ስለ መራራ ጉዲና በወሬ ወሬ የሰማሁት ነው!
መራራ ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ እንዲያወያይ አሜሪካ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተጋብዞ ይመጣል:: ሆቴል እንዳያርፍ ተብሎ የኦሮሞ ተወላጅ ከሆነ ኢትዮጵያዊና ቤተሰብ ጋ እንዲያርፍ ይደረጋል::
መራራ አሜሪካ መግባቱን የሰሙ ኦነጋውያን ለመራራ መልእክት ላኩበት:: "ዛሬ ማታ የራት ግብዣና ላንተም አንድ ሁለት ሺ ዶላር የኪስ ገንዘብ ተዘጋጅቷል እና እንዳትቀር"::
መራራም ለአስተናጋጅ ቤተሰቡ አንድም ነገር ሳይናገር ወቶ ከሌሊቱ 4 ሰአት (10 ሰእት ባበሻ) ተመልሶ መጣ::