kibramlak wrote: ↑16 Nov 2022, 04:57
ሰላም አሰገድ
ትላንት ይህች ሊንክ ላይ ኮመንት ሳደርግ (
https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=309335 ) በሰውየው የተለመደ ክብር ቢስ እና ፀያፍ አመላለሶች ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ የውሸታምነቱን ጥግ ማማ ላይ የሰቀለበት ላለመናገር ባደረገው ንግግር ነበር ሲያላዝን የቆየው፣፣ የወልቃይትን እና የአዲስ አበባን ጉዳይ አድበስብሶ ለማለፍ የተጠቀመበት አነጋገር በጣም ውርጋጥ እና ብስለት የሌለው መንደረኛ ንግግሩን ያስተጋባበት ክስተት ነበር፣፣ እኔ ሳጠቃለው ከትህነግ ጋር በኦነጋዊነቱ ካደረጋቸው ስምምነቶች ውስጥ ዋነኛዎቹ ሁለት ነገሮች ናቸው፣-
1) የጎን ውጋት የሆነባቸውን ፋኖ ለማስወገድ
2) የወልቃይትን ጉዳይ አለባብሴ ወደ ትግራይ በማስመሰል ሁለቱ ህዝቦች የማያቋርጥ አተካራ በማስገባት
አብይ ፋኖን በጣም አምርሮ ሲጠላው፣ ትህንግ ፋኖን አምርሮ ይፈራል
እፕብይ የወልቃይት ጉዳይ ሲድበሰበስ ለኦሮሙማ እና ለሸኔ ቀጣይ ጉልበት ይፈትራል፣፣ ለትህነግ በዲፕሎማሱ ደረጃ face saving ምላሽ ይዞ በመሄድ ለቀጣይ ጦርነት መቀስቀሻ ይጠቀምባታል
እነዛ ስልብ ገረዶች (ብአዴኖችን) እርሳቸው፣፣
ሁሉም የትህነግ ውጤቶች ናቸው፣፣ ውሻ ባለቤቱን አይረሳም እንደሚባለው አብይም ሆነ ገርዶች ብአዴኖች ያደረጉት ቢኖር አሳዳጊ እና ባለቤታቸውን ባለመርሳት የሚያደርጉት ውለታ ነው፣፣
እንግዲህ መሬት ላይ የሚሆነውን ማየት ነው
የሰማሁት ትክክል መሆኑን ባላረጋግጥም አንድ ወንድሜ እንዳጫወተኝ ከሆነ ሽመልስ እና አብይ በጣም መጠነ ሰፊ የጦር መሳሪያ ክምችት ላይ እንደሆኑ (እስከ 40 አመት የሚያዋጋ) እና የዚሁ እቅድ ምክንያት ደግሞ ከአማራ ጋር የከረረ ጦርነት ይከፈትብናል የሚል ስጋት እና የያዝነውን ስልጣን የሚያስለቅቀን አማራው ነው ብለው ስለሚገምቱ፣፣ የፈሪ ዱላ እንደሚሉ እንግዲህ እነሱም በቁሳዊ ትጥቅ ማስተማመኛ ለመፍጠር ይሆናል
ሰላም Kibramlak, so good to read from you.
ኣንተ ባነሳሃቸው ሓሳቦች ላይ እኔም እስማማለሁ። የደቡብ-ኣፍሪካው ድርድር ... ፋኖን ትጥቅ የማስፈታትና ወልቃይትን ወደ ትግራይ ክልል የመመለስ ስምምነትን እንደሚያጠቃልል ምንም ጥያቄ የለውም። አንዳንዶች ግን … logic, as an art and science of reasoning, ከሚነገረውና ከሚፃፈው
ባሻገር እውነታን የመግለፅ አቅም እንዳለው ስለማያውቁ፥ እኛም እንደነርሱ ሁሉን ሓሳብ at face value ገዘተን እንድንቀመጥ ይፈልጋሉ።
ወልቃይትን በተመለከተ ሌላው አስገራሚው የጠቅላይ ሚንስትሩ ቃል፥ ያንን አካባቢ የኢትዮዽያ መከላከያ ሀይል ነፃ አውጥቶ ለኣማራው ያስረከበው ይመስል … “
ዘላለም እዛ ድንበር ላይ ወታደር ማቆም አንችልም” ብለው የኣማራውን ህዝብና ሀይል ያሳነሱበት ንግግር ነው። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ፣ ከፈረሱም ኣፍ እንደሰማሁት .. ያ ጦርነት በተከፈተበት ወቅት “
ቶሎ ቶሎ ጦርነቱን አጠናቀን ወደ ቅዬአችን እንመለስ፤ የእርሻ ስራ (አጨዳ) አለብን" ብለው ፋኖዎች ቢለምኑም እንኳ መንግሥት ፍቃደኛ ስላልነበረ … “
ዝም ብለን እየበላን አንቀመጥም” ያሉ ፋኖዎች ጦርነቱን በራሳቸው ትጥቅ ጀምረው እየገፉ ሲሄዱ ነው የመንግስት (የኣማራ ልዩ ) ሀይል ቦኃላ ደርሶ የከባድ መሣሪያ ሽፋን የሰጣቸው። ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ …
ኣማራና የኣማራ ሀይል እራሱንና የራሱ የሆነውን ለመከላከል ኣቅመ-ቢስ እንደሆነ አድርጎ መሳል ስህተት ነው።
ሌላው, Kibramlak,
መሬት ላይ ካለው ሁኔታ በመነሳት ኣማራን ለማጥቃት የኦሮሚያ ክልል (መንግስት) ስውር ወታደራዊ ዝግጅት የሚጠበቅ ነው። የኣደረጃጀቱን መጠንና ጥልቀት ለመገመት የሚያስችል information ባይኖረኝም፥ እነ አቶ አባ ዱላ ገመዳ እንደሚሉት ከፖለቲካ “
ጡረታ” ወጥተው፣ ከማማከሩና ከማደራጀቱ ተግባር እራሳቸውን አግልለዋል ብዬ አላምንም። ከዚህም በተጨማሪ ግን … በግልፅ ከሚታየው መንግስት ሌላ
በመንግስት ቅርፅና ኣቅም የተደራጀ ሌላ የበላይ መንግስት ኢትዮዽያ ውስጥ እንዳለ ይሰማኛል። በየመስሪያ ቤቶቹ … በተለይም የፀጥታና የውጭ ግንኙነት ተቋማትን በስውር የሚሰልል ህቡዕ የሆነ ፣ ያልተበረዘና ያልተከለሰ ኦህዴዳዊ ኣካል አለ። አቶ ተመስገን ጥሩነህም ሆኑ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ … ተቀዳሚው ጠቅላይ ሚንስትር በግል በሚያዙት በሌላ ኣካል ራዳር ውስጥ ናቸው።
ይህ የሰላም ስምምነት እስከየት ድረስ ይጓዛል ለሚለው … አንተ እንዳልከው በሰዓቱ ማየት ነው። እኔ ግን ብዙም ሳንርቅ ወደ ነበርንበት እንደምንመለስ ጥርጥር የለኝም። ጠቅላይ ሚንስትሩ ሁለት ምርጫ አላቸው፦ ህወሃትን ለጊዜውም ቢሆን ለማሳደብ
ኣማራ ላይ ኣዲስ ጦርነት መክፈት ወይንም pause mode ላይ ያለውን የህወሃት ጦርነት በግዳጅ ማስቀጠል። በዚህም ሆነ በዚያ ግን ሁላችንም በኣንድ ነገር ላይ እርግጠኞች ነን … እጅግ በጣም የሚከብደው
በጦርነት ውስጥ ያለን ሰው ሳይሆን
በሰው ውስጥ ያለን ልብ ማሸነፍ እንደሆነ።
ወንድና ሴት ልጆቹ ወጥተው ያልተመለሱበት ቤተሰብ በሚኖሩበት ክልል፣ ለቁጥር አታካች የሆነ ወጣት አካለ-ጎዶሎ ሆኖ በተቀመጠበት ክልል፣ Multi party የምርጫ ሥርዓት እንዲያካሂድ የሚጠበቅ አምባገነናዊ አስተዳደር ባለበት ክልል፣ በአጠቃላይ ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል የእውነትም ሆነ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ የተበከለ አየር ለዘመናት ሲተነፍስ የኖረ ክልል … ኣንድ ወረቀት ላይ ለሰፈረ ፊደል ቃል ኪዳን ያስራል ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው።
በመጨረሻም, Kibramlak, በትላንትናው ጽሑፍህ ላይ "
ሶስቱ የኢትዮጵያ ጠላቶች (ኦነግ፣ ትህነግ እና ጴንጤ)" ያልከውን ተመልክቼ፥ እኔንም ጎሰም ብታደርገኝም "
ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተውቀጥ" በማለት በፈገግታ አልፌያታለሁ
መልካም ሳምንት ይሁንልህ, ወንድም Kibramlak