ባኒ መቀሌ
ናብ መቀሌ ብብከድከሉ እዋን ሃደ ዝገርመኒ ነገር ኔሩ:: ባኒ ናይ መቐለ!!!
መቀሌን የሚያውቅ መቼም መሃል ከተማ የሚገኘውን ገበያ ሳይጎበኝ አይመለስም:: በሬሳ ሳጥን ቅርፅ የተሰሩት ሱቆች ልዩ መገለጫው የሆኑት ይህ የገበያ ስፍራ በውስጡ አንድ ቁርስ ቤት ይዟል:: (ሱቆቹ በሬሳ ሳጥን ቅርፅ የተሰሩት ወያኔ በግፍ ጨፍጭፋ ያለቀባሪ የቀሩትን ለማስታወስ ነው ይባላል:: መሃንዲሱ ራሱ የገባበት አይታወቅም:: በሁለቱ ርእሶች እመለሳለሁ)::
ይህ ቁርስ ቤት አግድም ወንበር ያለው መሆኑና ሰው ሁሉ ፈታ ሊበላ መምጣቱ ግርም ይለኛል:: ፈታ ታዝና ዳቦና ሰሃን ይሰጥሃል ዳቦውን ቆራርሰህ ለስልሲ ተመልሰህ ትሄዳለህ:: ምንም አይገርምም::
የዳቦው ነገር ግን!!!!!!
ዳቦው ጭብጥ አትሞላም ነገር ግን ውስጧ ሙልት ያለ ሲሆን እንደዛ አይነት ዳቦ አይቼም አላውቅ:: አስቀያሚና ሌላ አማራጭ ስለሌለን ብቻ እንበላ ነበር::
አይ የመቀሌ ዳቦ
ምን አለ አዲስአባ መጥተው ዳቦ መጋገር እንኳን ቢማሩ እል ነበር ሁሌ::
ያየሁትን አልኩኝ እንጂ ከትግራይ ህዝብ ጋር ችግር የለኝም