Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40074
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ከጉራጌ ስነ ምግባር ና ሕገ ባህሪ አንዱ የበርቸ ወይም የጡር ካልቸር

Post by Horus » 12 Mar 2020, 00:15

ግፍና ከተፈጥሮም ከስብዕናም ያፈነገጡ አስቀያሚ፣ አሳዛኝ፣ ሌላውን አላግባብ የሚጎዱ፣ ግፈኛ ተግባራት ሁሉ ሰው ሰው ካያቸው እርግማን፣ ሰው ካላቸው ጡር (ክፉ መዘዝ የሚያስከትል ማለት ነው) ባህሪያት ሆነው ይመደባሉ ። ማህበረሰቡ እነሱን ከመሰሉ ተግባራት ራሱን ይጠብቃል ። ለምሳሌ አንድ የዱር አዋሪት እንደ ድኩላ ያለ ተሳስቶ ግቢ በገባ አይነካም ። አንድ ሽማግሌ ጉልበት ከሌለ ጉልበት የለውም ተብሎ አይጠቃም፣ ወዘተ፣ የባህል ሸንጎ የነዚህን ባህሪያት ጥፋት ልክ ዝርዝር አለው፣ ለመቀጮ ማለት ነው። ባጭሩ እነሆ !!!