Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

አማራ በተገደለ ቁጥር ሙሾ ማውረድ ወያኔ በቀጥታ የሚፈልገውን ነገር ማድረግ ነው!

Post by Ejersa » 23 Oct 2020, 22:05

Please wait, video is loading...

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: አማራ በተገደለ ቁጥር ሙሾ ማውረድ ወያኔ በቀጥታ የሚፈልገውን ነገር ማድረግ ነው!

Post by TGAA » 23 Oct 2020, 22:50

ስዩም ወያኔን እንዴ ሌሊት ጅብ ማስፍራረያ እያደረገ አማራን ሞትን ፤ መተራድን ፤ መስደድን ፤ በሀገሩ ብይተዋር መሆኑን እሰየው ብሎ መቀበል አለበት እያለ ሲያወራ መስማት ፤ የሚያንገሸግሽ ቀልድ ነው፡፡ ዬሄ ኦሮአማራ የሰማይ ቤት ላም የጠቀመው ነገር ቢኖር ሞጋሳ እንደፈልገ በኢትዮጵያ ላይ እንዲፈነጭ ፤ አማራው በሃገር ላይ ተሸማቆ እንዲኖር ነው፡ ስለዚህ ስዩም አዲስ አባባ ቁጭ ብሎ በአብይ ጓደኞች ዶክመት እየቀረበለት የነርሱን ፖለቲካ ስለሰራ እራሱን ከእነርሱ እኩል እያየ ሌላውን ሊያውናብድ ይሞክራል ፤ በወኔ፡፡ በዚህ አመት ብቻ ከ1000 በላይ አማራ በብሄራቸው ተገድለዋል እሁንም እየተገደሉ ነው። እነአብይ አማርውን በየቦታው እያስጨረሱ እነርሱ ግን ህጉን ከስሩ እየቀየሩ የበለጠ እያሽመደመዱት ነው፤ ከመውደቁ በፊት ተንገዳግዶ ከለተነስ ከወደቁ በኋላ መላላጥ የሚለውን የሚያመጥው፤ እንደ ስዩም አይነቶቹ ለአማራው የበለጠ ሞት እንጂ ምንም አያመጡለትም ፤ መሞት ካለ ገድሎ ለመሞት መቁረጥ ያስፈልጋል ፤ ማንኛው ብሄረሰብ ይህንን ያህል ሰው ቢገደል ኖሮ አገሪቷ ትታመስ ነበር፡ የነስዩም አይነቶቹ የዶር ማታ ሰበካ መጽየፍ ያለብን ወራዳ ፖለቲካ ነው፡ ስዩም የአማራውን ሞት ያቃልላል ፤ አብይ ፤ እነጀዋር ያናንቃሉ ፤ አማራው ይህንን ያህል ለመኖር ወኔ ያጣበት ምክንያት እንደ ስዩም እና እንደ ኢዜአ ፤አዲፖ የአማራን ህይወት ስለሚያናንቁ ነው ፡፡ ስዩም የሆነ እራሱን የሚይስቅውሰው ሀሺሽ ይወስድ እንድሆነ ቢያቆም ይሻለዋል፡ ምክሩ ሙቱ ፤ እራሳችሁን አትከላከሉ ፤ ዝም ብላቸሁ ለአብይ አጫፍሩ ሆኖል ፤ ይህ ጤነኛ አእምሮ አይመስለም ፡፡

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: አማራ በተገደለ ቁጥር ሙሾ ማውረድ ወያኔ በቀጥታ የሚፈልገውን ነገር ማድረግ ነው!

Post by kibramlak » 24 Oct 2020, 05:31

አብይ እንደሁ በፓርክ ስም ያላግጥብናል፣ አንተስ ምን ትላለህ? ምን ሶሉዩሽን አለህ?

Ejersa wrote:
23 Oct 2020, 22:05
Please wait, video is loading...

Wedi
Member+
Posts: 8601
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: አማራ በተገደለ ቁጥር ሙሾ ማውረድ ወያኔ በቀጥታ የሚፈልገውን ነገር ማድረግ ነው!

Post by Wedi » 24 Oct 2020, 06:21

ይድረስ ለካድሬው !
(አሌክስ አብርሃም)

ካድርየ…. እየውልህ እንዴት መሰለህ …እኔ ልክ እንደአንተ አገሬን እወዳለሁ ! አሳድጋኛለች ፣አስተምራኛለች ፣ምናልባትም ከአንተ የተሻለ በተለያዩ ቦታዎች ላይ አገልግያታለሁ! በሶሻል ሚዲያውም ቢሆን ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት እዚህ ከምታያቸው ብዙ አክቲቪስቶች እኩል ተሟግቻለሁ !እንደውም በስም ልዘረዝርህ የምችላቸው አንዳንዶቹ መፃፍ ሁሉ የተለማመዱትና የጀመሩት ለእኔ ኮሜንት በመፃፍ ነው ! ፅሁፎቸን ከግል ጋዜጦች እስከኢሳት እየተቀባበሉ መንግስትን ተችተውበታል! ሁለት የግጥም መፅሐፎቸን ካነበብክ ስለፆታዊ ፍቅር ከፃፍኩት ይልቅ ስለአገር የፃፍኩት በዝቶ ታገኘዋለህ ! ስርዓቱን የሞገትኩባቸው ፅሁፎች አንድ ሁለት ሳይሆኑ መዓት ዛሬም እዚሁ ታገኛቸዋለህ ! ካድሪያዊ አዕምሮህ ቢሮ ውስጥ ላለ ባዶ ወንበር እንድትሰግድ እንጅ በሐሳብ ለሚሟገት ፀሐፊ ክብር እንዲኖርህ አይፈቅድልህምና ሰደብከኝ አጣጣልከኝ ብየ አላዝንብህም ! ሙያህ እንኳን ስድብ መግደልን እንደሚያካትት ግልፅኮ ነው ! በደርግ ስርዓት እንዲህ እንዳንተ ይውደም ብለው በቃል የጀመሩ ናቸው በጥይት ወደማውደም የተሸጋገሩት ! እዚህ ድረስ እረደሃለሁ !

ቢሆንም አሁን ያለውን እውነት በየአዳራሹ ተሰብከህ ጆሮህንም አይንህንም ከደፈነው ጫጫታ በተለየ እንዲህ ተረዳው …ቀበሌ ለቀበሌ መፎክር ስታሰማ … በየሰፈሩ ማንንም አዲስ ባለስልጣን ሽ ዓመት ግዛን ስትል ውለህ ወደቤትህ ምሳ ልትበላ ተመለስክ እንበል …አሁን እናትህን ሚስትህን አስብ ምርጥ ምሳ ተሰርቶ ፣ቡናው በጀበና የከሰል ምድጃ ላይ ተጥዶ ቤቱ ደምቆ ልጅህ እየቦረቀ ገና ከሩቅ በፈገግታ ሲቀበልህ አይንህ ላይ ውል እያለ ፣ እንደውም በአበል ባገኘሃት ብር መንገድህ ላይ ካለች ዳቦ ቤት ዳቦ ገዝተህለት እቤትህ ደረስክ …ምን አጋጠመህ …ሰፈሩ በለቅሶ ተደበላልቆ የልጅህና ሚስትህ ሬሳ በደም ተጨማልቆ በር ላይ ነጭ ጨርቅ ጣል ተደርጎበት ጠበቀህ …ራቅ ብሎ ደግሞ የእናትህም !

የሰፈሩ ሰው ግማሹ አናቱ በገጀራና መፍለጫ ተጠርምሶ የተረፈ ግማሹ በተዓምር ከጭፍጨፋ ያመለጠ …ልክ እንደፊልም ሚስትና ልጅህ በወጠምሻ ዱርየዎች ማሩን እያሉ እየጮሁ የአንተን ስም አድነን እያሉ እየጠሩ በጭካኔ በመንጋ ተጨፍጭፈው እንደተገደሉ ተረኩልህ ! የተገደሉበት ምክንያት ወይ ሐይማኖታቸው አልያም ብሔራቸው መሆኑንም! ! እንዲህ በሀዘን ተንገብግበህ ሬሳህንን ታቅፈህ ቁጭ እንዳልክ ማታ በዜና ‹‹ ጉዳዩን አንዳንድ አካላት እንደሚያራግቡት ሳይሆን በጎረቤቶች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሰዎች ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል ›› ብሎ የምትወደው የካድሬ ሚዲያ ዘገበ! የሶስት ዓመት ልጅህና ሰው ቀና ብላ የማታይ ሚስትህ አንድ ግሩፕ ... ማንነታቸው የተደበቀላቸው ገዳዮች ሌላ ግሩፕ ሁነው ሲፋለሙ በመካከል የተፈጠረ ‹‹ግጭት›› ነው ተባልክ !

እናም ሌሎች ካድሬዎች በሶሻል ሚዲያው ‹‹አታካብዱ …ሰላም ነው …የሁለት ሰው ሞት ምን ይገርማል ወያኔ ስንት ሰው ስትጨፈጭፍ የት ነበራችሁ ?…ምድረ ነፍጠኛ አያቶችህ ስንት ሰው ሲጨፈጭፉ ገና ምን አይተህ ?…›› የሚል ማላገጥ አየህ ….ጭራሽ ጠቅላይ ሚንስትሩ ፓርላማ ላይ … ወደፊት አገራችን እንዴት ገነት እንደምትሆን …በፌስቡክ ፔጃቸውም ግንፍል ማለት እንደሌለብህ ፣የሸክላ ድስት መሆን እንዳለብህ በታሪክና ምሳሌ አስደግፈው ነገሩህ ! በቀጣዩ ቀን ደግሞ ከዛ አካባቢ ከኖርክበት ካፈረሃው ንብረት በነዛው ወጠምሻዎች ተባረህ ወደማታውቀው ሰፈር በጉልምስናህ ተሰደህ ለማኝ ወላ ጥገኛ ሆንክ! በአንድ ጊዜ በራስህ አገር ላይ ሐዘንተኛ ፣ ጥገኛ እና ካስፈለገም የነገሩ ቀስቃሽ ተብለህ እስረኛ ጭምር ልትሆን ትችላለህ!

ካድርየ! ስርዓት ያልፋል መሪ ይቀየራል ....አገር ልታድግም ላታድግም ትችላለች …አንተ ውስጥ ግን የአንተ ብቻ የሆነ መቸም በምንም የማይመለስ ነገር ሙቷል ! ጩኸትህ ለቅሶህ የአገር ማፍረስ ሰላም ማደፍረስ እንዳይባል ፈርተህ ብቻህን የምትንገበገብበት ታሪክ ትቶልህ አልፏል ! ይሄ ልብ ወለድ ሳይሆን አገራችን ላይ የብዙ ሺዎች ታሪክ እንዲህ ነው! …በዚች ደይቃ ...አሁን... ለእኔ ምላሽ ልትሰጥ ጥሬ ስጋ በሚጥሚጣ መብላትህ አቁመህ ዘመናዊ ስልክህ ላይ ልትፅፍ እጅህን ስትጠራርግ … ብዙዎች በዚህ ቁስል በዚህ ሐዘን ውስጥ ናቸው ! የሚያድናቸው ያጡ ብዙ ቤተሰቦች ህፃናት ልጆቻቸውን እንዳቀፉ ከአሁን አሁን መጥተው ጨረሱን በሚል ስጋት ውስት ናቸው ! አሁን አንተ ይችን እያነበብክ ስጋት ውስጥ ያሉ ብዙ ሽዎች ናቸው ! ድረሱልን ብለው የሚጠሩበት ስልክ ፣ ገዳያቸውን የሚለዩበት መብራት ፣የሚሸሹበት መኪና መንገድ በሌለበት ገጠር ጫካ ወገኖችህ በጭንቀት ላይ ናቸው ! አንተ ግን በብዙ ሺህ ውጭ አገር በሰለጠነ ጋርድ ታጅቦ ስራውን የሚሰራው ለዚሁ ቦታው ላይ የተቀመጠውን ሰውየ ለምን ወቀሳችሁት ሞራሉ ይነካልኮ …ለምን ሰው አድን አላችሁት ብለህ እያለቀስክ ነው ! አውቃለሁ ነፍስህ በሚወረወርላት ምስጋናና ሳንቲም ስለታወረች አሁን ይህን እየነገርኩህ እንኳን ምን እያለ ነው ከማለት ይልቅ ማን ስንት እየከፈለው ነው ብለህ እንደምታስብ አውቃለሁ !ካድርየ ቢከፈለኝ ኑሮ ከኔ ቀድመህ ከፋየ እግር ስር የምትደው አንተ ነበርክ !

አገሩን የሚጠላ የለም ! ግን የአንተ የአዞ እንባ የአገር ተስፋ አንድነትና የህዝቦች የነገ እጣን የሚያበሰብስ የሚያሟሟ አሲድ ነው …የእነዛ ንፁሃን ከደም ጋር የተቀላቀለ እንባ ግን ምንም የማያመጣ መስሎ ቀስ በቀስ አገር የምታክል ትልቅ አለትን የሚሰነጥቅ የመርገምት ጠብታ ነው ! እነሱ አይደሉም አገር የሚያፈርሱት እንባና ደማቸው ነው !….እያልን ያለነው አገር ትፍረስ ሳይሆን ያ እንባና ደም ይታበስ ይቁም ነው !!

መንግስት ካልቻለ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ እርዳታ ይቅ ነው ! አለሁ እያለ ህዝብ አያስጨርስ ነው! እንዳለመታደል ሁኖ ለዚህ ጥያቄ ትክክለኛው ሰው አገሪቱን በበላይነት የሚመሩት አንተ የምትወዳቸው፣ የምትንሰፈሰፍላቸው ጠ/ሚንስትሩ ናቸው ! ስለረበሽንብህ ይቅርታ ! ግን አንተም በስልጣንና በካድሬነት ለመክረም ሚስኪኑም ህዝብ በሕይዎት ለመክረም ያለን አማራጭ እሳቸው ላይ መጮህ ብቻ ነው !

Post Reply