Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11363
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

ሂውማን ራይትስ ዎች፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ቀደም ሲል ለተፈጸሙ እና ባሁኑ ወቅት እየተፈጸሙ ለሚገኙ ጥሠቶች ተጠያቂነትን ማስፈን ፈተና ሆኖ መቀጠሉን ገለጠ

Post by MINILIK SALSAWI » 06 Feb 2026, 14:23

ሂውማን ራይትስ ዎች፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ቀደም ሲል ለተፈጸሙ እና ባሁኑ ወቅት እየተፈጸሙ ለሚገኙ ጥሠቶች ተጠያቂነትን ማስፈን ፈተና ሆኖ መቀጠሉን ገለጠ። ድርጅቱ የአውሮፓዊያኑን 2025 የዓለም ሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ አስመልክቶ ትናንት ባወጣው ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ ለጥሠቶች ተጠያቂነት እንዲሠፍን ዓለማቀፍና አገር ዓቀፍ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ገልጧል። ድርጅቱ፣ ባለፈው የአውሮፓዊያን ዓመት በአገሪቱ በርካታ አካባቢዎች ሲቪሎች የሰብዓዊ፣ የጸጥታና ሰብዓዊ መብት ቀውሶች ተጋርጠውባቸው እንደቆዩ ጠቅሷል። የአገሪቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ምኅዳር ይበልጥ መጥበቡን፣ ባለሥልጣናት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችንና ጋዜጠኞችን ማስፈራራታቸውንና ማንገላታታቸውን እንዲሁም የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማኅበርንና በርካታ ሲቪል ማኅበራትን ማገዳቸውን የጠቀሠው ድርጅቱ፣ የኢኪኖሚና ማኅበራዊ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ማሽቆልቆሉንም አውስቷል። በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ግጭቶች መቀጠላቸውን ድርጅቱ የጠቀሠ ሲሆን፣ በተለይ በአማራ ክልል በድሮን በተፈጸሙ ጥቃቶች ሲቪሎች ተገድለዋል ብሏል።


















Post Reply