በዚህ ሰሞን የሚወሩት መለስተኛ ግዜያዊ ወሬዎችን ወደ ጎን እናድርግ ። ያ ሁሉ ያልፋል !
ትልቁ ቁም ነገር አንድ፣ ጉራጌ ስለ ተከፋፈለ በ16ኛ ዘመን የደረሰበት ጥቃት ደግሞ እንዳይሞከርበት ማንኛውንም ዝግጅት ማድረግ አለበት ።
ሁለት፣ የጉራጌ ታሪካዊ አገርና ደንበር በምዕራብ የጊቤ ወንዝ ነው፤ በሰሜን ያዋሽ ወንሽ ነው ፤ በምስራቅ የዝዋይ ሃይቅ ነው። በደቡብ ወዳጅ ህዝቦቻችን እነ ሃዲያ፣ እነከምባታ፣ ወላይታ፣ የም እነዳውሮ፣ እነ ጃዬሮ ተራሮች ናቸው።
ሶስት፣ ዛሬ የጉራጌ ሕዝብ ቁጥር 1 ትኩረት ራሱ በራሱ ውስጥ አንድ ጽኑ አንድነት መፍጠር ነው። ስልጤ ከወገኑ የነጠሉት ሊያዳክሙት ነው። አሁን በቀቤና ፣ ወለኔ፣ ማረቆ ወዘተ ላይ ሚሰራው ራሱ ጉራጌን በታትኖ አዳክሞ ለመግደል ነው። ዛሬ ስልጤ ወደ ዘሩ ቢመለስ ራሱ እጅግ ሃያል ህዝብ ይሆናል። ዝዋይና የጉራጌ ሃይቆች ሁሉ የተወሰዱብን በዚህ ደባ ነው። የዛይ ጉራጌ ደራሽ ይፈልጋል፤ የኡርባረግ፣ ያዘርነት፣ የወረብ ጉራጌ ደራሽ ይፈልጋል ። ለዚህ ደሞ ስልጤ መጠንከር ከሰሜንና ከምዕራብ ወንድሞቹ ጋር ማበር አለበት ።
ጉራጌ ያለ አላማ የሚንከላወስ ጭፍን ሕዝብ አይደለም ። ጉራጌ አጀንዳ አለው ፣ ያም አጀንዳ ከኢትዮጵያ አጀንዳ ጋር አንድ ነው። ጉራጌ ማለት ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ ማለት ጉራጌ ነው።
ስለዚህ እጅግ አንገብጋቢ ጉዳይ የጉራጌ ክልል ለዚያ ታልቅና ታታሪ ሕዝብ የሚመጥን ከጊቤ እስከ አዋሽ፣ ካዋሽ እስከ ዝዋይ የተዘራውን በብዙ ስም የሚጠራው ጉራጌን በአንድ ትልቅ ራስ ገዝ አገር የሚያቆምና የመላው ጉራጌን ስልጣኔ ከፍ የሚያደርግ ክልል ነው ሚያስፈልገን!!!
ይህን ራዕይ የሰነቁ መሪዎች ሁሉ ባምስት፣ አስር ሚሊዮን የሚቆጠር ጉራጌ ባገርቤት፣ ባዲሳባ፣ በኢትዮጵያ ከተሞች፣ በመላ አለም በተዘሩት እንደ ሚደገፉ ጥርጥር የለንም ።
ጉራጌ መደራጀትና ራሱን መጠበቅ፣ ህልውናውና እድገቱን ሚያረጋግጥበት ማንኛውም ዘዴ ከመፍጠር መገታት የለበትም፣ ሚገታውም ሊኖር አይችልም ።
እሺ ለመሆኑ ጉራጌ ለምንድን ነው ክልል መሆን የሚፈልገው? ጥቂት የጉራጌ ፖለቲካ ልሂቃን የራሳቸው አላማ ሊኖራቸው ይችላል ። ነገር ግን የሚተለው የማነኛውም ጉራጌ ፍላጎት ነው ።
በመጀመሪያ ጉራጌ በማነኛውም ማዕከላዊ መንግስት ውስጥ የሚወከልበትም ሆነ የሚካፈልበት የራሱ መወከያና ራሱን ማስተዳደሪያ ድርጅት ያስፈልገዋል። ይህን ድርጅት የጉራጌ አስተዳደር ተባለ፣ የጉራጌ ክልላዊ መንግስት ተባለ ለውጥ የለውም ።
ሁለተኛ፣ ሁሉንም የጉራጌ ሕዝብ የሚያቅፍ፣ ሁሉንም የጉራጌ ሕዝብ ጉዳዮችን የሚያስተናግድ የጉራጌ ሕዝብ እድገት ድርጅት መፈጠር አለበት። ከዚህ ጋር በተያያዘ እንዲሁ በሁሉም መስክ የጉራጌን ነገር የሚያጠና የጉራጌ ምርምር ተቋም መፍጠር አለበት ።
በአንድ ውቃል፣ የጉራጌ ሕዝብ ቢያንስ የሚከተሉት 4 አላማዎች አሉት።
1 ጉራጌ አንድነቱ የጠነከረ፣ የተረጋጋ፣ ሴራው የጸና፣ ጠንካራ ሕዝብ መሆን ስለሚፈሊግ፤
2 ጉራጌ ነጻ፣ ዲሞክራሲ፣ ፍትህ፣ እኩልነት የጸናበት ራስ ገዝ ማህበረስብ መሆን ስለሚፈልግ፤
3 የጉራጌ ሕዝብ በኢኮኖሚ የበለጸገ፣ በትምህርት በቴክኖሎጂ በሳይንስ በጥበባት የዳበረ የላቀ መሆን ስለሚፈልግ፤
4 ጉራጌ በፈጠራ፣ በኪነት፣ በስነት የዳበረ ለኢኮሎጂው ደህንነት የቆመና በመንፈሳዊነት በኬርነት የጸና ባህል ወይም ካልቸር መሆን ስለሚፈልግ፤
ራሱ በራሱ የሚገዛበት፣ የራሱን እድገት የሚከውንበት፣ ሚመራመርበት አስተዳደር፣ ማህበር፣ ተቋም ያስፈልገዋል።