Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
AbebeB
Member+
Posts: 7694
Joined: 15 Oct 2016, 10:31

Ethio 360: የሽግግር ምሥረታ አስፈላጊነት፣ ቅርጽና ይዘት ሳይሆን ሊቀርብ የሚገባው አማራ ለሽግግሩ ተቋም የሚያቀርበውና ስለ ሌላው ብሔር የሚሰጠውን ዕውቅና ድራፍት ነው። የማያዋጣ ከሆነ

Post by AbebeB » 11 Mar 2020, 19:03

የሽግግር ምሥረታ አስፈላጊነት፣ ቅርጽና ይዘት ሳይሆን ሊቀርብ የሚገባው አማራ ለሽግግሩ ተቋም የሚያቀርበውና ስለ ሌላው ብሔር የሚሰጠውን ዕውቅና ድራፍት ነው። የማያዋጣ ከሆነ ሌላው ብሔር ወደ ሽግግሩ የመግባት አስፈላጊነት ላይታየው ይችላል።

አማራ ስለ ጮሄ ብቻ ሽግግር እያለ መጨናበስ ለምን ያስፈልጋል? የምርጫው ውጤት በእኔ ብሔር ላይ የሚያመጣው ጉዳትና ጥቅም አለ ወይ የሚል ግምገማ የማያደርግ የብሔር ፓርቲ አለ ብዬ አልገምትም። ስለዚህ የአማራ ልህቃን እንዲሁ በጅምላ ከመጮህ እልፍ ብሎ (ልደታም ቢሆን) አሁን በአለው ሁኔታ ለሌላው ብሔር የሚሰጠው ዕውቅናና ልደራደርበት እፈልጋለሁ የሚለውን መብት፣ ጥቅሙንና ግዴታውን ለይቶ ማስታወቅ ይጠበቅበታል።