Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15366
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

በጄርመን ከተማ እንዳያ በአፍላው ዘመን - እንዳልሸለለባት፤ ዐብይ አህመድ አሊ ዛሬ ተጨንቆ ዋለባት አንገቱን - በመድፋት ከሰው አነሰባት።

Post by Abere » 21 Nov 2023, 11:03

በጄርመን ከተማ እንዳያ በአፍላው ዘመን - እንዳልሸለለባት፤
ዐብይ አህመድ አሊ ዛሬ ተጨንቆ ዋለባት፤
አንገቱን - በመድፋት ከሰው አነሰባት።

ምነው ውሃ በሆንኩ - ምነው ባልተፈጠርኩ እያለ በሆዱ፥
ከፍ ከፍ ብሎ ወርዶ ተንኮታኩቶ አንሶ መዋረዱ።

አማራ ተራራ መሆኑን ረስቶ፥
ከተራራ ጋር ተላትሞ ተጋጭቶ፥
በዓለም አደባባይ አረጉት እንኩቶ።

በእግዜር ስር መግባት አይሁንብኝ እንጅ፥
የአብይ አህመድ አይነት አይወለድ ልጅ።

እንትፍ ፕሬዚደት፤ እንትፍ ጠ/ሚንስትር፤
በአፍንጫዬ ይውጣ ፤ የሚልዮን ፍጥረት ደም በእጄ ከሚቆጠር።

የዝች ጠባብ ጎጆ ምድር የምትባል - ድንኳን ናት ታልፋለች፤
የትልቁን እልፍኝ አዳራሽ በር ቁልፍ ካስጣለች፥
እምቢ አልወለድ ሚንስትር አልሆንም ንጹህ ነፍስ ትላለች።

በኦሮሙማ ዛር ፈረስ ከንቱ ከከነፈች፥
የአጋንንት ቆሪጥን የጨለማ ካባ ደፍራ ከደረበች፤
በደም ጎርፍ አባል ቀልታ ከጨቀየች፥
ለሰው በፈጣሪ እጅግ ከቀፈፈች፥
በምድር በሰማይ ዘለአለም እርጉም ነች።

እምቢ አልወለድም ዐብይን አልሆንም፥
ሚልዮን በመግደል በምድር በሰማይ ነፍሴን አልበድልም።

እንደ ቸርነትህ እንደ አበሳችን አይሁን - እያልን ስንማጸን፤
የከፋውን ወንጀል -የሄሮድሱን አይነት - እግዜር አታሳየን።

አማራዋ ራሄል እግዜር እየሰማት፤
ፈርዖን አብይን የሚቀጣ ፋኖን ፈጥኖ ሰደደላት።