Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11396
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

የቻይናው አምባሳደር ተጠርተው ማብራሪያ ሊጠየቁ ይገባል !

Post by MINILIK SALSAWI » 19 Dec 2019, 13:34

During a meeting PM AbiyAhmed had with Tigray native businesspeople who are serving as go-betweens with the TPLFites, he went as far as suggesting he could hand universities in Tigray over to the regional state, thus cutting federal resources, gossip says.

Minilik Salsawi

ቻይና ትግራይና የፌዴራሉ ሕገ መንግስት ?

የቻይናው አምባሳደር ተጠርተው ማብራሪያ ሊጠየቁ ይገባል !

የኢፌዲሪ ሕገ–መንግሥት የፌድራል መንግሥትን ሥልጣንና ተግባር በወሰነበት አንቀጽ 51 (4) የውጭ ግንኙነትን ስትራቴጂና ፖሊሲ ማውጣትና ማስፈጸም የፌድራል መንግሥቱ ሥልጣን መሆኑን በግልጽ ይደነግጋል።

የቻይና መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት እውቅናና ፈቃድ ውጪ ለፌዴራሉ መንግስት የውጪ ጉዳይና ኢንቨስትመት ቢሮ ሳታሳውቅ ባለስልጣናቷን ወደ ትግራይ ክልል ለመላክ አይሮፕላን ማሳፈሯ የሃገር ሉዓላዊነትን ከመድፈር ተለይቶ አይታይም።

የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርፖርት የመለሳቸው የቻይና ባለስልጣናት የመንግስትን አሰራር በመጣስ ወደ መቀሌ ሊያቀኑ የነበሩ መሆኑ በውስጥ ጉዳያችን ንትርክ ተከትሎ ያሳዩን ንቀት ነው።

PM AbiyAhmed also said it is possible to cut flights to the region down to one or suspend federal subsidies and other public services to the regional state, claims gossip.

ወደ ሆንግኮንግም ሆነ ታይዋን ለመሔድ የሚፈልጉ የሃገራት ባለስልጣናት የቻይናን ፈቃድ እንደሚጠይቁ ሁሉ ቻይናም ወደ ማንኛውም የኢትዮጵያ ክልሎች ለመሔድ የፌዴራሉን መንግስት ፈቃድ መጠየቅ ነበረባት፤ በባለስልጣናቱ ላይ የተወሰደው እርምጃ ተገቢ ቢሆንም አምባሳደሯ ግን ማብራሪያ ሊሰጡ ግድ ይላል። #MinilikSalsawi


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11396
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: የቻይናው አምባሳደር ተጠርተው ማብራሪያ ሊጠየቁ ይገባል !

Post by MINILIK SALSAWI » 19 Dec 2019, 13:47

9 አባላት የያዘ ከአንዲት የቻይና ግዛት የተላከ ልኡክ ትላንት ማታ በ 1 ሰዓቱ የአየር በረራ ለስራ ጉዳይ ወደ መቐለ ለመብረር ፍተሻ ጨርሰው ለመብረር ሲዘጋጁ ድንገት 'ከውጭ ጉዳይ ነው የታዘዝነው' ባሉ የአየር መንገዱ ሰዎች ትእዛዝ መሰረት ቦሌ ኤርፖርት ላይ ወደ መቐለ እንዳይጓዙ መከልከላቸውና አ.አ እንዳደሩ ታውቋል።

በመሀከላቸው ከቻይና ኤምባሲ ዲፕሎማት ከልኡኩ ጋር ቢኖርም የጉዞአቸው ምክንያት ለማብራራት ቢሞክሩም ''እኛም ታዘን ነው የምናውቀው ነገር የለም'' የሚል መልስ ተሰጥቶዋቸዋል። ኤምባሲው ትላንት አመሻሽ በስልክ ደውሎ ለውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ሀላፊዎች ቅሬታውን ገልጿል ተብሏል።

ቀደም ሲል የኤዥያ አምባሳደሮች በአንድ ላይ የትግራይ ክልል መንግስትንና የክልሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመጎብኘት በሄዱበት ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱኳን አያኖ ወደ ልኡካኑ ቡድን መሪ (ዲን) የሆኑት የባንግላዴሽ አምባሳደር የቪየና ኮንቬንሽን በመጣስ ስልክ በመደወል በአስቸኳይ ወደ አ.አ እንዲመለሱ ትእዛዝ መስጠታቸው አነጋጋሪ ሆኖ ነበር።

Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: የቻይናው አምባሳደር ተጠርተው ማብራሪያ ሊጠየቁ ይገባል !

Post by Revelations » 19 Dec 2019, 14:00

With the current grip of China over Ethiopia, it's unlikely Qibewu the wimp will dare do such a thing. But tweeps are saying Ethiopia will be the first in the world to have a gun salute to a satellite launching! Is there an end to this nonsense?! :lol: :lol: :lol:

Zelku
Member
Posts: 109
Joined: 03 Jul 2017, 16:23

Re: የቻይናው አምባሳደር ተጠርተው ማብራሪያ ሊጠየቁ ይገባል !

Post by Zelku » 19 Dec 2019, 14:12

Minew amemeh Rivo? Isist neger neh!!

Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: የቻይናው አምባሳደር ተጠርተው ማብራሪያ ሊጠየቁ ይገባል !

Post by Revelations » 19 Dec 2019, 14:17

Zelku wrote:
19 Dec 2019, 14:12
Minew amemeh Rivo? Isist neger neh!!
Whaaaat? Are you saying Qibew isn't wimp or gun salutes for satellite launching (satellite made by China, launched by China which will give it even more leverage over Ethiopia..) is not nonsense? :oops:

Post Reply