የኣለምን የተለያየ ቋንቋና ባህል ያቀፈችው፣ ከዛሬ ፭0 ኣመት በሗላ ይህ መናጋት ተጀምሯል። ለምን
እንደምናውቀው፣ ሃያላን ሆነው እስልምናን፣ ካቶሊክን፣ ቅኝ ግዛትን፣ ዛሬ ደሞ ዋሃቢን፣ ፕሮቴስታንትንና ኢኮኖሚን ተጠቅመው የህዝብ የሰላም ምኖሪያ ማንነታቸውን ኣጥፍተው ይኸው ኣልም ጫፍ ደርሳለች ወደ ባርነት ልትሔድ። ማናልባትም የኮሮና ያመጡትም የመጨረሻው ህዝብን ለመቆጣጠር ያስችላቸዋል።
ነፃውጪዎችም ይህን ተማምነው ነው ኢትዮዺያን ህዝብ እያጠፉ ያሉት።
የድር ኣብይና የሻብያ መቀራረብ ኣስጊ ነው። ለምን ኢሳያስ ለብዙ ኣመት ከውጭ የለመደውን ልምድ ወደ ኢትዮዺያ ኣስተላልፎ ህዝብን እንዴት ማታለልና ህዝብን በቁጥጥር ውስጥ ለማድረግ ጥልቅ የሆነ ልማድ ኣለው። ከ ፭0 ኣመት በሗላ ደሞ ተመልሶ ኢትዮዺያን ኣታሎ ከውጭ ግብረ ኣበሮቹ ጋር በመሆን ኢትዮዺያ የሚሉትን ማህበረሰብ ለማጥፋት ጫፍ ደርሷል። የነ ዶር ኣብይ ስራ ኢትዮዺያ ህዝብን እንቅልፍ ማስተኛት ይሆናል። ተስፋ የምናደርገው እውነት ኢትዮዺያን ከወደደ ከሻብያ ኢሳያስ መብለጥ ኣለበት። ብዙ ብዙ ማስረጃ እኮ ኣለ ክህዋሃት እንኳን ሳይስማሙ ሲቀሩ ኢትዮዺያን የማዳከም ኣጀንዳው። እውነት ለሰላም ከሆነ እሰየው ነው ግን በብዙ ነገሮች መፈተን ኣለበት ሰላምን መፈለጉ። ኢትዮዺያኖች ከህዋሃት ጋር ግጭት ያለው ሻብያ ያንን ኣይተን መፈንደቅ የለብንም። እራሳችን ስራ መስራት ኣለብን። ሻብያዎች ከኤርትራም ሆነ ከትግራይም የመጡ ቢሆንም ኣስተሳሰባቸው ነው ኢትዮጲያ ላይ ያላቸው ኣላማ የሚለየው።
የኢትዮዺያ ህዝብ የሚታለልበት ምክንያት
፩ ትግራይ ማህበረሰብን በማታለል ህዋሃትን ልከው ማን ከማን ላለመለየት እኛና እናንተ ኣንድ ነን በብዙ ነገር እንመሳሰላለን በማለት፣ ከሗላ ግን የማይፈልጉትን በኢትዮዺያነታቸው የሚኮሩትን ትግራይን የሗላ ቀር በማለት ኣጋሜ በማለት የሚንቋቸው ግን ህዝቡን ከኢትዮዺያውያን ጋር እንዲዋጋለትና እንዲተላለቅ የሚፈልግ ነው። ከዛም ወደ ድንበር ምስፋፋት የማድረግ ኣላማ ነው።
፪ ህዋሃት ከስልጣን ሲወርድ ሻብያ ኢሳያስ ወዲያውኑ ኣማራውን በማታለል፣ እኛ እኮ ኣይደለንም መለስና ህዋሃት ናቸው ያጣሉን በማለት ኣምራውን ለማለስለስ እያደረጉ ናቸው። ሻብያ ኢሳያስ መሬት ላይ ስለ ኢትዮዺያ መረጃ ስለሚኖረው ምን እንደሚከሰት ኢትዮዺያ ውስጥ ጥርት ኣድርጎ ያውቃል። ኣስቀድሞ የህዋሃት ተቃዋሚዎች የሚላቸውን እየተንከባከ ዛሬ እየተከሰተ ያለውን ኢትዮዺያ ውስጥ ሲመጣ ተቃዋሚዎችን ይኸው ማስረጃዬ ከኢትዮዺያኖች ጋር እየሰራሁ ነበር የሚል ማሳመኛ። ኣንዳንድ ኣማራ ውስጥ የቂም በቀል፣ ጥላቻ ትቶ ግን ኣገርና ማህበረሰብን ብቻ መከላከል ኣለበት ይህ ማለት ጦርነትም እኮ በቂም በቀል በጥላቻ ሳይሆን እራስንና ህልውናን ለመጠበቅ ነው።
፫ ኤርትራ ውስጥ የነበሩ ተቃዋሚዎች ማን ናቸው ከኦነግ ሌላ። ምን ኣይነት ፕሮፖጋንዳ ተደርጎባቸዋል ምንስ ያህል የሻብያን ሚስጥርና ኣላማ ይገነዘባሉ። ኣብዛኛው ኢትዮዺያውያን ህዋሃትና ሻብያን ለምንድን ነው ለየብቻ የሚያየው። ፈተና ከመጣባቸው እነዚህ ሁለቱ ኣንድ ላለመሆናቸው ኢትዮዺያውያኖች ምን ማስረጃ ኣላቸው። ከኢሳያስ ሻብያ ጀርባ ያሉት ሃያላን እነ ማን ናቸው። ልምን የውጭ ሃያላን ህዋሃት በህዝብ ሃይል እንደሚወርድ ስለሚያውቁ ኣዲሱን መንግስት ባስቸኳይ ከሻብያ ጋር ስምምነት ኣድርግ ብለው መከሩ። ማንን ይጠቅማል። መጀመርያውኑስ በነሱ ሃይል እና በኣረቦች ሃይል ኣይደል ሻብያ ያሸነፈው።
፬ ሌላው ሿሿ፤ ሻብያ ደቡብን የማታለል በተለይ እንደ ጉራጌን የመሰሉትን፣ እናንተ እኛ እኮ ኣንድ ነን ከጉራ በሚባለው ስፍራ ነው የመጣችሁት በማለት ይሄንን የማለስለስ ማህበረሰብ።
፭ ኦሮሞውን ደሞ ኦሮሞ ኣቃፊ መሆኑን በመገንዘብ ማህበረሰብ ውስጥ በመግባት ማንነትን ቀይሮ ኦሮሞ በመምሰል ኢትዮዺያ ማህበረሰብ ላይ በተለይም ኣማራው ማህበረሰብ ላይ የጥላቻ እሩምታ ማስደረግ ነው። ይህ ግልፅፅ በሆነ በተስፋዬ ገ እባብ እና ወርቅ ነህ ገበየሁ መረጃ ነው። ኣባ ዱላስ እውነት ማነው። ዶር ኣብይ የመጣው በኣባ ዱላ ነው።
ሻብያም ሆነ ህዋሃት የኢትዮዺያ ወዳጅ የነበሩትን ኣገራት ሃሰት በመናገር ለነሱ ብቻ እንዲጠቅሙ ኣድርገዋል። በሃይለ ስላሴ ጊዜ ማንኛውም ዲፕሎማሲ ለኢትዮዺያ እንጂ ለግላዊ ኣልነበረም። ለዚህ ነው በተለይ ባለም እየተከሰተ ያለውን ሁኔታ በማየት ከመንግስት ውጪ ኢትዮዺያውያን እኔ የዚህ ዘር ነኝ የዚህ ሃይማኖት ነኝ ከማለት በውጭና በነፃውጪዎች ባስቀመጡላቸው ውስጥ ኣምኖ ከመግባት ጥናት ኣድርገው ህልውናቸውን ኣንድ ላይ ማስከበር ግዴታቸው ነው።