ያቤሎ፤
በጣም አመሰግናለሁ ! እዝኬር ያብሊ !!!
የግጥሙ ደራሲ መደነቅ ይገባዋል ። ለምን ብትል የግጥሙ ይዘት፣ መልዕክትና ትምህርት ዘመን፣ ትወልድ፣ መንግስት ተሻጋሪ ስለሆነ ። እስቲ ከምንም መንግስት ፣ ከምንም ፓርቲ ሳታያይዝ ስማው !! ድንቅ ነው ። አንድም ቃል ሳይለወጥ ፣ ለምኒልክ፣ ለሃይለ ስላሴ፣ ለደርግ፣ ለዎያኔ ፣ ለአቢይ አህመድ ፣ ለብልጽና ፓርቲ፣ ለኢዜማ ሁሉ መዝሙር ሆኖ የሚሰራ ነው ።
ለምን ናዪቭ (ሞኝ) እንዳልከው አልገባኝም፤ ኦነስት ቢባል ትክክል ነው። ያ የዚያ ዘመን ወጣት ተስፋና እምነት ነበር ። ዛሬም ይሰራል ። ይህ መዝሙር የዛሬ 16 አመት ወጣት ሲሰማው የሚሰማው ስሜት ከኛ ጋር አንድ ነው ።
በነገራችን ላይ እኔን እጅግ ሆድ የሚባባኝ ወጣቱ ለእድገት በህብረት ወደማያቁት ገጠር ሊሄድ ሲጫን 'አገር ምድሪቱ በሰላም ትቀበላችሁ' እየተባለ ይዘመር የነበረውና የኢሕአፓ ልጆች በቡድን ሊረሸኑ ሲዘጋጁ (ከቀኑ 12 ሰአት ካባቢ) እስር ቤት ይዘመር የነበርውን ሳስታውስ ነው ።
ኬር !!!
Re: HORUS: here is a much better version of the famous 'tenesa-teramed' song complete with the lyrics. Enjoy!
ያቤሎ፣
እንደ ገና ትልቅ ምስጋና ! አዎ በዚያ እንደ ማር ወለላ በሚወርደው የማይረሳው የታምራት ሞላ ድምጽ 'አድባር ትቀበላችሁ' ይባል ነበር ። የያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት ይህን ታሪክ ስላስቀሩልን ይመስገኑ ። በገራችን ላይ እነዚህን መዝሙሮች የጻፈው ሰው አሁንም በህይወት አለ፣ በታማኝ ወይም በተቦርነ ፕሮግራም ቀርቦ ነበር ። ኬር !