ይህን ጥያቄ ከዚህ ቀደም አንድ ሁለቴ አንስቼው ነበር ። ነገር ብዙ ኢትዮጵያዊያን ስለ አድዋ ጦርነትና ድል ሲጽፉ የማርች 1 ቀን ለምን እንደ ተመረጠ አያነሱም ። ይህን ቀን የወሰኑት አጼ ምኒልክ ወይም የርሳቸው ጦር አዛዦች አልነበሩም ። ይህችን ቀን የመረጡት ራሳቸው ጣሊያኖች ነበሩ።
ለምን?
በጣሊያን ታሪክ፣ በሮማዊያን ታሪክ፣ በሮማዊያን ኢምፓየር ማርች 1 ቀን ታላቅ ነገር ነበር ። የጁሊያን ቀን መቁጠሪያ ተብሎ የሚታወቀውና በጁለየስ ቄሳር የተመሰረተው የዘመን አቆጣጠር ዘመን የሚለወጥበት አዲስ አመት ቀን ማርች 1 ቀን ነበር ። ያውሮፓዊያን መጀመሪያ ወር የዛሬው ጃኑዋሪ ሳይሆን ማርች ነበር ።
ማርች በዚያን ዘመን ማርስ ይባል ነበር ። ማርስ ዛሬም የታወቀው የቀዩ ፕላኔት ስም ነው ። ግን ማርስ የሚለው ስም ፋይዳ የፕላኔት ስም መሆኑ አልነበረም ። በሮማዊያን የፔጋን ሃይማኖት አማልክት ከነበሩት እጅግ ሃያል ተብሎ ይታመንበት የነበረው የሮማዊያን የጦርነት አምላክ እሱ ማርስ ነበር ። አማልክት ማርስ እጅግ የተዋበ ቤተ መቅደስ ተገንብቶለት ብዙ ብዙ መስዋዕት ይቀርብለት ነበር፣ ልክ እንደ ዛሬ ስለት መግባት እና ስለት ማድረስ ማለት ነው።
ስለሆነም ማንኛውም የሮማ ቄሳርም ሆነ የጦር አዛዥ ወደ ጦር ከመዝመቱ በፊት ለጦር አምላክ ማርስ መስዋዕት አርዶ፣ ደም አፍሶ ነበር ዉጊያ የሚሂደው ። ይህ ነበር በአድዋ የዉጊያ ዋዜማ የነበረው የጣሊያን ጦር መሪዎች ህሳቤና እምነት ። ማለትም ልክ እንደ ሮማዊያን ጦር ዘማቾች ነበር የአማልክት ማርስ እንዲቀናቸው ቶርነቱን በማርች 1 1896 እንዲሆን የወሰኑት ።
እርግጥ እነብልሁ ምኒልክ፣ እነአባ መላው ሃብቴ ይህን የጣሊያኖች ቅድመ እምነት ይውቁት እንደ ነበር በታሪክ ሲጠቀስ አይታይም ።
እዛሬ ላይ ሆነን ይህን ታሪካዊ ግዙፍ ኤፒክ ድራማ ሳናስበው ይገርማል !! ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈረሰኛውና ጦረኛው ታቦት ነው ክምኒልክና ጣይቱ ጋር አድዋ ዘምቶ ድል አድርጎ የተመለሰው !! ማለትም በምሳሌና በሜታፎር ስናየው ያ ታላቅ፣ ያ ያፍሪካ ታሪክ የለወጠው ግጥሚያና ፍልሚያ የተደረገው በቅዱስ ጎርጊስ ፈረሰኛውና በሮማዊያኑ ጦር አምላክ ማርስ መካከል ነበር !!!
በነገራችን ላይ የማርስ ትጥቅም ጦርና ጋሻ ነው ፤ የቅዱስ ጎርጊስም ትጥቅ ፈረሰ ጦርና ጋሻ ነው !!!
ኢትዮጵያ የእግዚአብሄር አገር ነች የሚባለው ለዚህ ነው። እንኳን በዚህ ድል የሚኖር ትውልድ ለመሆን አበቃን !!!
ኢትዮጵያ የጥሩር ዘር ነጻነት ምልክት ለዘላለም ትኑር
https://en.wikipedia.org/wiki/Mars_(mythology)