Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4773
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Horus አይነ ኩሉ እንዲነበብ ከጋበዘው ከ‘ዶፍተር‘ አፈወርቅ ገብረእየሱስ መጠሓፍ ስንቀነጭብ

Post by Meleket » 17 Apr 2021, 05:07

Meleket wrote:
16 Apr 2021, 09:28
Horus wrote:
13 Apr 2021, 19:02
. . .ካሻችሁ መለስ ብላችሁ የዶ/ር አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ አጤ ምኒልህ የሚለውን ለንባብ ተከልክሎ የነበረውን መጽሃፍ አንብቡ ። ዛሬም የኢትዮጵያ ካንሰር የትግሬ ክህደትና ካልቸር ነው።
. . . ኢትዮጵያን ለ50 አመት እንደ ነቀርሳ እየበላት ያለ ነገረ የባንዳነት፣ የኢትዮጵያ የመክዳት፣ የድብቅነትና የዉሸታምነት የትግሬ ካልቸር ነው። ከዚህ ሌላ ተሾመ ስዩም ምን አለ?
አፈወርቅ ገብረእየሱስ = መም ገብረኪዳን ደስታ = የዘርና የጥላቻ ቦለቲካ አራማጆች = የታላቋ ጦቢያ ነቀርሶች ብለናቸዋል ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች። :mrgreen:
Horus አይነ ኩሉ እንዲነበብ ከጋበዘው መጠሓፍ "ዳግማዊ ምኒልክ" በዘረኛው አፈወርቅ ገብረእየሱስ እይታ

"የሸዋ መኳንንት ሁሉም ተሁሉ ሁሉ ራስ ዳርጌ ራስ ጉበና እነደጃች ገርማሜ እንዋጋ ይዋጣልነ እናስገብራለን እንጂ ለትግሬ አንገብርም አሉ። ነገሩ በዚህ ተቈረጠ። አጤ ምኒልክ ከዚህ ወዲያ ከምስር ንጉሥ ጋር ተላላኩ። . . ." ገጽ 23 [ምስር ማለት ግብጥ መሆኗን ልብ ቢለናል!]

“አጤ ምኒልክ ከምስር መንግሥት ጋር በመላላካቸው ሰው ባላወቀው ነገር አማ እንጂ ላገራቸው ሰው ላጤ ዮሐንስ ትተው ለባዕድ እስላም ለምስር ጦር ለማገዝ አልነበረም።. . ." ገጽ 24

"ዳግማዊ ምኒልክ የዚያን ግዜ ጀምሮ ፈረሱ ከህንድ ባሕር ጀምሮ እስከ ሱዳን ድረስ እየጋጠ ጥማቱን ተነጩ ኣባይና ከቢቶሪኣ ባሕር እንዲአበርድ ከኤርትራ ባሕር እንዲዋኝ ያውቀው ነበረ።" ገጽ 30 :mrgreen: :mrgreen:

"የትግሬ ሰፈር አለ ምኒልክ ጐኑ አይቀናም ነበረ።" ገጽ 31

"የምቦቦ ጦርነት . . . የምኒልክ አሽከር የምኒልክ ቀኝ ክንድ ጉበና ኣባ ዳቂ መቸም ፈረሱ እንቅፋት አይመታው ልጓም ኣይገታው፡ በክንፍ እንጂ ባራት እግር የሚሄድ አይመስል ነበር፡ እንዲአው የጋላ ደም እየጠማው ግቤን ተሻግሮ ሌቃን መዛብሮ በወለጋ ሜዳ አፍንጫውን ነፍቶ እንደተቆጣ አንበሳ ዓይኑን እያጕረጠረጠ በግሩ እየደነፋ ወዲህና ወዲያ ሲፏልል የጎጃም ጦር ብቅ አለና እንቅፋት ሆነው። ገጽ 32

"አረርጌ፦ ያባ ዳኘው ፈረስ የጉበናን ፈረስ መንገድ መሪ አድርጎ . . . ከጠራና ከደብረ ብርሃን ከጅሩ በመለስ አንድ ክርስቲያን ትርው ብሎ አይደርስበት የነበረ ድሮ ሁሉን ሰጥ አድርጎ ገዛና እሴት በንቅብ ወርቅ ተሸክማ ተንጦጦ ወለጋ ተወለጋ ከፋ ሌት ተቀን ብትጓዝ ብትንከረተት ምንም አንዳይነካት አደረገ። ገጽ 41

"ደዳች ወልደ ገብርኤል እስከ ቦሰና ድረስ ጋለቡና ብዙ ጋላ ፈጁ።" ገጽ 42

"ኢቴጌ ጣይቱ የዚያን ጊዜ ገና ወይዘሮ ጣይቱ ይባሉ ነበር እንጦጦ ቀሩ። የዚያን ጊዜ አዲስ አበባ ገና ስሙ ያልታወቀ የቆማጣ መሰብሰቢአ ነበረ። አጤ ምኒልክ ሁለት ሶስት ጠማማ ሰቀላ መሳይ ብቻ አስቁመውበት ነበረ።" ገጽ 43

"ያረርጌ መያዝ የምስራቹ እንጦጦ በደረስ ጊዜ ድሉ መቸም የልደት ዕለት ነበረና እቴጌ ጣይቱ እንዲህ ብለው ገጠሙ፥-

የተጓዘው ሰንጋ የተነዳው ሽህር ለልደት ባይደርሥ
እስላም አርደው ዋሉ የሸዋው ንጉሥ።” ገጽ 44 [እዉን ክብርቷ እቴጌ እንዲህ ብለው ገጥመዋልን?] :mrgreen:

"ከጣይቱ ብጡል በቀር አንድ በምክር የሚያግዝ ተመኳንንቱ ሳይገኝ ባንድ ንጉሥ ልብ ይኈ ሁሉ ታስቦ ለመደረግ የሚችል አልነበረም። . . . ከመኳንንቱ ከራሱ እስከ ቢትወደዱ ከባላምባራሱ እስከ ሻለቃው ተወታደሩ እስከ ጋሻ ጃግሬው . . ለጌታው አንድ በምክር የሚአግዝ አልነበረም።" ገጽ 45

"በምንቸት እንደተጣደ ሁሉ ፍል ውሀ ሲባል የነበር የቆማጣ መደበር አንድ ገጠር በጣይቱ ብጡል ቃል እንዲህ ተቀድሶ አዲስ አበባ ተብሎ ፀሐይ ባየው ዓለም ይታወቅ ዘንድ ማን አስቦት ነበር።" ገጽ 46

"ያባ ዳኘው ፈረስ ተሸዋ ተነሥቶ በጭራው ወሎን እየነካ ባንድ ወገን አዳልን አረርጌን ባንድ ወገን አሩሲን ከፋን ባንድ ወገን ወለጋን ሻንቅላን ረገጠ። ከዚህ በኋላ ያባ ዳኘው ፈረስ ፈረስነቱን ንቆ አንበሳ መሆኑን ጨርሶ ወደደ። ይሄ የሰለሞን አንበሳ ድሮ ፊቱን ወደ ትግሬ ወደ ጐንደር ቀና ማድረግ ጀመረ። ለዚህ የውነተኛ አንበሳ ያረርጌ ሰንጋ የጋላ ድልብ የሸዋ ሽህር ሰለቸውና የትግሬን ያንበሳ ለምድ የለበሰ በሬ መስበር ወደደ።" ገጽ 47

"ድፍን ኢትዮጵያ በትግሬ ጥፍር ገብታ መቸም ተጨንቃለች ታለቅሳለች መከራዋን ታያለች። ብልሀቱ አይታወቅም ገና ከዚህ ሁሉ በፊት የሸዋው ምኒልክ በኢትዮጵያ ሰባት አመት ይነግሣል የሚሉት ንግር ነበረ። ሰባት ዓመት ይነግሣል ማለቱ ት ተሳስታ አለሥፍራዋ ገብታ ነው እንጂ ንግሩ ሰባ ዓመት ለማለት ይሆናል።" ገጽ 48

“ጐጃምን የመሰለ ደግ አገርም ሶስት ወር ሙሉ በትግሬ አንበጣ ተመደመደ።" ገጽ 52

"የትግሬ ወታደር በዚያ ጉረሮ በሚፍቅ ቋንቋው ኩሪ ኩሪ እያለ እርጉዝ አስወረዳት እምጫት ጡቷ ደረቀባት፡ ቄሱ ተቤተክሲአን ገበሬው ተዱሩ ነጋዴው ተመደበሩ ተሸሽጎ በትግሬ ወታደር አለቀሰ ተማለአል።" ገጽ 54

"እንዲህ ዮሐንስን የመሰለ ንጉሥ ከዚያው ወድቆ ቀረ የኢትዮጵያ ንጉሥ ያን ያህል ተገዛው አገር ለሶስት ክንድ መሬት ሳይበቃ ከደርቡሽ መሬት ወድቆ ቀረ። ያ የተቀደሰ ገላው ባረመኒ ጦር ተሰንጥቆ እረከሰ ያን የመሰለ ንጹህ ገላው በደም ተነክሮ ባፈር ተለውሶ መተማ ላይ ወድቆ ቀረ። . . . ያጤ ዮሐንስ ሞት ግን ባጤ ምኒልክ ብርታት ነው ኣንጂ በዚያ ደካማ ደርቡሽ ብርታት እንዳልሆነ ሁላችን እናውቃለን።" ገጽ 56

"የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የተቀደሰ ሬሳው በርኩስ እስላም እጅ ወድቆ መቃብር አጥቶ ሲቀር ምነው አለማዘነዎ። በዚኢህስ የውነቱን መናገር ነው የኢትዮጵያ ቅስም ተሰበረ። የትግረ አንበሳ በደርቡሽ ጦር ተወግቶ ለሶስት ክንድ ላገሩ መሬት ሳይበቃ ሞት አይቀርም በመጋቢት ፲፰፻፹፩ ዓመአ ምህረት መተማ ላይ ቀረ። ነፍሱን ይማር ነፍሱን ይማረው።" ገጽ 57