ለምን በሉ?
አንድ፣ አቢይ መዘጋጀት ያለበትን የጦርነት ኢንፍራ እስትራክቸር ሁሉ በትግዕስት ጊዜ ወስዶ ስርቷል፣ በጂኦፖለቲካም ሆነ ሌላ ።
ሁለት፣ ትህነጎች መስራት የሚችሉትን ያህል ስህተቶች ሁሉ እንዲሰሩ ደካማ በመምሰል አሳስቷችዋል ። ይህም በመሆኑ ዛሬ ፍጹም የተነጠሉ፣ የተወገዙ ሃይል ሆነዋል ።
ሶስት፣ ጦርነት ያንድ አገር ጠቅላላ ሃይልና ትብብር መለኪያ ስለሆነ ያንን ስርቷል ።
አራት፣ ሕጋዊነትና የሞራል የበላይነት ይዟል ።
አምስት፣ ልክ ማንኛውም ፕሮጅችት ማኔጅ ለማድርግ የሚጠቀመውን የፕሮጅችት አፈጻጸም ስልት ስራ ላይ እያዋለ ነው ። ለምሳሌ ...
አንድ ተግባር ቁርጥ ቀን ተወስኖለት በዚያ ቀን የሚያስጨርስ ፕሮጅችት ማኔጀር ነው ። ለጄኒራሎቹ የሰጠው መመሪያ ያ ነው ።
ሌላው ቀርቶ ትህነግ ራሱ ይህን ቁርጥ የግዜ ወሰን እንዲከትል አጣብቂኝ ውስጥ ጥሎታል ። ትህነግን ሚደግፉት የውጭ ሃይሎች ሁሉ የዚህ የግዜ ወሰን መከተል አለባቸው ።
ደሞ ይህን መስል ቁርጥ የግዜ ወሰን በጠላት ላይ ግዙፍ የሳይኮሎጂ ተጽዕኖ ያደርጋል ። ስይኮሎጂያዊ ፕሬሸር ትልቅ የውጊያ ስልት ነው ።
ይህ ብቻ ሳይሆን በሜንታል እና ፕርስናሊቲ ፕሮፋይል በማድረግ አቢይ ትህነግን ሙሉ በሙሉ ሸውዶዋቸዋል ። አቢይ በስለላ ተቋም ውስጥ በነበረ ግዜ የሚጠቀሙበት የሱ ፐርሰናሊቲ አሁን ከሚያድርገው የተለየና እነሱን ፈጽሞ ያሳሳተ ጉዳይ ነው። የዚህን ምስጢር እዚህ አልገልጸውም ።
በሚያስገርም ምንገድ አቢይ ያሉትን ጠንካራ ፕርሰናሊቲና ደካማ ፐርሰናሊቲ በደንብ አውቆ ጠላት ለደካማ ፐርሰናሊቲው እርምጃ እንደ ሚወስዱበት አውቆ ያንን 100% በተቃራኔው ቢሄቭ በማድረግ ሳይዋጋ እያሸነፋቸው ነው ።
ማለትም አቢይ ራሱን የሚያውቅ ግለሰብ ነው ። የሚንቁት ሁሉ ግዙፍ ሽንፈት ይደርስባቸዋል ። ይህን ምስጢር እዚህ ለጠላት የሚዘረገፍ አይደለም ።