ኤርትራ .. በኢትዮጵያ ቀውስ ምክንያት በቀጣይ ምን ይገጥማት ይሆን ?sarcasm wrote: ↑08 Jan 2022, 19:30
I watched Isaias's interview and he is still in his ክተት mood and he will not support Abiy's reconciliation with Tigray. That means Abiy cannot reconcile with Tigray and continue the በአንድ ቂጥ እንራ close relationship with Isaias. Gimbot 7 and Isaias cannot let Abiy to go for a reconciliation with Tigray. That means if Abiy want to go on the path of peace with Tigray, the alliance has to be broken.
Finfinne Times
አሜሪካንን ክፉኛ አብጠልጥለው ቻይናን ያነገሱት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትግራይ ክልል ላይ ተጨማሪ የጦርነት ትንኮሳ እያደረጉ እንደሆነ የTDF ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስታውቀዋል። እንግዲህ ውጥረቱ ቦታ ቦታውን እየያዘ የመጣ ይመስላል።
"የኢትዮጵያ ጦር ከመቀሌ ይወጣል ብለን አልጠበቅንም ነበር" ... በኢትዮጵያ መንግስት የሚወሰነው ማንኛውም ፖለቲካዊ ጉዳዮች ኤርትራ ላይ ተፅዕኖ እንደሚኖው ያስታወሱት ወዲ አፎም .. የሰሞኑ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደትንም እንደሚከታተሉትም ተናግረዋል።
በእርግጥ ከብልፅግና ጋር ያላቸው ግንኙነት ጥሩ እንደሆነና ለወደፊቱ እንደሚጠናከር ቢገልፁም ንግግራቸው ግን ከዲፕሎማሲ አንፃር የተቃኘ ነው። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የአብይና የኢሱ ፍቅርን ለመግለጽ አስቸጋሪ ነው።
ጠ/ሚ አብይ አህመድ በምዕራባዊያንና በአሜሪካን ጫና ብሎም በመላው ሀገሪቱ በጦርነቱ ሳቢያ በደረሰው አጠቃላይ ውድመት ተፅዕኖ ወደውም ሆነ ተገደው ሰላማዊ አማራጮች ላይ አተኩረዋል። ይህ ውሳኔ በወዲ አፎም በፍፁም አይወደድም።
ከTDF ጋር ብልፅግና የሚደራደር ከሆነ ከኤርትራ ጋር የሚኖረው ቀጣይ ግንኙነት ሊደበዝዝና ከነአካቴው ሊቋረጥ ይችላል። ይህም የኤርትራና የትግራይ ጉዳይ በጦርነት በድንበር በደም ስለጨቀየ ወይም በቀላሉ ሊቀረፍ በማይችል ቀውስ ስላለፈ ነገርዬውን ያከረዋል። በዚህ ቀውስ ላይ የፌደራሉ መንግስት ሚናን የነበረው አስተዋጽኦን አረሳነውም።
ስለዚህ የፌደራሉ መንግስት ከTDF ጋር በአስገዳጅ ጫናዎች ለመደራደር ቢያስብ እንኳን ከኤርትራ ጋር ያለው ግንኙነትን ማጤን ግዴታው ነው።
ዘላቂ መፍትሔ ደግሞ ለማምጣት የፌደራሉ መንግስት የኢትዮጵያን ሉአላዊነትን በየትኛውም መንገድ ማስከበር ብሎም ከTDF ጋር በሚኖረው ቅድመ ድርድር ሂደት በፊት ከአማራ ክልልና ከኤርትራ ጋር ያለውን ስስ ቀውሶች መፍታት አለበት።
ከአማራ ክልል ጋር ተያይዞ ምዕራብ ትግራይን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። ኤርትራስ ..?? አሜሪካን የኤርትራ ሰራዊት ከትግራይ መሬት እንዲወጡ በተደጋጋሚ አሳስባለች። ጠ/ሚ አብይ አህመድ ደግሞ በሰሞኑ ውሳኔያቸው ላይ የአሜሪካን ተፅዕኖ በግልፅ እየታየ ነው።
ኤርትራ ደግሞ ወታደሮቿን በተጨማሪ ትግራይ ላይ እያሰፈረች ነው። ትንኮሳዎችንም እያደረገች ነው። TDF የትግራይ ህዝብን ደህንነትና ጥቅም ለማስከበር የትኛውንም አማራጭ መከተሉ አይቀርም።
ነገር ግን በተጨማሪነት በድርድሩ ቅድመ ሁኔታ ላይ የትግራይ ክልል ህጋዊ ግዛቶች መከበር አለባቸው። ይህንን ደግሞ ማስከበር ያለበት የፌደራሉ መንግስት ነው። ዘላቂ የሚሆነውም በሿሿም ሆነ በጓጓ ኢትዮጵያን እንድመራ ሉአላዊነቷን እንዳስከብር ስልጣን በምርጫ አግኝቻለሁ የሚለው ብልፅግና መሆን አለበት።
ውስጣዊ የፖለቲካ ቀውሱን በሰላማዊ ድርድር ለመፍታት ስላሰብኩ የኤርትራ መንግስት ትግራይን ለቆ እንዲወጣ ብሎም ማንኛውንም ትንኮሳ ማቆም እንዳለበት ማሳሰብ የአባት ነው። ቀውሱ ካልተቀረፈ ደግሞ ህግ ማስከበር ከሀገሪቱ ሉአላዊ ጥቅም አንፃር ትክክል ነው።
ሳጠቃልለው የኤርትራ ሰሞናዊ የቻይና ወዳጅነት መጠንከር ፥ በመሪዎች ደረጃ ብቻ መሰረቱን የሰራው የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነት መቀዝቀዝ ፥ የፌደራሉ መንግስት የጦርነት ቀውሱን በድርድር ለመፍታት ማሰብ ፥
አሜሪካን በኢትዮጵያ ተፅዕኖዋና ሚናዋ እየጎላ መምጣት ፥ የኤርትራ ትንኮሳ በትግራይ ክልል ላይ መጨመር ... የመሳሰሉትን አበይት ጉዳዮችን ስንገጠጥማቸው ጦርነቱ በቀጣይ በሀገራት መካከል ሊሆን እንደሚችል ይጠቁመናል።
ዘመቻ አዲመራ ወደ አስመራ በቀጣይ ይኖር ይሆን ?? አሜሪካን በኤርትራ ላይ ያላትን የረጅም አመታት ፖሊሲንም መርሳት የለብንም።
Finfinne Times
https://www.facebook.com/permalink.php? ... 1731586155


