Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

የአማራ ባንክ ከ3.12 ቢልዮን ብር በላይ አክስዮን በመሸጥ ወደስራ ሊገባ ነው። የአክሲዮን ሽያጭ የሚጠናቀቀው ታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ነው

Post by Maxi » 03 Jan 2020, 13:04

የአማራ ባንክ ከ3.12 ቢልዮን ብር በላይ አክስዮን በመሸጥ ወደስራ ሊገባ ነው። የአክሲዮን ሽያጭ የሚጠናቀቀው ታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ነው

በምስረታ ላይ የሚገኘው የአማራ ባንክ አክሲዮን ሽያጭ በሚመለከት የተሰጠ አጠር ያለ መረጃ!!



Amhara Economic Think Tank S.C.


ምስጋና!

በምስረታ ላይ የሚገኘው የአማራ ባንክ አክሲዮን ሽያጭ የሚጠናቀቀው ታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ነው።

እስካሁን የተፈረመ 3.12 ቢሊዮን እና
የተከፈለ 2.35 ቢሊዮን ደርሷል።

የአክሲዮን ሽያጭ ከመጠናቀቁ በፊትና የወደፊት አመራር ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ግን በፕሮጀክቱ ተሳትፎ ላደረጉት አካላት ምስጋና እናቅርብ።

የአማራ ባንክ አ.ማ ምስረታ እውን ለማድረግ በርካታ ሰዎች በቅንነት እና በቁርጠኝነት ለአንድ አመት ያክል ደክመዋል።
ይህ ፕሮጀክት ከ 50 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያደረገበት የቤተ ንዋይ ፕሮጀክት ነው።

በምስረታ ላይ ያለው የአማራ ባንክ ፕሮጀክት የአንድ ግለሰብ፥ የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የአንድ አካባቢ ቡድኖች ብቻ የስራ ውጤት አይደለም። ገንዘቡ፥ የስራ ሂደቱ፥ አመራር መምረጡ፥በብሄራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት፥ የባንኩን የወደፊት አቅጣጫ በበላይነት የሚወስኑት ባለ አክሲዮኖች ናቸውና ለባለ ድርሻ አካላት አደራና ምስጋና ይድረስልን።

ባላክሲዮኖች እስከ ሶስት ቢሊየን ብር የሚጠጋ ካፒታል ማሰባሰብ የቻሉት፥ ለሃገር ህልውና የሚጠቅም፥ ለብዙሃኑ የህብረተሰብ ክፍል የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴ አወንታዊ ለውጥ ሁነኛ ሚና ይጫወታል የሚለውን የፕሮጀክቱ አላማ አምነውበት እንጅ፥ በአንድን ግለሰብ ተማምነው በስሜት የወሰኑት እንዳልሆነ እንረዳለንና በድጋሜ ክብር ለህዝብ፤ ትልቅ ምስጋና ለባለ አክሲዮኖች ይገባቸዋል!!

በፕሮጀክቱ ቆይታ ሁሉም 50 ሚሊዮን ህዝብ ፍፁም እኩል የሆነ አስተዋፅኦ ላይኖረው ይችላል፤ ለባንኩ ዕውን መሆን ግን የሁሉም ተሳታፊዎች፥ የሁሉም ባላክሲዮኖች፥ የባንኮች፥ የሴክተር መስሪያ ቤቶች ወዘተ የጋራ ውጤት መሆኑ ታሪካዊ ሃቅ ነው።

ሆኖም፥ ባሳለፍነው ከባድ የፖለቲካ ሞገድ በነበረበት አመት፥ ለኢትዮጵያውያን የሚበቃ ቤተ ንዋይ ፕሮጀክት ቀርፀው ለዚህ ላበቁ ወጣት ምሁራን እና ዘግይተውም ቢሆን ተቀላቅለው ፕሮጀክቱ ከዚህ ደረጃ እንዲደርስ ጥረት ላደረጉ ሃላፊዎች፥ አስተባባሪዎች፥ ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች አበርክቷቸውን በጥቅል ለመዘከር መልካም ስራን እንድናስታውስ ይረዳናል።

ስለ አማራ ባንክ እና ሌሎች ቀጣይ ፕሮጀክቶች ለ 8 ወራት ያክል ሲወያዩ፥ አካሄድ ሲነድፉና ሰነድ ሲያዘጋጁ ቆይተው፥ ይህን ፕሮጀክትን ወደ መሬት በተግባር በማውረድ ፈር ቀዳጅ የሆኑ ወጣት ሙሁራንን ወደፊት እንጠቅሳለን።

ለዛሬው ግን እደጉልን በሏቸው።

እስካሁን ባለው የፕሮጀክቱ እንቅስቃሴ በተሳካ ሁኔታ እንዲሄድ ተሳትፎ ያደረጉ ግለሰቦች፥ በስራ ሂደቱ ላይ ያበረከቱት ጉልህ ሚና እና መልካም ስራቸው ማህበራዊ ሚዲያው እንዲያስታውሰውና፥ የመልካም ስራ መንፈስ መንሸራሸር ትርጉሙ በቃላት ከሚገለፀው በላይ ሊሆን ስለሚችል፥

ቅን ልቦች ሁሉ ይባረኩ።

ሲቀጥልም፥ እንደ አማራ ምጣኔ ሃብት መማክርት አባላት እምነት፥ አብረውን ለደከሙ ሁሉ ከወዲሁ እጅ መንሳታችን እንጅ፥ በስምና በግብር ተዘርዝሮ ጊዜ በሚፈቅደው፥ በሚመጥናቸው ቦታ እና ሁኔታ፥ አስተዋጽኦቸው እንዲዘከር ቀጣይ ሌላው የቤት ስራችን ይሆናል ።

ከወዲሁ ግን እግዚያብሄር ይባርካችሁ ብለናል።

ልዩ ምስጋና፦

ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እና የአዲስ ባንኮች ክትትል ክፍል የስራ ባልደረቦች፥ የስራ መሪዎች፤

ለሁላችሁም እጅ ነስተናል!

ለንግድ ባንኮች፦

አቢሲኒያ ባንክ፥ አባይ ባንክ ፥ ቡና ባንክ፣ ዳሽን ባንክ፣ ኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበር፣ ሕብረት ባንክ፣ አንበሳ ባንክ፣ ንብ ባንክ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፥ እና አዋሽ ባንክ ...

ስማችሁ በአወንታዊ ጎኑ፥ Basel III ከፍ አድርጎ ይጥራው፤ የአለም ባንኮች ጉልላት ሁኑልን፤ በጣም እናመሰግናለን!!!

የሴክተር መስሪያ ቤቶችና ድርጅቶች፥
የኢትዮጵያ ንግድና ኢንድስትሪ፥
የጥበብ ሰዎች፥
የማስታወቂያ ድርጅቶች፥

የዜና አውታሮ፦

Amhara Mass Media, ASRAT Media House, SBS Radio, Ethiopian Broadcast Service, The Reporter, Walta Television, Fana Broadcast Corporation, Amhara FM Radio, Ahadu Radio, Amhara Media Center, አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ..........

ሁላችሁንም ከልብ እናመሰግናለን።

ሰላማዊ አርብ ከሰአትና መልካም ምሽት፥ የደስታ በአል ይሁንላችሁ!!


https://www.facebook.com/amharaeconomic ... 6475190368