የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ልዩ ኃይል የአማራ ሚኒሻ ራያ አላማጣን ከከሃዲው የትህነግ ቡድን ለማስለቀቅ በነበረው ውጊያ ከተያዙ ቦታዎች ባሻገር ቁጥራቸው በርከት ያለ የትህነግ ልዩ ኃይልና ሚሊሻዎች ሙትና ቁስለኛ ሲሆኑ በሌላ በኩል እድል የቀናው የትህነግ ሰራዊት እግሬ አውጭኝ ብሎ እየፈረጠጠ ነው። ቁጥሩ ቀላል የማይባል የትህነግ ሰራዊት ደግሞ ለመከላከያ እና ለአማራ ልዩ ኃይል እጃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።
በስፍራው ያገኘናቸው የራያ ዋጃ ጥሙጋ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለፁት ከዚህ ቀደም ጨቋኙና ጨፍጫፊው የትህነግ ቡድን ከፍተኛ ጭቆና ሲደርስባቸው እንደነበር ገልፀው አሁን ላይ የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፖሊስ እና የሚሊሻ ኃይሉ ባንዳውን ቡድን አባሮ እኛን ነፃ አውጥተውናል ብለዋል።
አሁን ላይ የራያ የዋጃ ጥሙጋ ከተማ ነዋሪዎች ከከሃዲው እና ጨፍጫፊው የትህነግ ቡድን ነፃ በመውጣታቸው በራያ ባህላዊ ጭፈራ ደስታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።
ራያ አላማጣ መሆኒ ማይጨው እያለ ይቀጥላል!!!!
ድል ለመከላከያ









