Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
AbebeB
Member+
Posts: 7694
Joined: 15 Oct 2016, 10:31

@Oromia: አፋን ኦሮሞ የፌደራል የሥራ ቋንቋ እንዳይሆን ሕገ-መንግስቱ አይከለክልም፡፡ ስለዚህ ሕገ-መንግስቱን ማሻሻል ሳያስፈልግ አፋን ኦሮሞ የፌደራል የሥራ ቋንቋ ማድረግ ይቻላል፡፡

Post by AbebeB » 28 Aug 2019, 15:58

አማርኞች አፋን ኦሮሞን የፌደራል የሥራ ቋንቋ ለማድረግ ሕገ-መንግስቱ መሻሻል አለበት በማለት በግርግር ውስጥ አንድ ዳቦ ጠፋ ለመጫወት ይጥራሉ፡፡ እውነቱ ግን ሕገ-መንግስቱ አማርኛን ደነገገ እንጂ አፋን ኦሮሞን አልተቃወመም፡፡

ስለዚህ እንደ አስቸኳይነቱ መጠን ሕገ-መንግስት ማሻሻል ገለ-መሌ ሳንል አፋን ኦሮሞ የፌዴራል የሥራ ቋንቋ መሆኑን ማወጅ ብቻ ነው፡፡ ያውም ለኢትዮጵያ አፍቃሪዎች ሲባል እንጅ ይህ የኦሮሞን ሕዝብ ብዙም አያስጨንቀውም፡፡ ይልቁንስ ወደ ዋናው ግባችን እንድንጣደፍ ያግዘናል፡፡