ኢትዮጵያ ይህን ሁሉ ችግርና ቀውስ የሚደርስባት ሕዝብ ስለሌላት አይደለም፣ መሬት ስለሌላት አይደለም፣ ዉሃ ስለሌላት አይደለም፣ እውቀት ስለሌላት አይደለም ። ኢትዮጵያ ይህን ሁሉ ስቃይ፣ ረሃብ፣ ጦርነት፣ ሁከት እና ውርደት የሚደርስባት መላ አሜሪካ፣ አውሮፓ እንደ ራሳቸው ሱቅ ሲያሻቸው ከፍተው ሲያሻቸው የሚዘጓት ባለቤት የሌላት የማንም መቀለጃ ስለሆነች ነው።
ይህም የሆነው የመሪዎችዋ እና የልሂቃኖችዋ ራስ ወዳድነትና ያለም ሃያላን ተምጽዋች ሙሰኛ ሆነው ለገንዘብ ሲሉ ሕዝባችንን በዘርና ሃይማኖት ስለ ከፋፈሉት ነው። ዛሬ አሜርካና አውሮፓ ቪዛ ከልክለናል፣ ገንዘብ አቁመናል፣ ጉቦ አቁመናል ብለው መነሳታቸው ለሞኞችና ፈሪዎች መጥፎ ነገር ነው ።
አበሻ ሁሉ አሜሪካን እንደ ኮኬይን ሱሰኛ ስለሆነ ያለ አሜሪካ አገር ሊኖር የማይችል ይመስለዋል ። ያለ አሜሪካ ብድርና ምጽዋት እድገት የሌለ ይመስለዋል ። እነዚህ ሁሉ ላለፈው 30 አመት ላሽከርነታቸው ክፍያ ኢትዮጵያ እየተበደረች እየለመነች ህዝቡ ግ ን ዉሃ የለው ፣ መንገድ የለው ፣ ሚበላው የለውም ።
ስለዚህ ያሜርካ ብድርና ምጽዋት ኢትዮጵያን ከፍ ማድረግ ሳይሆን እንዲያውም ሕዝባችንን በጎሳ ከፋፍሎ የጥላቻ፣ የጦርነት፣ የቀውስ ምድር ያደረገ ይህ የቅኝ ገዥዎች ገንዘብ ነው።
ዛሬ አሜሪካ ተነስቶ ይህን አልሰጥም፣ ይህን አላበድርም፣ ይህና አልመጸውትም ሲል ሆረስ እሰዬ ነው የሚለው! ለምን በሉኝ?
ኢትዮጵያ አሁን ሰርታ ትበላለች ! ኢትዮጵያ አሁን ከልመና ወደት ነጻ ትሆናለች ! ኢትዮጵያ አሁን ከራሷ ጋር ታርቃ፣ ከብራ ራሷን ትመግባለች !
ኢትዮጵያ አሁን ለምና ሳይሆን ሰርታ ትበላለች !!
ኢትዮጵያ አይበገሬ !!
ሲ አይ ኤ ሾሞ ሲ አይ ኤ ከሚያወርዳቸው መሪዎች ፈጣሪ አገራችንን ይጠብቅ !

