Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ኮሎኔል ይርጋለም ፍቃዱ እና ሌተናል ኮሎኔል ተወልደ ብርሃን ሊሸሹ ሲሉ አፋር ላይ መያዛቸውን መርመሪ ፖሊስ ለችሎት ገለፀ!

Post by Ejersa » 21 Dec 2020, 09:23

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አራዳ ምድብ 2ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት እነዚህ ተጠርጣሪዎችን ጨምሮ 10 የመከላከያ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ተመድበው ሲሰሩ የነበሩ መኮንኖችን ጉዳይ ተመልክቷል።

ተጠርጣሪዎቹ ኮሎኔል ሃረጎት በርሄ ፣ ሌተናል ኮሎኔል ሙሉ አለሙ ፣ ብርጋዴል ጄኔራል ይልማ ከበደ ፣ ኮሎኔል በረከት ወልደአብየዝጊ ፣ መቶአለቃ ገብረጎርጊስ ፣ ሌቴናል ኮሎኔል ግደይ ገብረእየሱስ ፣ ሻለቃ ሃሳቡ መሃመድ ፣ መቶአለቃ ጸሃየ ሃይሉ ፣ ኮሎኔል ይርጋለም ፍቃዱ እና ሌተናል ኮሎኔል ተወልደ ብርሃነ ናቸው።

ተጠርጣሪዎቹ በመከላከያ ሰራዊት በስራ ላይ ሆነው ለወንጀል መፈጸም የስራ ክፍፍል አድርገው ሲሰሩ እንደነበር በማስረጃ አረጋግጫለው ሲል መርመሪ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ የሰራውን ስራ ለችሎት ገልጿል።

ውጭ ሃገር ላሉ አካላት ሃሰተኛ መረጃ ሲያቀብሉ ነበር ያለው መርማሪ ፖሊስ በወቅቱም በመከላከያ ሰራዊት ችግር እንዲስፋፋ ሲያባብሱ ነበር ብሏል ፖሊስ ለችሎቱ።

በዚህ ተሳትፏቸውም በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ሲሰሩ እንደነበር ባገኘሁት ማስረጃ አረጋግጫለው ሲል ተናግሯል።

ተጠርጣሪዎቹ በተለያዩ ቦታዎች በስራ ላይ እንደነበሩ ገልጸው ፤ የወንጀል ተሳትፏችን ሊገለጽ ይገባል ፣ ከወንጀሉ ጋር ገንኙነት የለንም ሲሉ በነጻ አለያም በዋስ እንዲወጡ ችሎቱን ጠይቀዋል።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ ኮሎኔል ይርጋለም ፍቃዱ እና ሌተናል ኮሎኔል ተወልደ ብርሃን ሊሸሹ ሲሉ አፋር ላይ መያዛቸውን ለችሎት ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ቡድኖቻቸው ግብረ አበሮቻቸው ስላሉ ከዚህ ቢወጡ ጉዳት ሊያደርሱና ሊሸሹም ይችላሉ ሲል ዋስትናውን ተቃውሞ ተከራክሯል።

የሁለቱን ክርክር ያዳመጠው ችሎቱ የእያንዳንዳቸውን ተሳትፎ ከመዝገቡ ተመልክቶ ትዛዝ ለመስጠት ለታህሳስ 15 ቀን 2013 አ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ሲል ፋና ዘግቧል።

Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

Re: ኮሎኔል ይርጋለም ፍቃዱ እና ሌተናል ኮሎኔል ተወልደ ብርሃን ሊሸሹ ሲሉ አፋር ላይ መያዛቸውን መርመሪ ፖሊስ ለችሎት ገለፀ!

Post by Hameddibewoyane » 21 Dec 2020, 10:58

:oops: :oops: :oops: :oops: :oops: :oops:
quote=Ejersa post_id=1136339 time=1608557022 user_id=52247]
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አራዳ ምድብ 2ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት እነዚህ ተጠርጣሪዎችን ጨምሮ 10 የመከላከያ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ተመድበው ሲሰሩ የነበሩ መኮንኖችን ጉዳይ ተመልክቷል።

ተጠርጣሪዎቹ ኮሎኔል ሃረጎት በርሄ ፣ ሌተናል ኮሎኔል ሙሉ አለሙ ፣ ብርጋዴል ጄኔራል ይልማ ከበደ ፣ ኮሎኔል በረከት ወልደአብየዝጊ ፣ መቶአለቃ ገብረጎርጊስ ፣ ሌቴናል ኮሎኔል ግደይ ገብረእየሱስ ፣ ሻለቃ ሃሳቡ መሃመድ ፣ መቶአለቃ ጸሃየ ሃይሉ ፣ ኮሎኔል ይርጋለም ፍቃዱ እና ሌተናል ኮሎኔል ተወልደ ብርሃነ ናቸው።

ተጠርጣሪዎቹ በመከላከያ ሰራዊት በስራ ላይ ሆነው ለወንጀል መፈጸም የስራ ክፍፍል አድርገው ሲሰሩ እንደነበር በማስረጃ አረጋግጫለው ሲል መርመሪ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ የሰራውን ስራ ለችሎት ገልጿል።

ውጭ ሃገር ላሉ አካላት ሃሰተኛ መረጃ ሲያቀብሉ ነበር ያለው መርማሪ ፖሊስ በወቅቱም በመከላከያ ሰራዊት ችግር እንዲስፋፋ ሲያባብሱ ነበር ብሏል ፖሊስ ለችሎቱ።

በዚህ ተሳትፏቸውም በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ሲሰሩ እንደነበር ባገኘሁት ማስረጃ አረጋግጫለው ሲል ተናግሯል።

ተጠርጣሪዎቹ በተለያዩ ቦታዎች በስራ ላይ እንደነበሩ ገልጸው ፤ የወንጀል ተሳትፏችን ሊገለጽ ይገባል ፣ ከወንጀሉ ጋር ገንኙነት የለንም ሲሉ በነጻ አለያም በዋስ እንዲወጡ ችሎቱን ጠይቀዋል።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ ኮሎኔል ይርጋለም ፍቃዱ እና ሌተናል ኮሎኔል ተወልደ ብርሃን ሊሸሹ ሲሉ አፋር ላይ መያዛቸውን ለችሎት ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ቡድኖቻቸው ግብረ አበሮቻቸው ስላሉ ከዚህ ቢወጡ ጉዳት ሊያደርሱና ሊሸሹም ይችላሉ ሲል ዋስትናውን ተቃውሞ ተከራክሯል።

የሁለቱን ክርክር ያዳመጠው ችሎቱ የእያንዳንዳቸውን ተሳትፎ ከመዝገቡ ተመልክቶ ትዛዝ ለመስጠት ለታህሳስ 15 ቀን 2013 አ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ሲል ፋና ዘግቧል።
[/quote]

Post Reply