Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Selam/
Senior Member
Posts: 17891
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

የነ አሪዮስ መጨረሻ አላማ ምንድነው?

Post by Selam/ » 08 Feb 2023, 06:57

በቋንቋችን ለመናገር የራሳችን ዻዻስ ያስፈልገናል የሚባለው የኦነግ-ሸኔ ክርክር ውሃ የማይቋጥር ማጨናበሪያ ነው።

አገልግሎት በተለያየ ቋንቋ እየተሰጠ ነው። ግን ባይሰጥ እንኳን ምዕመናኑ አሻፈረኝ ብሎ ቤተ-ክርስቲያኑን ይክዳው፣ መባ ይንሳውና ባለመሳተፍ አቅም ያሳጣው እንጂ፣ የኦነግ-ሸኔ ካድሬ ምናባቱ አግብቶት ነው ቤተ ክርስቲያን አሰራር ውስጥ የሚፈተፍተው? ነገ ቁርዐን በአፋን ኦሮሞ ካልተቀራ ሊሉ ነው ማለት ነው?

ዋና አላማቸው ግን እርቶዶክስንና በአጠቃላይ ክርስትናን ማፍረስ ነው። ዻዻስ ለመሆን 20-30 ዓመት አፈር ልሰው መማር ሲገባቸው፣ የመንደር ጎረምሶችን ቆብ አልብሰው አቀሰሷቸው። እነዚህ ሰካራሞች በየቤተክርስቲያኑ እየሄዱ የተሳሳተ ትምህርት እንዲያስተምሩና ምዕመናኑን አስመርረው ቤተመቅደሱን ለማዘጋትና ህገ አራዊነትን ለማስፋፋት ነው የሰለጠኑት። በቃ ይኸው ነው!


Post Reply