"የዛሬዋን ኢትዮጵያ በስሁት መንገድ እየነዳ አምጥቶ ገሃነም በር ላይ አስቀምጦ የሄደው የህወሃት ዋና ፈሊጥ አማራ የሚባለውን የኢትዮጵያ ህዝብ በሆነውም ባልሆነውም መክሰስ፣ ማክፋፋት፣ ቅስም መስበር ነው፡፡ ህገ-መንግስት ሲፅፍ የአማራውን ትምክህት ለመስበር እንደሆነ ለተላላ ሰሚዎቹ ይነግራል;
የመሬትን ባለቤትነት ለብሄር ብሄርሰቦች ሰጠሁ ሲል መሬቱን አማራ እንዳይገዛው እየጠበቅኩላችሁ ነው ሲል እየሰበከ ነው፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ አማራው ንጉስ የጠላው ፍጡር የሚያየውን መከራ ሁሉ አይቷል፡፡የህወሃት የስልጣን ዘመን የተሟሸው አማራው በበደኖ እና አርባጉጉ ባሰማው የሲቃ ድምፅ ነው፡፡ይህ የሲቃ ድምፅ ለህወሃት የድል ማህተም ነው፤ የአማራ አከርካሪ መሰበር፣ ላይመለስ ሞቶ ርቆ መቀበር ምልክት ነው፡፡ የሰው ልጅ አሰቃቂ ሞት የሰብዓዊ መብት ጉዳይ መሆኑ ቀርቶ የዝቅተኝነት ስሜት ማርገቢያ ሙዚቃ ሆነ፡፡ የአማራው መፈናቀል፣ በአንድ ሌሊት ሃብት ንብረት አራግፎ ነፍስ ብቻ ይዞ እግር ወደመራው መትመም አጀብ የማያሰኝ አዘቦታዊ ነገር፣ ጆሮ ዳባ ልበስ የሚባል ተገቢ ነገር መሰለ፡፡ ይህ የሆነው ለአጭር ጊዜ አይደለም-ለሩብ ምዕተዓመት እንጅ!
በሃገራችን መፈናቀል ብርቅ ሆኖ ማነጋገር የጀመረው ከሁለት አመት ወዲህ፣ የዘር ፖለቲካው ከአማራው ሌላ ብሄረሰቦችን ቤት ማንኳኳት ሲጀምር ነው፡፡የዘውግ ፖለቲካው ከጨቋኙ የአማር ብሄር በስተቀር ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችን አስተቃቅፎ የሚያኖር፣ ከአማራ ጭቆና የሚታደግ ድንቅ እድል ተደርጎ ሲሰበክ ኖሯል፡፡ የዘውግ ፌደራሊዝሙ ለአማራው ያልተመቸው ደግሞ ሊጨቁን በሃገር ዳርቻ ስለተበተነ ነው የሚል ተረክ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሲተረክ ኖሯል፡፡ ይህ ተረክ እውነት አለመሆኑ እየታየ የመጣው በጨቋኝነት የማይታወቁት እንደ ጌዲኦ፣ ኦሮሞ ከሶማሌ ክልል፣ ከምባታ ከከፋ፣ ወላይታ ከሲዳማ በገፍ መፈናቀል ሲጀምሩ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ይህ እውነታ የታወቀው እጅግ ዘግይቶ በመሆኑ አማራው ከብዙ አቅጣጫ በሚወረወር ጦር እንዲዋከብ አድርጎት ኖሯል፡፡ የዚህ ድምር ውጤት ዛሬ በአስፈሪ ሁኔታ እያደገ የመጣውን የአማራ ብሄርተኝነት ወልዷል፡፡" Meskerem Abera
https://ethiothinkthank.com/2019/09/25/ ... tionalism/
-
Za-Ilmaknun
- Member
- Posts: 4486
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
-
Za-Ilmaknun
- Member
- Posts: 4486
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Re: "የህወሃት የስልጣን ዘመን የተሟሸው አማራው በበደኖ እና አርባጉጉ ባሰማው የሲቃ ድምፅ ነው"
ባለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት አማራ መሆን ራሱን የቻለ ችግር ሆኖ ኖሯል፡፡ በዚህ ዘመን ባለችው ኢትዮጵያ በተለይ ከክልሉ ውጭ የሚኖረው የአማራ ተወላጅ ሰው ቤት እንዳለ ሰው አሳቃቂ ተቆጭው በዝቶ የኖረ ህዝብ ነው፡፡ ሆኖም የዚህ ህዝብ እንግልት አደጋውን በሚመጥን ደረጃ የሚታገልለትነት የአማራ ብሄርተኝነትን ሳይወልድ ቆይቷል፡፡ በዚህ ምክንያት የአማራ ህዝብ ብርቱ ጠበቃ በሚያስፈልገው የህወሃት የስልጣን ዘመን ሁነኛ ተሟጋች ሳያገኝ መራራ ፍዳውን በየግሉ ሲጎነጭ ኖሯል፡፡ ይህ ለምን ሆነ ለሚለው ወሳኝ ጥያቄ ዋነኛው መልስ የህወሃት ጫና ነው፡፡ባለስልጣኑ ህወሃት ከጫካ ጀምሮ የተዋጋለት ዓላማ የአማራውን ቅስም መስበር ነው፡፡ በኋላ ጠቤ ከገዥ እና ነጅው አማራ ጋር ነው እንጅ ከህዝቡ ጋር አይደለም የሚለውን ኢህአዴጋዊ መቀላመድ አምጥቷል፡፡ ሆኖም ህወሃት አማራን እንደ ህዝብ እንደ ባለጋራ የሚያይበት ልክፍት እንዳልለቀቀው ማሳያው ብዙ ነው፡፡ ከብዙው አንዱ አፈር ገፊውን አማራ ለዘር ያስቀመጠውን እህል ሳይቀር በቀበሌ ካድሬ እንዲቃጠልበት እያደረገ ሲያፈናቅል፣ ይህ ደግሞ ትክክል መሆኑን በፓርላማ ሳይቀር ሊያስረዳ ሲነሳ ነው፡፡
ህወሃት በአንድ በኩል አማራውን በእሾህ ለበቅ እየገረፈም የተበድየ ተረክም ሆነ ተጨባጭ በደል የሚወልደው የዘውግ ብሄርተኝነት በአማራው ዘንድ ብቻ ሲሆን እንዳይበቅልም ወገቡን አስሮ ይሰራ ነበር፡፡ ለምን ቢባል የአማራው ብሄርተኝነት ከተወለደና ካደገ አማራን እንደ ጭራቅ እየሳሉ ማስፈራራት አይቻልም፡፡ ይህ ካልሆነ ግንዛቤ የጎደለውን የዘር ፖለቲከኛ በዚሁ አማራ በተባለው ጭራቅ ተፃራሪ አሰልፎ ‘እኔ አማራ ከተባለ ከጭራቅ የማድናችሁ ታዳጊያችሁ ህወሃት እባላለሁ’ እያሉ ስልጣን ማስረዘም አይቻልም፡፡ በበኩሌ ህወሃት አማራውን ከኢትዮጵያዊነት ከፍታ አውርዶ ብሄርተኛ አድርጎ ለማሳነስ ሲሰራ ኖሯል በሚለው ሙግት አልስማማም፡፡ ይልቅስ ተቃራኒውን አምናለሁ፡፡ ህወሃት የአማራው ብሄርተኝነት አድጎ በህዝቡ ላይ የሚወርደውን በደል ባያስቀር እንኳን በደሉ ስለመድረሱ ሰብዓዊነት ለሚሰማው ሁሉ ክስ እንዳያቀርብ ተግቶ ሲሰራ መኖሩ ትክክለኛ ትንታኔ ሆኖ ይታየኛል፡፡
ህወሃት በአንድ በኩል አማራውን በእሾህ ለበቅ እየገረፈም የተበድየ ተረክም ሆነ ተጨባጭ በደል የሚወልደው የዘውግ ብሄርተኝነት በአማራው ዘንድ ብቻ ሲሆን እንዳይበቅልም ወገቡን አስሮ ይሰራ ነበር፡፡ ለምን ቢባል የአማራው ብሄርተኝነት ከተወለደና ካደገ አማራን እንደ ጭራቅ እየሳሉ ማስፈራራት አይቻልም፡፡ ይህ ካልሆነ ግንዛቤ የጎደለውን የዘር ፖለቲከኛ በዚሁ አማራ በተባለው ጭራቅ ተፃራሪ አሰልፎ ‘እኔ አማራ ከተባለ ከጭራቅ የማድናችሁ ታዳጊያችሁ ህወሃት እባላለሁ’ እያሉ ስልጣን ማስረዘም አይቻልም፡፡ በበኩሌ ህወሃት አማራውን ከኢትዮጵያዊነት ከፍታ አውርዶ ብሄርተኛ አድርጎ ለማሳነስ ሲሰራ ኖሯል በሚለው ሙግት አልስማማም፡፡ ይልቅስ ተቃራኒውን አምናለሁ፡፡ ህወሃት የአማራው ብሄርተኝነት አድጎ በህዝቡ ላይ የሚወርደውን በደል ባያስቀር እንኳን በደሉ ስለመድረሱ ሰብዓዊነት ለሚሰማው ሁሉ ክስ እንዳያቀርብ ተግቶ ሲሰራ መኖሩ ትክክለኛ ትንታኔ ሆኖ ይታየኛል፡፡
-
Za-Ilmaknun
- Member
- Posts: 4486
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Re: "የህወሃት የስልጣን ዘመን የተሟሸው አማራው በበደኖ እና አርባጉጉ ባሰማው የሲቃ ድምፅ ነው"
"በነገራችን ላይ የማንኛውም ዘውግ ብሄርተኝነት ማደግ የትኛውንም ዘውግ ከመበደል አያድነውም፡፡ለምሳሌ በኢትዮጵያ በአንጋፋቱ ከህወሃትም የሚቀድመው የኦሮሞ ብሄርተኝነት የኦሮሞን ህዝብ ከእስር፣ እንግልት፣ መፈናቀል መሰደድ፣ መሞት፣ መታሰር አላዳነውም፡፡ ያደረገለት ነገር ቢኖር ይህ መከራው ለሰሚ እንዲታወቅ ሪፖርት ማድረግ፣ ህዝቡን ለተቀናጀ ትግል ማነሳሳት ነው፡፡ ህዝብን ከፖለቲካዊ በደል የሚታደገው የዘውግ ብሄርተኝነት ማደግ ሳይሆን የዲሞክራሲ ስርዓት መገንባት ብቻ ነው!
ወደ ቀደመ ጉዳያችን ስንመለስ የአማራ ብሄርተኝነት እንዳያድግ እንቅፋት የሆነው የህወሃት ክርን ነው፡፡ይህ የህወሃት ክርን ለምን አስፈለገ ስንል ሁለት ምክንያት ይኖረዋል፡፡ የመጀመሪያውና ዋነኛው የአማራ ብሄርተኝነት ካደገ ህወሃት መወጣጫ አድርጎት ወደ ስልጣን የመጣበትን መሰላል ስለሚያነሳ ነው፡፡ ያ መሰላል አማራን እየወቀሱ፣ እንዳይመለስባችሁ የምጠብቃችሁ እኔ ነኝ እያሉ ከሌሎች ብሄርሰቦችን የታዳጊነት እምነት አግኝቶ ስልጣን ላይ መቀመጥ ነው፡፡ ሁለተኛው ጉዳይ የአማራ ብሄርተኝነት ካደገ በአማራው ላይ እየተደፈደፈ ያለውን ለሁሉም የሃገሪቱ ችግር መነሾ የመደረግ የጥፋተኝነት ዳፋ ሃሰትነት ለማስረዳት መነሳቱ፣ በሃሪቱ ዳርቻ በአማራው ላይ የሚደረገወውን ግፍ ነቅሶ አውጥቶ ማሳወቁ አይቀርም፡፡"