ኢዮ እንዞሪቴ ገና ነበቦ፣
በባዮች አንቃት ጮታ ገነኖ፣
በገና ኧሚት ሰብ ሚረቀኖ፣
በዛዎች ገንዳ አውከሬ ዪኖ፣
አሲዮ ኢዮ በል ይደምቅብኖ።
ግሪዳዲማ ይብልማን ኢምር፣
የምሸት ደራቃ የቅናን ጨበር፣
ኢምር የምሸት የጠጥበት ደምበል፣
ቢቲ ተሳጥሽም የገና ጀምበር።
ኢዮ እንዞሪቴ ገና ነበበ ማለት እነሆ ሆያ ሆዬ እንዞራለን ገና ደረሰ ማለት ነው ። ኤቦ ሆነ፣ በራ ፣ አበበ ማለት ነው።
አንቃት የገና ጨዋታ ነው ። ራሱ ኳሱ (ጥንጉ) እንዲሁ አንቃት ይባላል። በትክክል ግን አንቃት ጠማማ እግር ያለው ዱላ ማለት ነው።
የሴቶቹ ወግ ውስጥ ኢምር ማለት እጅግ እጹብ ድንቅ የሆነ የኮከብ ብርሃን ሲሆን ጸሃይን ለማቆላመጥ የሚዘፍኑት ነው ።