Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
pushkin
- Member+
- Posts: 9682
- Joined: 23 Jul 2015, 06:10
Post
by pushkin » 13 Mar 2020, 05:58
ቅዱስ እግዚአብሔር ህዝብ ወይም ፍጡር እንጅ ካርታ እና ባንዴራ የለውም። ሁሌ የሚከነክነኝ አንድ ነገር አለ። እኔ የእመቤቴ ቅድስት ድንግል ልጅ የጌታ እየሱስ ክርስቶስ ተከታይ ክርስቲያን ወይም ንጹሕ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ነኝ። ከዚህ ልጅ ጀምሮ በብዙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊያን ዘንድ ግን በጣም የተሳሳተ እና የተዛባ አንድ አጉል ባህል ወይም ድንቁርና እመለከታለሁ። ይሄም ሰማያዊውን እምነት ከምድራዊው ሀገር፣ ባንዴራ እና ዘር ጋር የማቆራኘት በሽታ ነው። ቅድስት ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ሀገሯ - ሰማይ፣ ህዝቧ - ምእመናኑ ፣ መሪዋ - ክርስቶስ፣ ቋንቋዋ - ፍቅር፣ አርማዋ(ባንዴራዋ) ደግሞ መስቀል ብቻ ነው። ነገርግን ምድራዊውን እና ሰዋዊውን አስተሳሰብ ከሰማያዊ እምነት ጋር እየደባለቃቹ የቤተክርስቲያኒቱን ግብ እና ኣላማ እባካችሁ አታርክሱ፣ መእመኗንም ከደጇ አታርቁ። ሀገር እና እምነትን ለያይታቹ ተመልከቱ።
“የቄሳርን ለቄሳር፣ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ” የሚለው ቃል ይግባቹህ እንጅ? ይህ ባንዴራ እና ካርታ ምድራዊ ነው። ፈጣሪ ካርታ የለውም፤ አምላክ ካርታ እና ባንዴራ ቢኖረው ንሮ ጀርመን ወይም ኢትዮጵያ አንዷ የሰይጣን አንዷ ደግሞ የእግዚአብሔር ሌሎቹ ደግሞ የሌሎች በሆኑ ነበር። በተለይ አንተ ዘመድኹን የምትባል ኃላ ቀር ገገማ በጣም ሲበዛ ይህን ህገ-ወጥ ካርታ ኣብዝተህ ትጠቀማለህ፤ ይህም ድንቁርናህን ለመግለጽ ያህል እንጅ kitchen ውስጥ ሁኖ ለሚዘባርቅ አንድ ፈሳም እና ወረኛ ያውም ሰባት ባህር ተሻግረህ እና የፈረንጅ ፍርፋሪ እየበላህ ለሚፎክር ሴታሴት ዋጋ እና ትርጉም ሰጥቼ አይደለም። የሚያሳዝነኝ ግን ይህን በሀገሩ የሚኖር ምስኪኑን ህዝብ ማዶ ሁናቹ ከወንድሙ እና ከጎረቤቱ ህዝብ ጋር በእምነቱ ይሁን በዘሩ ወይም በባንዴራ ይሁን በካርታ ስታናቁሩት ሁሌ መመልከቴ ነው።
ሰውየ ወንድ ከሆንክ ከራየን ወንዝ ማዶ ሳይሆን ከአባይ ወይም ከአዋሽ ወንዝ ማዶ ወርደህ ፎክር እሽ ?
ዓወት ለሓፋሽ !!!
ሰሚራ ነኝ ከመረብ ወንዝ ማዶ
Please wait, video is loading...