ቡርትካን አታበቅልም?!የሚመለከተው አካል ምን እየሰራ ነው?green tea አለ እንዴ?coconut አገራችን ለምን አ

Post by Abaymado » 27 Jun 2021, 06:33

አገራችን ላይ ላለፉት አምስት ወራት ገበያ ላይ የነበረው ሙዝ የቀቸጨ: የማይጥም : የማይበስል :ሲያዩት የማያምር ነው:: ባለፈውም ዓመት እንዲህ ይሆን ነበር:: ምክንያቱ ግን ምን ይሆን?

ቡርቱካን ከበላሁ ብዙ ግዜ ሆኖኛል:: ቡርቱካን እስከንችራሹ ገበያ ላይ የለም:: አሁን ብቅ እያለ ቢሆንም ዋጋው በክሎ 80 ብር ነው:: ለዛውም ሎሚ ሎሚ የሚል::

ምንድነው ምክንያቱ? ለመሆኑ ይህን የሚከታተል የመንግስት አካልና ባለሙያ አለ?

አፍሪካ ውስጥ የሚበቅሉ በጣም አሪፍ እና ተወዳጅ አትክልቶች ለምን አገራችን ላይ እንዲበቅል አልተደረገም? ችግር አለብን እንዴ ? ለምሳሌ ለቸኮሌት የሚፈለገው cocoa፣

እንዲሁም coconut
በስታርችህነቱ ይዘቱ የሚታወቀው እና በምዕራብ አፍሪካ የሚታወቀው yam አገራችን ላይ የሉም:: ለምን ለምን?


በጣም ትልቁ ነገር green tea እኛ አገር ለመሆኑ አለ እንዴ ? ይህ የሻይ ዘር በጣም ለጤና አስፈላጊ መሆኑ ቢታወቅም አገራችን ላይ አይገኝም:: ለምን fermented/ቀይ ሻይ ከሆነው ሻይ ይህ ገበያ ላይ አይቀርብልንም:: አገራችን ችግር ላይ ያለች ይመስለኛል: