Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42875
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

6 አይነት የካልቸር በሽታዎችና 4ቱ የካልቸር ኳሊቲ መለኪያዎች!

Post by Horus » 20 Oct 2022, 00:09

ደራሲና ፈላስፋ አለማየሁ ገላጋይ በዋሊያ የደራሲያን ፎረም ላይ ስላቀረበው ትችት በጁን 16 2022 እዚህ ፎረም ላይ ፖስት ያደረኩት

አለማየሁ ገላጋይ እንደነ ዶስኪዮቭስኪ ኒሂሊስት ቢሆንም ብዙ ሃሳቦቹ ይመቹኛል ። ሃይማኖት የስራ ጠላት ነው፤ የእድገት፣ የስልጣኔ ጠላት ነው።

እኔ ሆረስ ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ደሞ ስነምግባር ነው፤ ስራ ነው ብዬ ነበር። አለማየሁ በቀጥታ የሚለው ያንን ነው።

የኢትዮጵያ ችግር የስራ ስነምግባር (work ethic) ችግር ነው። ለእኔ አግዚአብሄር ማለት፣ ፈጣሪ ማለት የሥራ፣ የፈጠራ፣ የጥበብ፣ የፍልስፍና አምላክ እንጂ የሰነፎች የሰማይ የምድር መቀባጠር አይደለም።

ፈጣሪ ጥበብ ነው፣ እውቀት ነው፣ ብርሃን ነው፣ መንገድ ነው ። እግዚአብሄር የስራ አምላክ ነው።

አለማየሁ ስድስት (6) የኢትዮጵያ ጠላቶች ያላቸውን ዘርዝሯል።

(1) ሌቦች፣ ሰው የሰራውን ። ጎሬላ በለው፣ ሽፍታ በለው፣ ኪስ አውላቂ በለው፣ ነጻ አውጪ በለው ያልሰራውን የሚቀማ ሌባ ነው ።

(2) ውሸታሞች፣ አታላዮች፣ አጭበርባሪዎ፣ ፌክ ታሪክና ወሬ ፈልፋዮች፣ የውሸት እግዚአብሄሮች፣ ጠንቋዮች፣ ሰባኪዎች፣ ባንድ ቃል በውሸት የሚኖሩ ከሌቦች የማይለዩ የህዝብ ጠላቶች።

(3) ለማኞች፣ ሙሉ አካል እያላቸው ሰው የሰራውን በመለመን፣ በሰው እጅ የሚኖሩ፣ ለስብዕናቸው ክብር የሌላቸው ከውሻ ያልተለዩ፣ እንደ ውሻ ምግብ ከጌታቸው ከመጋቢያቸው በመለመን የሚኖሩ ወራዶች።

(4) ሴተኛ አዳሪዎች፣ እራሳቸውን፣ ስብ ዕናቸውን የሚሸጡ ከእንስሳ በታችህ የሆኑ።

(5) ሰነፎች፣ በሕይወታቸው አላማና ትርጉም የሌላቸው፣ በዘመድ፣ በዲያስፖራ እርዳታና ሬሚታንስ የሚኖሩ ስራ ጠል መንጋዎች።

(6) የማያስቡ፣ ባይምሮአቸው ጠቃሚ ሃሳብ፣ አዲስ ሃሳብ፣ አዲስ እምነት፣ አዲስ ራዕይ፣ አዲስ ነገር ማየት የማይችሉ ለዘመነ ዘመናት በአንድ የህላዌ በረት ውስጥ የታሰሩ በድንቁርና ከርቸሌ ውስጥ የሚማቅቁ የሰው አካል ያላቸው እንሰሶች ናቸው ይላል።

አው ሌሎች ሰዎች ከነዚህም የተለዩ ማህበራዊ ደዌዎችን ሊጠቅሱ እንደ ሚችሉ አምናለሁ ።

ሌላው ቀርቶ እነዚህ 6 ግዙፍ የበሰበሰ ካልቸር ጉድፎችን ብናጸዳ እንኳ የትና የት በደረሰን!!!

ዛሬ ሃይማኖቶች ሁሉ የነዚህ ቆሻሻ ባህሎች መደበቂያ ናቸው ። ልክ የጎሳ ፖለቲካ የነዚህ ቆሻሻ ባህሎች መሸሸጊያ ዋሻ እንደ ሆነ ሁሉ!!!
Last edited by Horus on 20 Oct 2022, 00:58, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 42875
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 6 አይነት የካልቸር በሽታዎች

Post by Horus » 20 Oct 2022, 00:54

የሰው ልጆች በፍጥረትና ቁስ አካላዊ ውልደታቸው እኩል ናቸው፣ በካልቸር ግለሰቦችም ሆነ ማህበረሰብ በካልቸር እኩል አይደሉም፣ አንድ አይነት አይደሉም። ካልቸር ፍጥረት ሳይሆን ስራ ነው ። ካልቸር ማለት ሰው ሰራሽ ማለት ነው ። በስራ ግለሰቦችም ማህበረሰቦች የተለያዩ ናቸው፣ አንዱ ካንዱ ያንሳል፣ አንዱ ካንዱ ይበልጣል ። ሰው ሁሉ በስራው እኩል ነው የሚሉ የማይሰሩ ሰነፎችና የካልቸር ምንነት ያልገባቸው መሃይሞች ናቸው ።

ሁለት ካልቸሮች ወስደን የቱ ነው ጥሩ ካልቸር፣ የቱ ነው መጥፎ ካልቸር ተብለው የሚመዘኑበት 4 መለኪያ መስፈርቶች አሉ ።

አንድ፣
አዲስ፣ የሌለ፣ ያልነበረ፣ የልተለመደ ነገር፣ ሃሳብ፣ ዘዴ፣ እውቀትና ኤክኖሎጂ የሚፈጥር ካልቸርና ለዘመነ ዘመናት ባለበት የደነዘዘ ካልቸር ፤ ፈጣሪ ካልቸርና በድን ካልቸር!

ሁለት፣
ታዳጊ፣ የሚያድግ፣ ዴቨለፕ የሚያደርግ፣ የሚሻሻል፣ ነገሮችን የሚያሻሽል፣ የሚጨምር፣ የሚማር ካልቸርና የማይሻሻል፣ የማያድግ፣ የማይበልጽግ፣ የጫጨ፣ ድሃ፣ የቆረቆዘ ካልቸር፤

ሶስት፣
በተፈጥሮና ታሪክ የተሰጠውን፣ የተረከበውን ጸጋ መልካም ነገር ሁሉ የሚጠብቅ፣ የሚያክብር፣ የሚንከባከብ ሪስፖሲብል ካልቸርና ከተፈጥሮ የተጣላ፣ አደራ የተሰጠውን ታሪክና ምድር የሚያወድም ገዋ፣ ደደብ፣ ካልቸር ፤

አራት፣
አንድ ነገር ሲያረጅ፣ ሲበላሽ፣ ግዜው ሲያልፍ፣ ጥቅሙ ሲያበቃ የሚለውጥ፣ መጥፎ ባህልን በጥሩ የመለወጥ ችሎታና ፈቃድ ያለው ካልቸርና መለወጥ የማየልግ፣ የማይችል፣ ድንዝዝ፣ ዝግ፣ ግብዝ ካልቸር ናቸው ።

የየትኛውም ሕዝብ ካልቸር ከሌላ ሕዝብ ካልቸር ጋር አነጣጥሮ የቱ ካልቸር ይሻላል፣ የቱ ካልቸር አይሻልም ተብሎ የሚለኩት በነዚህ አራት ዩኢቨርሳል መመዘኛዎች ነው ።

የቀረው ሁሉ ስለዚህ ጉዳት ምንም እውቀት የሌላቸው ሰዎች የራሳቸውን ጭፍን ስሜት ለህዝብ የሚያቀርቡበት ድራማ ነው ። አንድ ነገር በቃላት ተጽፎ ለፓፕሊክ ስለቀረበ ብቻ ዋጋ አለው ማለት አይደለም ። እልፍ አዕላፍ ፋይዳ ቢስ ሃሳቦች በቃላት ተቀርጸው ሚዲያ ላይ ይወጣሉና!

Selam/
Senior Member
Posts: 17918
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: 6 አይነት የካልቸር በሽታዎችና 4ቱ የካልቸር ኳሊቲ መለኪያዎች!

Post by Selam/ » 20 Oct 2022, 09:00

ሽሜው - ይኸ ሁሉ ዙሪያ ጥምጥም፣ የአንተን በሹካ መብላት ከሌላው በጣት መብላት የተሻለ ነው ብለህ የዘባረቅከውን ምክንያት ለመስጠት ነው። አይ! ውሸት ነው፣ ማጨናበር ነው፣ የአንተ የድንቁርና ምልክት ነው አልኩህ።

በጣቱ ይበላል ብለህ የምትንቀው ህብረተሰብ፣ ብረት ቀጥቅጦ፣ ሸክላ ቀርፆ፣ እንጨት ፍቆ፣ ለመኖር የሚያስፈልገውን የቤት ቁሳቁስ እየሰራ ለዘመናት ኖሯል። በምን ፋይዳ ያንተ በሹካ መብላት ከነሱ በሽክና ከመጠጣት፣ በእርቦ ከመብላት ከፍተኛ እንደሚያረገው አንተ ቅራቅንቦው ብቻ ነህ የምታውቀው።

ደግሞ ለሌብነት፣ ለሴሰኝነትና ለውሸት መንስዔው ሃይማኖት ነው ያለው የትኛው ድፍን ነው? ከአህዛብ ምዕራብያውያን የበለጠ አጭበርባሪ፣ ሸርሙጣና ሌባ አለ እንዴ? አፍሪካን የመዘበሩት ፣ ሃይማኖትንም ለዝርፊያ መጠቀሚያ ያደረጉት ፣ የኢትዮዽያን የሃሰት ነቢያት ያመጡብን እኮ እነሱ ሃይማኖተ-ቢሶቹ ናቸው።

ለኢትዮዽያ ኋላ ቀርነት ዋና ምክንያቶች ታች ያሉ ድሃ ህዝቦች ሳይሆኑ፣ እንዳንተ ያሉ ስራ ፈትና ራስ ወዳድ ልሂቃኖች ናቸው። ህብረተሰቦችን ከማቀራረብና ልምድንና ባህልን ከማወራረስ ይልቅ ማበላለጥና ማበጣበጥ ስለምትመርጡ ፤ ለምዕራብ ባህል ስለምታጎበድዱ ፤ ሰማይ ተንጠልጥላችሁ ወሬ ከማውራትና ነገር ከመሰንጠቅ ባሻገር መሬት ወርዳችሁ ስለማትሰሩ ፤ ትምክህተኛ፣ ምቀኛና ስግብግብ ስለሆናችሁ ነው። እንዲሁም ህዝቦች ለዘመናት ያዳበሩትን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ የህክምናና የእርሻ ጥበብ ፈልፍሎ አውጥቶ አቀናጅቶ ከማሳደግ ይልቅ፣ ሁሉንም ነገር እንደወረደ በአቋራጭ ከሌላ ሀገር ማምጣትን ስለምትመርጡ ነው።

ብቻውን ፍልስፍናማ ቢወቅጡት እምቦጭ እንደሆነ በታናሽ ወንድምህ ዶር ዳኛቸው አየነው።
Horus wrote:
20 Oct 2022, 00:09
ደራሲና ፈላስፋ አለማየሁ ገላጋይ በዋሊያ የደራሲያን ፎረም ላይ ስላቀረበው ትችት በጁን 16 2022 እዚህ ፎረም ላይ ፖስት ያደረኩት

አለማየሁ ገላጋይ እንደነ ዶስኪዮቭስኪ ኒሂሊስት ቢሆንም ብዙ ሃሳቦቹ ይመቹኛል ። ሃይማኖት የስራ ጠላት ነው፤ የእድገት፣ የስልጣኔ ጠላት ነው።

እኔ ሆረስ ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ደሞ ስነምግባር ነው፤ ስራ ነው ብዬ ነበር። አለማየሁ በቀጥታ የሚለው ያንን ነው።

የኢትዮጵያ ችግር የስራ ስነምግባር (work ethic) ችግር ነው። ለእኔ አግዚአብሄር ማለት፣ ፈጣሪ ማለት የሥራ፣ የፈጠራ፣ የጥበብ፣ የፍልስፍና አምላክ እንጂ የሰነፎች የሰማይ የምድር መቀባጠር አይደለም።

ፈጣሪ ጥበብ ነው፣ እውቀት ነው፣ ብርሃን ነው፣ መንገድ ነው ። እግዚአብሄር የስራ አምላክ ነው።

አለማየሁ ስድስት (6) የኢትዮጵያ ጠላቶች ያላቸውን ዘርዝሯል።

(1) ሌቦች፣ ሰው የሰራውን ። ጎሬላ በለው፣ ሽፍታ በለው፣ ኪስ አውላቂ በለው፣ ነጻ አውጪ በለው ያልሰራውን የሚቀማ ሌባ ነው ።

(2) ውሸታሞች፣ አታላዮች፣ አጭበርባሪዎ፣ ፌክ ታሪክና ወሬ ፈልፋዮች፣ የውሸት እግዚአብሄሮች፣ ጠንቋዮች፣ ሰባኪዎች፣ ባንድ ቃል በውሸት የሚኖሩ ከሌቦች የማይለዩ የህዝብ ጠላቶች።

(3) ለማኞች፣ ሙሉ አካል እያላቸው ሰው የሰራውን በመለመን፣ በሰው እጅ የሚኖሩ፣ ለስብዕናቸው ክብር የሌላቸው ከውሻ ያልተለዩ፣ እንደ ውሻ ምግብ ከጌታቸው ከመጋቢያቸው በመለመን የሚኖሩ ወራዶች።

(4) ሴተኛ አዳሪዎች፣ እራሳቸውን፣ ስብ ዕናቸውን የሚሸጡ ከእንስሳ በታችህ የሆኑ።

(5) ሰነፎች፣ በሕይወታቸው አላማና ትርጉም የሌላቸው፣ በዘመድ፣ በዲያስፖራ እርዳታና ሬሚታንስ የሚኖሩ ስራ ጠል መንጋዎች።

(6) የማያስቡ፣ ባይምሮአቸው ጠቃሚ ሃሳብ፣ አዲስ ሃሳብ፣ አዲስ እምነት፣ አዲስ ራዕይ፣ አዲስ ነገር ማየት የማይችሉ ለዘመነ ዘመናት በአንድ የህላዌ በረት ውስጥ የታሰሩ በድንቁርና ከርቸሌ ውስጥ የሚማቅቁ የሰው አካል ያላቸው እንሰሶች ናቸው ይላል።

አው ሌሎች ሰዎች ከነዚህም የተለዩ ማህበራዊ ደዌዎችን ሊጠቅሱ እንደ ሚችሉ አምናለሁ ።

ሌላው ቀርቶ እነዚህ 6 ግዙፍ የበሰበሰ ካልቸር ጉድፎችን ብናጸዳ እንኳ የትና የት በደረሰን!!!

ዛሬ ሃይማኖቶች ሁሉ የነዚህ ቆሻሻ ባህሎች መደበቂያ ናቸው ። ልክ የጎሳ ፖለቲካ የነዚህ ቆሻሻ ባህሎች መሸሸጊያ ዋሻ እንደ ሆነ ሁሉ!!!

Horus
Senior Member+
Posts: 42875
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 6 አይነት የካልቸር በሽታዎችና 4ቱ የካልቸር ኳሊቲ መለኪያዎች!

Post by Horus » 20 Oct 2022, 11:56

selam - አንተ ሹክሻክ ወናፍ!

Abere
Senior Member
Posts: 15468
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: 6 አይነት የካልቸር በሽታዎች

Post by Abere » 20 Oct 2022, 12:25

ሆረስ፥

እንደነኝህ አይነቶቹን የባህል ሳንካዎች ስትጠቅስ በጥቅሉ የሚያሳየው በአንድ ብሄራዊ የባህል (dominant culture) ጥላ ስር የሚገኙ ንዑስ ባህል (sub-culture)ነው።በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ለምሳሌ የወሮ በላ ወይም የአደንዛዥ ዕጽ (drug subculture) ተጠቃሚ ወይም የዝሙት አዳሪ፥የግበረሶዶም ወዘተ ንዑስ ባህል አለ። በእነርሱ(በቡድኑ) አስተያየት ጤናማ ባህል ነው ብለው ይከተሉታል ምክንያቱም ባህል አንድ የሚፈልጉትን ጥቅም ስለሚያስገኝላቸው። ያ መንገድ ግን ወጣ ያለ በመሆኑ የብዙሃኑን ይሁንታ ስለማያገኝ እንደ ጎጅ ተደርጎ ይወሰዳል።

ለምሳሌ የወሮ በላ ቡድን ሳይሰራ በአቋራጭ ሰርቆ ገንዘብ ያገኛል። ይህ መንግድ ህገ-ወጥ ነው። በአንጻሩ በኋላቀር ማህበረሰብ ደግሞ ሽፍትነት ነው። ሽፍትነት በትግራይ መተዳደያ ባህል ወይም ወግ ይመስላል። ሽፍታ ህግ አያውቅ፤ ፈሪሃ እግዜር የለው፥ ሰርቶ አይበላ፤ መዝረፍ፤ወዘተ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባህል (National Culture) ግን እንድህ አይነቱን አይፈቅድም። ባይፈቅድም ግን ውስልትና ይኖራል - መቀነስ ግን ይቻላል። እንደት ለሚለው እንደ ዘረ-መል ባህሉ የተሰራበትን ድር ላይ ያተኮረ ገንቢ አስተምህሮ እና ድርጊት በማከናወን - targeted action on select detrimental cultural traits. እነኝህ (traits) ሲቀየሩ ጎጅ የሆኑት ድርጊቶች እና አስተሳሰቦች ይጠፋሉ ወይም ይቀንሳሉ።

Horus wrote:
20 Oct 2022, 00:54
የሰው ልጆች በፍጥረትና ቁስ አካላዊ ውልደታቸው እኩል ናቸው፣ በካልቸር ግለሰቦችም ሆነ ማህበረሰብ በካልቸር እኩል አይደሉም፣ አንድ አይነት አይደሉም። ካልቸር ፍጥረት ሳይሆን ስራ ነው ። ካልቸር ማለት ሰው ሰራሽ ማለት ነው ። በስራ ግለሰቦችም ማህበረሰቦች የተለያዩ ናቸው፣ አንዱ ካንዱ ያንሳል፣ አንዱ ካንዱ ይበልጣል ። ሰው ሁሉ በስራው እኩል ነው የሚሉ የማይሰሩ ሰነፎችና የካልቸር ምንነት ያልገባቸው መሃይሞች ናቸው ።

ሁለት ካልቸሮች ወስደን የቱ ነው ጥሩ ካልቸር፣ የቱ ነው መጥፎ ካልቸር ተብለው የሚመዘኑበት 4 መለኪያ መስፈርቶች አሉ ።

አንድ፣
አዲስ፣ የሌለ፣ ያልነበረ፣ የልተለመደ ነገር፣ ሃሳብ፣ ዘዴ፣ እውቀትና ኤክኖሎጂ የሚፈጥር ካልቸርና ለዘመነ ዘመናት ባለበት የደነዘዘ ካልቸር ፤ ፈጣሪ ካልቸርና በድን ካልቸር!

ሁለት፣
ታዳጊ፣ የሚያድግ፣ ዴቨለፕ የሚያደርግ፣ የሚሻሻል፣ ነገሮችን የሚያሻሽል፣ የሚጨምር፣ የሚማር ካልቸርና የማይሻሻል፣ የማያድግ፣ የማይበልጽግ፣ የጫጨ፣ ድሃ፣ የቆረቆዘ ካልቸር፤

ሶስት፣
በተፈጥሮና ታሪክ የተሰጠውን፣ የተረከበውን ጸጋ መልካም ነገር ሁሉ የሚጠብቅ፣ የሚያክብር፣ የሚንከባከብ ሪስፖሲብል ካልቸርና ከተፈጥሮ የተጣላ፣ አደራ የተሰጠውን ታሪክና ምድር የሚያወድም ገዋ፣ ደደብ፣ ካልቸር ፤

አራት፣
አንድ ነገር ሲያረጅ፣ ሲበላሽ፣ ግዜው ሲያልፍ፣ ጥቅሙ ሲያበቃ የሚለውጥ፣ መጥፎ ባህልን በጥሩ የመለወጥ ችሎታና ፈቃድ ያለው ካልቸርና መለወጥ የማየልግ፣ የማይችል፣ ድንዝዝ፣ ዝግ፣ ግብዝ ካልቸር ናቸው ።

የየትኛውም ሕዝብ ካልቸር ከሌላ ሕዝብ ካልቸር ጋር አነጣጥሮ የቱ ካልቸር ይሻላል፣ የቱ ካልቸር አይሻልም ተብሎ የሚለኩት በነዚህ አራት ዩኢቨርሳል መመዘኛዎች ነው ።

የቀረው ሁሉ ስለዚህ ጉዳት ምንም እውቀት የሌላቸው ሰዎች የራሳቸውን ጭፍን ስሜት ለህዝብ የሚያቀርቡበት ድራማ ነው ። አንድ ነገር በቃላት ተጽፎ ለፓፕሊክ ስለቀረበ ብቻ ዋጋ አለው ማለት አይደለም ። እልፍ አዕላፍ ፋይዳ ቢስ ሃሳቦች በቃላት ተቀርጸው ሚዲያ ላይ ይወጣሉና!

Horus
Senior Member+
Posts: 42875
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 6 አይነት የካልቸር በሽታዎችና 4ቱ የካልቸር ኳሊቲ መለኪያዎች!

Post by Horus » 20 Oct 2022, 13:39

አበረ፣
በርግጥ በአንድ ብሄራዊ ካልቸር (ባህልና) በውስጡ ካሉ ንኡስ (አናሳ) ባህሎች መሃል ያለው ትስስር ምንድን ነው የሚለው ጥያቄ እጅግ ውስብስብ ነገር ነው ። በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ባለብዙ ጎሳዎች፣ ሃይማኖቶች እና መልካምድሮች አገር የቱ ነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ካልቸር? የተኞቹ ናቸው የዚህ ብሄራዊ ካልቸር ንኡስ አካላት? የሚለው ጥያቄ እስከ ዛሬ በውል ተመርምሮ ብሄራዊ ስምምነት የተደረሰበት ጉዳይ አይደለም ።

ነገር ግን በኔ ከብዙ አመታት ህሳቤ በኋላ የደረስኩበት መደምደሚያ ቢያንስ ማንኛውም ኢትዮጵያዊን ሊያስማማ የሚችሉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ካልቸር መሰረቶች አሉ ። እነሱም የሚከተሉት ናቸው ።

አንድ፣
ኢትዮጵያ የብዙ ሃይሞኖቶች አገር ናት፤ ማለት ህዝቧ በተለያዩ አይማኖቶች የተከፋፈለ ነው ። ነገር ግን ሁሉም የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች በአንድ ፈጣሪ ያምናሉ። ይህ አንዱ የብሄራዊ ካልቸር መቆሚያ መሰረት ነው ። ማንኛውም ካልቸር መቆሚያ እምነት ስለሚፈልግ ማለት ነው ።

ሁለት፣
ስለሆነም ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የዚህ አንድ ፈጣሪ ፍጡራን ስለሆኑ በሰባዊነት ወንድማማቾች ናቸው። ይህ የካልቸር መሰረት ሙሉ በሙሉ በመላው የኢትዮጵያ ግለሰቦች ውስጥ የሰረጸ ሳይኮሎጂ መሆኑን ያጠራጥራል ። ያገሪቱ ፖለቲካ ስርዓት በጎሳዎች ወንድማማችነት ሳይሆን ልዩነት ላይ ስለቆመ ይህ ዛሬ ላይ አከራካሪ ነጥብ ነው ። ነገር ግን አንድ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ካልቸር ይኖር ዘንድ የግድ ህዝቦችዋ ያንድ ፈጥሪ ልጆች የሆንን ወንድማማች ነን ብሎ ማመን አለበት ።

ሶስት፣
የኢትዮጵያ ሕዝብ በልዩ ልዩ ጎሳዎች፣ ቡድኖች፣ የተለያየ ብዛትና መሬት ስፋት ቢኖራቸውም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በአንድ ፈጣሪ የተፈጠረ እኩል ፍጡር ነው የሚለው ሌላው ቁልፍ የካልቸር መቆሚያ መሰረት ነው ። በዚህ የማያምን ህዝብ እኩልነትና ፍትሃዊነት ያለው ካልቸር ሊኖረው በፍጹም አይችልም ። ይህም ዛሬ ትልቅ ችግር ላይ ያለ መሰረት ነው ምክኛቱም የፖለቲካ ስርዓታችን በኢትዮጵያ ግለሰብ ዜጋ ልዕልናና እኩልነት ላይ የቆመ ሳይሆን በጎሳዎች ሃይልና ፉክክር ላይ የቆመ ሰለሆነ።

አራት፣
ስነ ምግባር ወይም ስነ ስራ (ወርክ ኤቲክ) ነው ። ካልቸር ማለት የሰው ልጅ በራሱ እጆች የፈጠረው አለም፣ ነገር ማለት ነው ። ካልቸር ቴክኖሎጂንም ጨምሮ የሰው እጅ፣ የእደ ጥበብ ውጤት ነው ። አለማችን በሁለት ይከፈላል፤ ተፈጥሮ ሰራሽ እና ሰው ሰራሽ ። ሰው ሰራሽ ማለት ካልቸር ማለት ነው ። ስለዚህ ስራ (ተግባር) የካልቸር እምብርት ነው ። ስነ ስራ፣ ስነ ተግባር፣ የስራ ሳይንስ፣ የተግባር ሳይንስ የሌለው ህዝብ ካልቸር አለው ለማለት አይቻልም። እምነት ወይም ሃሳብ ብቻውን ካልቸር አይሆንም። ካልቸር ሶሺያል ፕራክቲስ ነው ። ስለዚህ በስራ ክቡርነት ማመን ሌላው ግዴታ የካልቸር መቆሚያ መሰረት ነው ። ይህም ቢሆን ዛሬ ላይ ሙሉ በሙል የኢትዮጵያ ህዝብ ብሄራዊ እምነት መሆኑ ያጠራጥራል ።

በነዚህ አራት ቁልፍ ጥያቄዎች የተነሳ ነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ካልቸር የቱ ነው? ምን ይመስላል? ይዘቶቹ ምንድን ናቸው? ያሚሉት ጥያቄዎች መመለስ ያለብን ።

ከላይ ያሰፈርኳቸው አራት የካልቸር ኳሊቲ መለኪያዎች ለምንኛውም ካልቸር ፤ የቡድን፣ የጎሳ ፣ የድርጅት፣ የትልቅም የትንሽም ማህበረሰብ ካልቸር ለመለካት የሚሆኑ ናቸው። አንድ ልሁቅ ካልቸር ከንኡስ ካልቸር ጋር ከተጋጩ ከላይ ባሉት መሰረቶችና መለኪያዎች ላይ ሲለያዩና መስማማት ሲያቅታቸው ነው ማለት ነው ። ያ ሲሆን ነው የካልቸር ለውጥ የሚያስፈልገው ማለት ነው ። የካልቸር ለውጥ የእምነትም የተግባርም ለውጥ ይፈልጋል ።

Abere
Senior Member
Posts: 15468
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: 6 አይነት የካልቸር በሽታዎችና 4ቱ የካልቸር ኳሊቲ መለኪያዎች!

Post by Abere » 20 Oct 2022, 14:07

ሆረስ፤

እንደ ጠቀስከው ባህል እጅግ ውስብስብ ነው። ረቂቅም ቁሳዊም ነው። በማንኛውም ባህል ውስጥ ብዙ ከሌሎች ባህል ጋር የሚመሳሰሉ እንዳሉ ሁሉ የሚለያያቸውም እንድሁ ብዙ ነው። ታድያ ስለ አንድ አገር ሳንወሳ ያች አገር የእራሷ ከሌሎች አገራት ለየት የሚያደርጋት ብሄራዊ ባህል አላት። ይህ ብሄራዊ ባህል በፓለቲካ ወይም በመንግስት ጫና የመጣ ሳይሆን በሂደት ከሰዎች ማህበራዊ መስተጋብር ሳብያ የተወለደ፥ያደገ፥የዳበረ እና ከሞላ ጎደል ሁሉም ዜጋዎች የሚጋሩት ባህል ነው። አስተውል ይህ እንደ ነጻ ገበያ እጅ ሳይገባበት የተገኘ የጋራ ማንነት ነው ። The dominant national culture is born due to invisible hand in the cultural intercourse of the various social segments of a sovereign country over an extended years. When one says Ethiopia is a cultural mosaic it does not mean Ethiopia does not have a dominant national culture. It is true Ethiopia is a melting pot of different sub-cultures practiced yet there is national culture that salient to almost all. When I hear of people preserving this or that culture, they must have aware of culture is an evolving process, in a world where cultural contact is intense and increasing, the greater concern is not even so much preserving smaller sub-culture but is preserving dominants culture of a country given a global culture is in the making.

Horus wrote:
20 Oct 2022, 13:39
አበረ፣
በርግጥ በአንድ ብሄራዊ ካልቸር (ባህልና) በውስጡ ካሉ ንኡስ (አናሳ) ባህሎች መሃል ያለው ትስስር ምንድን ነው የሚለው ጥያቄ እጅግ ውስብስብ ነገር ነው ። በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ባለብዙ ጎሳዎች፣ ሃይማኖቶች እና መልካምድሮች አገር የቱ ነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ካልቸር? የተኞቹ ናቸው የዚህ ብሄራዊ ካልቸር ንኡስ አካላት? የሚለው ጥያቄ እስከ ዛሬ በውል ተመርምሮ ብሄራዊ ስምምነት የተደረሰበት ጉዳይ አይደለም ።

ነገር ግን በኔ ከብዙ አመታት ህሳቤ በኋላ የደረስኩበት መደምደሚያ ቢያንስ ማንኛውም ኢትዮጵያዊን ሊያስማማ የሚችሉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ካልቸር መሰረቶች አሉ ። እነሱም የሚከተሉት ናቸው ።

አንድ፣
ኢትዮጵያ የብዙ ሃይሞኖቶች አገር ናት፤ ማለት ህዝቧ በተለያዩ አይማኖቶች የተከፋፈለ ነው ። ነገር ግን ሁሉም የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች በአንድ ፈጣሪ ያምናሉ። ይህ አንዱ የብሄራዊ ካልቸር መቆሚያ መሰረት ነው ። ማንኛውም ካልቸር መቆሚያ እምነት ስለሚፈልግ ማለት ነው ።

ሁለት፣
ስለሆነም ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የዚህ አንድ ፈጣሪ ፍጡራን ስለሆኑ በሰባዊነት ወንድማማቾች ናቸው። ይህ የካልቸር መሰረት ሙሉ በሙሉ በመላው የኢትዮጵያ ግለሰቦች ውስጥ የሰረጸ ሳይኮሎጂ መሆኑን ያጠራጥራል ። ያገሪቱ ፖለቲካ ስርዓት በጎሳዎች ወንድማማችነት ሳይሆን ልዩነት ላይ ስለቆመ ይህ ዛሬ ላይ አከራካሪ ነጥብ ነው ። ነገር ግን አንድ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ካልቸር ይኖር ዘንድ የግድ ህዝቦችዋ ያንድ ፈጥሪ ልጆች የሆንን ወንድማማች ነን ብሎ ማመን አለበት ።

ሶስት፣
የኢትዮጵያ ሕዝብ በልዩ ልዩ ጎሳዎች፣ ቡድኖች፣ የተለያየ ብዛትና መሬት ስፋት ቢኖራቸውም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በአንድ ፈጣሪ የተፈጠረ እኩል ፍጡር ነው የሚለው ሌላው ቁልፍ የካልቸር መቆሚያ መሰረት ነው ። በዚህ የማያምን ህዝብ እኩልነትና ፍትሃዊነት ያለው ካልቸር ሊኖረው በፍጹም አይችልም ። ይህም ዛሬ ትልቅ ችግር ላይ ያለ መሰረት ነው ምክኛቱም የፖለቲካ ስርዓታችን በኢትዮጵያ ግለሰብ ዜጋ ልዕልናና እኩልነት ላይ የቆመ ሳይሆን በጎሳዎች ሃይልና ፉክክር ላይ የቆመ ሰለሆነ።

አራት፣
ስነ ምግባር ወይም ስነ ስራ (ወርክ ኤቲክ) ነው ። ካልቸር ማለት የሰው ልጅ በራሱ እጆች የፈጠረው አለም፣ ነገር ማለት ነው ። ካልቸር ቴክኖሎጂንም ጨምሮ የሰው እጅ፣ የእደ ጥበብ ውጤት ነው ። አለማችን በሁለት ይከፈላል፤ ተፈጥሮ ሰራሽ እና ሰው ሰራሽ ። ሰው ሰራሽ ማለት ካልቸር ማለት ነው ። ስለዚህ ስራ (ተግባር) የካልቸር እምብርት ነው ። ስነ ስራ፣ ስነ ተግባር፣ የስራ ሳይንስ፣ የተግባር ሳይንስ የሌለው ህዝብ ካልቸር አለው ለማለት አይቻልም። እምነት ወይም ሃሳብ ብቻውን ካልቸር አይሆንም። ካልቸር ሶሺያል ፕራክቲስ ነው ። ስለዚህ በስራ ክቡርነት ማመን ሌላው ግዴታ የካልቸር መቆሚያ መሰረት ነው ። ይህም ቢሆን ዛሬ ላይ ሙሉ በሙል የኢትዮጵያ ህዝብ ብሄራዊ እምነት መሆኑ ያጠራጥራል ።

በነዚህ አራት ቁልፍ ጥያቄዎች የተነሳ ነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ካልቸር የቱ ነው? ምን ይመስላል? ይዘቶቹ ምንድን ናቸው? ያሚሉት ጥያቄዎች መመለስ ያለብን ።

ከላይ ያሰፈርኳቸው አራት የካልቸር ኳሊቲ መለኪያዎች ለምንኛውም ካልቸር ፤ የቡድን፣ የጎሳ ፣ የድርጅት፣ የትልቅም የትንሽም ማህበረሰብ ካልቸር ለመለካት የሚሆኑ ናቸው። አንድ ልሁቅ ካልቸር ከንኡስ ካልቸር ጋር ከተጋጩ ከላይ ባሉት መሰረቶችና መለኪያዎች ላይ ሲለያዩና መስማማት ሲያቅታቸው ነው ማለት ነው ። ያ ሲሆን ነው የካልቸር ለውጥ የሚያስፈልገው ማለት ነው ። የካልቸር ለውጥ የእምነትም የተግባርም ለውጥ ይፈልጋል ።

Horus
Senior Member+
Posts: 42875
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 6 አይነት የካልቸር በሽታዎችና 4ቱ የካልቸር ኳሊቲ መለኪያዎች!

Post by Horus » 20 Oct 2022, 14:37

አበረ፣
ዶሚነንት ካልቸር ያልከው ኮመን ካልቸር እንዳልክ አድርጌ ነው የምወስደው ። ትክክል ነው ካልቸር በፕሮሴስ ነው የሚጸናው፣ ካልቸር ማለት ለረጅም ግዜ የተደጋገመ ቢሄቪየር ወይም ተግባር ማለት ነው ። የካልቸር ለውጥም የሚመጣው እንዳልከው በኮንታክት ነው ። ያም የሚሆነው ከላይ እንደጠቀስኩት ካልቸር ተግባር ነው፣ በአይን በሚታይ ተግባር እንጂ በምናብ በማንበብ አይቀዳም ። ለምሳሌ ፈረስ ስለ መጋለብ ሺ አመት ከመጻፍ ላይ ብናነብ መጋለብ አንችልም ። በተግባር ፈረስ ላይ ወጥተን መጋለብን መማር አለብን ማለትም አንድ ሰው ፈረስ ሲጋልብ በኮንታክት ካየይ በኋላ ማለት ነው ።

እንጅ በመሰረቱ ካልቸር ማለት ባህሪ ማለት ነው። ባህሪ ባህል ነው ። ባህል ብሂል፣ ብልሃት ወይም ዘዴ ነው ። ካልቸር አንድ ነገር መተግበሪያ ዘዴ ነው ። ስለዚህ የጋራ ካልቸር ወይም የጋራ ብልሃት እንጂ ዶሚናንትና ሰቦርዲኔት ባህል የለም ። ፈረስ መጋለብ ከፍተኛና ዝቅተኛ የለውም ። አንድ ዘዴ በከፈተኛ ደረጃ እንችለዋለን ወይም አንችለውም ። ሁለት ሰዎች ፈረስ መጋለብ ከቻሉ የጋራ ካልቸር አላቸው እንላለን ። እርግጥ ይህ የጋራ ካልቸር በሁለቱ ሰዎች ኮንታክ ማድረግ ይጀመራል ።
Last edited by Horus on 20 Oct 2022, 19:50, edited 1 time in total.

Tiago
Member
Posts: 3349
Joined: 30 Jul 2018, 02:09

Re: 6 አይነት የካልቸር በሽታዎችና 4ቱ የካልቸር ኳሊቲ መለኪያዎች!

Post by Tiago » 20 Oct 2022, 14:50

Culture is: all the norms, social rules, symbols, shared meanings, traditions, customs, methods of doing things, beliefs ,rituals and interpretations of the world around, shared by particular group or population. ( Way of life )

If a group is part of some culture but differs in some of the aspects listed above, then it is a subculture.

Abere
Senior Member
Posts: 15468
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: 6 አይነት የካልቸር በሽታዎችና 4ቱ የካልቸር ኳሊቲ መለኪያዎች!

Post by Abere » 20 Oct 2022, 15:51

ሆረስ፥

የጋራ ባህል አለ ማለት ነው እጅ ይህ ወይም ያ ባህል ይበልጣል ወይም ያንሳል ማለት በፍጹም አይደለም።ባህልን ከባህል ማወዳደር አይቻልም - ሁሉም ባህል የእራሱ ማህበረሰቡ እንደ ደረሰብት የዕድገት ደረጃ ጠቀሜታ አለው። ነገሮች ሁሉ አንጻራዊ ናቸው - ከጊዜ እና ከቦታ አኳያ። ይህ ማለት ጎጅ ልማዶች አይኖሩም ማለት ግን አይደለም። ልክ እንደ መድሃኒት ጊዜ ሊያልፍባቸው የሚችሉ አሉ- ለምሳሌ ብልት ሰልቦ ለጋብቻ ጥሎሽ መስጠት ወይም ሴት ልጅ ግርዛት ወዘተ:: የአገራችን ዐብይ ባህላዊ እሴት (Macro cultural asset/value) የጋራነት እና የአብሮነት ነው። ይህ መሰረታዊ የባህል የጋራ ውርስ ባህርይ ባይኖር 27 አመታቱ የወያኔ ዘመን እጅግ እጅግ በከፋ ወይም ኢትዮጵያ የምንላት አገራችን ከመቅጽበት ዶግ አመድ በሆነች ነበር። አሁን ያ የጋራ ድር እና ማግ በጎሳ አይጦች እየተበላ እየመነመነ እና እየተበሰከ ይገኛል - but still there is a dominant national culture more or less everyone in the land shares or subscribe to.

Horus wrote:
20 Oct 2022, 14:37
አበረ፣
ዶሚነንት ካልቸር ያልከው ኮመን ካልቸር እንዳልክ አድርጌ ነው የምወስደው ። ትክክል ነው ካልቸር በፕሮሴስ ነው የሚጸናው፣ ካልቸር ማለት ለረጅም ግዜ የተደጋገመ ቢሄቪየር ወይም ተግባር ማለት ነው ። የካልቸር ለውጥም የሚመጣው እንዳልከው በኮንታክት ነው ። ያም የሚሆነው ከላይ እንደጠቀስኩት ካልቸር ተግባር ነው፣ በአይን በሚታይ ተግባር እንጂ በምናብ በማንበብ አይቀዳም ። ለምሳሌ ፈረስ ስለ መጋለብ ሺ አመት ከመጻፍ ላይ ብናነብ መጋለብ አንችልም ። በተግባር ፈረስ ላይ ወጥተን መጋለብን መማር አለብን ማለትም አንድ ሰው ፈረስ ሲጋልብ በኮንታክት ካየይ በኋላ ማለት ነው ።

እንጅ በመሰረቱ ካልቸር ማለት ባህሪ ማለት ነው። ባህሪ ባህል ነው ። ባህል ብሂል፣ ብልሃት ወይም ዘዴ ነው ። ካልቸር አንድ ነገር መተግበሪያ ዘዴ ነው ። ስለዚህ የጋራ ካልቸር ወይም የጋላ ብልሃት እንጂ ዶሚናንትና ሰቦርዲኔት ባህል የለም ። ፈረስ መጋለብ ከፍተኛና ዝቅተኛ የለውም ። አንድ ዘዴ በከፈተኛ ደረጃ እንችለዋለን ወይም አንችለውም ። ሁለት ሰዎች ፈረስ መጋለብ ከቻሉ የጋራ ካልቸር አላቸው እንላለን ። እርግጥ ይህ የጋራ ካልቸር በሁለቱ ሰዎች ኮንታክ ማድረግ ይጀመራል ።

Selam/
Senior Member
Posts: 17918
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: 6 አይነት የካልቸር በሽታዎችና 4ቱ የካልቸር ኳሊቲ መለኪያዎች!

Post by Selam/ » 20 Oct 2022, 19:45

You nailed it, Abere!

ከሰው ደህንነት ጋር እስካልተጋጨ ድረስ፣ ማንም ተነስቶ ይኸ ባህል ዝቅተኛ ወይም ውዳቂ ነው፣ ያኛው የተሻለ ነው ማለት ስህተት ነው። አይደለም የሌላ ማህበረሰብ ባህል፣ በራስህም ውስጥ ያለውን ባህል ማጣጣል ነውር ነው። እያንዳንዳችን በየጊዜው የሚሸጋሸገው፣ የሚዳቀለው፣ የሚወለድና የሚጠፋው የላእላይ የባህል አካሎች ነና።

አስተዳደርና ፓለቲካ ያመጣው የሰው ሰራሽ የድንበር ማካለል ባይኖር ኖሮ፣ ይሄ የኔ የግሌ ባህል ነው፣ ያኛው ደግሞ ያንተ ነው የሚለው እሰጣ እገባ አይኖርም ነበር። ምክንያቱም ባህል ከብዙ ህብረተሰቦች ተወራርሶና ተነካክቶ የተገኘ ውጤት እንጂ፣ በአንድ ጎጥ ይዞታ (ownership) የተወሰነ አይደለም።

አዋቂ ነኝ የሚል የሰው ፍጡር፣ አብሮ ባህልን ለመማማር ለማሻሻል አእምሮውን ክፍት አድርጎ በጋራ መስራት እንጂ ያለበት፣ መበላለጥ ለመላላጥ ብቻ ነው፣ በተለይ በአፍሪካ ሀገር። አንድ ጎሳ ብቻውን ቢንጠራራ ቢወራጭ የትም አይደርስማ።

Abere wrote:
20 Oct 2022, 15:51
ሆረስ፥

የጋራ ባህል አለ ማለት ነው እጅ ይህ ወይም ያ ባህል ይበልጣል ወይም ያንሳል ማለት በፍጹም አይደለም።ባህልን ከባህል ማወዳደር አይቻልም - ሁሉም ባህል የእራሱ ማህበረሰቡ እንደ ደረሰብት የዕድገት ደረጃ ጠቀሜታ አለው። ነገሮች ሁሉ አንጻራዊ ናቸው - ከጊዜ እና ከቦታ አኳያ። ይህ ማለት ጎጅ ልማዶች አይኖሩም ማለት ግን አይደለም። ልክ እንደ መድሃኒት ጊዜ ሊያልፍባቸው የሚችሉ አሉ- ለምሳሌ ብልት ሰልቦ ለጋብቻ ጥሎሽ መስጠት ወይም ሴት ልጅ ግርዛት ወዘተ:: የአገራችን ዐብይ ባህላዊ እሴት (Macro cultural asset/value) የጋራነት እና የአብሮነት ነው። ይህ መሰረታዊ የባህል የጋራ ውርስ ባህርይ ባይኖር 27 አመታቱ የወያኔ ዘመን እጅግ እጅግ በከፋ ወይም ኢትዮጵያ የምንላት አገራችን ከመቅጽበት ዶግ አመድ በሆነች ነበር። አሁን ያ የጋራ ድር እና ማግ በጎሳ አይጦች እየተበላ እየመነመነ እና እየተበሰከ ይገኛል - but still there is a dominant national culture more or less everyone in the land shares or subscribe to.

Horus wrote:
20 Oct 2022, 14:37
አበረ፣
ዶሚነንት ካልቸር ያልከው ኮመን ካልቸር እንዳልክ አድርጌ ነው የምወስደው ። ትክክል ነው ካልቸር በፕሮሴስ ነው የሚጸናው፣ ካልቸር ማለት ለረጅም ግዜ የተደጋገመ ቢሄቪየር ወይም ተግባር ማለት ነው ። የካልቸር ለውጥም የሚመጣው እንዳልከው በኮንታክት ነው ። ያም የሚሆነው ከላይ እንደጠቀስኩት ካልቸር ተግባር ነው፣ በአይን በሚታይ ተግባር እንጂ በምናብ በማንበብ አይቀዳም ። ለምሳሌ ፈረስ ስለ መጋለብ ሺ አመት ከመጻፍ ላይ ብናነብ መጋለብ አንችልም ። በተግባር ፈረስ ላይ ወጥተን መጋለብን መማር አለብን ማለትም አንድ ሰው ፈረስ ሲጋልብ በኮንታክት ካየይ በኋላ ማለት ነው ።

እንጅ በመሰረቱ ካልቸር ማለት ባህሪ ማለት ነው። ባህሪ ባህል ነው ። ባህል ብሂል፣ ብልሃት ወይም ዘዴ ነው ። ካልቸር አንድ ነገር መተግበሪያ ዘዴ ነው ። ስለዚህ የጋራ ካልቸር ወይም የጋላ ብልሃት እንጂ ዶሚናንትና ሰቦርዲኔት ባህል የለም ። ፈረስ መጋለብ ከፍተኛና ዝቅተኛ የለውም ። አንድ ዘዴ በከፈተኛ ደረጃ እንችለዋለን ወይም አንችለውም ። ሁለት ሰዎች ፈረስ መጋለብ ከቻሉ የጋራ ካልቸር አላቸው እንላለን ። እርግጥ ይህ የጋራ ካልቸር በሁለቱ ሰዎች ኮንታክ ማድረግ ይጀመራል ።

Horus
Senior Member+
Posts: 42875
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 6 አይነት የካልቸር በሽታዎችና 4ቱ የካልቸር ኳሊቲ መለኪያዎች!

Post by Horus » 20 Oct 2022, 20:33

አበረ፣
ይህ በጣም የቆየ ክርክር ነው፤ ክሪቲካል ቲኦሪ የሚባል መጥቶ ሄዷል ። ካልቸራል ሬላቲቪዝምም እንዲሁ። እነዚህ ስለ ካልቸር ቅኝት የተደረገባቸው ርዕዮተ አለሞች ናቸው ። ካልቸር የሚለው ቃል ልክ እግዚአብሄር (ጎድ) እንደ ሚለው ቃል በ1001 ስም የሚታወቅ፣ የተለያዩ የቲኦሪና ፍልስፍና ት/ቤቶች የየራሳቸው ኮንሴፕቿላይዜሽና ፍሬም የሚያደርጉት ጽንሰ ነገር ነው ።

በአንድ እስኩል ኦፍ አንትሮፕሎጂ (ገርጥዝ) ካልቸር የትርጉም ወይም የሚኒግ ሲስተም ነው ይለዋል ። አንተ ያልከው ከዚህ የሚጠጋው ካልቸር ያንድ ሕዝብ ወይም ቡድን ቫልዩ ሲስተም ወይም ለነገሮች ዋጋ መስጫ ሲስተም ነው የሚለው ነው ። ቫልዩ እራሱ ውስብስብ ኮንሴፕት ቢሆንም ቁልፍ ይዘቱ መፈለግ ማፍቀር መውደድ ነው ። ስለዚህ ቁላ መቁረጥ እንደ አንድ ተፈላጊ ተወዳጅ ቫልዩ ዋጋ ያለው ነገር ነው ለዚያ ሕዝብ ። ስለዚህ አንድ ሕዝብ በደረሰበት የማሰብ ደረጃ መሰረት የወደደውን ነገር ማንም ትክክል አይደለም ሊል አይችልም የሚለው ድሮ ሁላችንም ያደረግነው አይዲዮሎጂካል ክርክር ነው ።

ግን እኔ በማደርገው ውይይት ውስጥ ቁልፍ ሃሳቡ ያ አይደለም ። አንዱ ትልቁ የካልቸር ምንነት ሶሺያል ፕራክቲስ ነው ። ይህም ማለት የተባለው ሁሉ ተብሎ የታመነው ሁሉ ታምኖ መጨረሻ ላይ የምናገኘው የካልቸር ይዘትና ትክክለኛ መገልለጭ ተግባር ነው፣ ድርጊት ነው ፣ ቢሄቪየር ነው ። ቁላ መቁረጥ ተግባር ነው። ለዚያ ተግባር የምንሰጠውን የተለያየ ትርጉም ወይም ሚኒግ ትተን ማለት ነው ።

ተግባር ማለትም በተደጋጋሚ ልማድ ሆኖ እንደ ሪቿልና ከስተም የምንተገብረው ተግባር ነው የካልቸር ዋና ጭብጥ! ተግባር የሚለካ፣ የሚታወቅ፣ የሚታይ፣ አላማና ውጤት ያለው የሰው የሕዝብ አክቲቪቲ ነው ። በዚህ የተነሳ ተግባር ይለካል፣ ይመዘናል፣ አንድ ተግባር ከሌላ ተግባር በጋራ ክራይቴሪያ ላይ ይነጻጸራል ። ይህም ስለሆነ ነው ታዳጊ ካልቸር ኋላ ቀር ካልቸር የሚባሉ እካልቸር አይነቶች ሊኖሩ የቻሉት ። ይህን መሰል የካልቸር መመልከቻ ሳትይዝ ቁላ የመቁረጥ ካልቸርን ልትነቅፍ አትችልም ። አንድ ሕዝብ ከፈለገ ማንኛውንም ተግባር እንደ ከስተም ቢፈጽም ሊገሰጽ አይቻልም ካልክ ወይም ያ ከሆነ ያንተ የካልቸር አረዳድ በምንም አይነት ቁላ መቁረጥ ክትፎ ከመብላት የሚያሳንሰው ነገር አይኖርም ።

በንደፈ ሃሳቦች ፎግ ጉም ውስጥ ለዘመናት ሙልጭልጭ የሆነ ካልቸር የሚባለው ጽንሰ ነገር መጀምሪያ ምን እንደ ሆነ ጥርት አድርገው ዲፋይን ካላደረጉት ማንኛውም ትርጉም የሚሰጠው ሳሙና ይሆናል ማለት ነው።

በሞራል ፊሎሶፊ ውስጥ ማለትም ቲኦሪ ኦፍ ቫልዩ ውስጥ ተግባር (ቢሄቪየር) የሚለካ የሚመዘን፣ ክፉና ደግ፣ ዉሸትና እውነት ተብሎ የሚለው ነገር ነው ። ስለሆነም ካልቸርም እንዲሁ ይለካል አንዱ ካንዱ ይለያል፣ በእድገት ሚዛን ላይ አንዱ ካንዱ ይበልጣል፣ ያንሳል ። ጥያቄው እድገት ዴቬሎፕመንት በሚባለው የማህበረሰብ ህይወት መለኪያ ላይ ስምምነት መደረስ አለበት ። ማለትም አንድ ኪሎ ክብደት ምን ይሁን፣ አንድ ማይል ርቀት ምን ያህል ነው በሚለው ስምምነት መኖር አለበት ።

ካልቸር መለኪያ የሌለው ሶሺያል ቢሂቨየር ነው የሚል ከሆነ ክርክሩ ያ ሙሉ በሙል የተለየ ሃሳብ ነው ። ማለትም ቁላ መቁረጥ በምን መለኪያ ነው የተሳሳተ ወይም መጥፎ ተግባር የሆነው? ያ ነው ጥያቄ ? ፊሎሶፊ ኦፍ አክሽን ያን ጥያቄ ይመልሳል? ሞራል ፊሎሶፊ ያን ጥያቄ ይመልሳል ።

Selam/
Senior Member
Posts: 17918
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: 6 አይነት የካልቸር በሽታዎችና 4ቱ የካልቸር ኳሊቲ መለኪያዎች!

Post by Selam/ » 20 Oct 2022, 22:18

የሌላ ሰው አካልን ማጉደል ወንጀል ነው። ወንጀልም ካልሆነ ጎጂ ነው - ቁላ መቁረጥ በለው፣ ቂንጥር መቀንጠስ ወይንም እንጥል መቁረጥ በለው። ባህል ከህግ የበለጠ ተጽዕኖ ቢኖረውም፣ ህግ ይገዛዋል።

አንተ ክትፎ የምትበላው ነፍስ አጥፍተህ ቢሆንም፣ ወንጀል አይደለም፣ የጎጂነት አመላካችነትም የለውም። በአንዳንድ ባህሎች ግን፣ አንተ ከዱር አውሬ በረቀቀ ጭካኔ ፣ የላሟን አንገት በቢላዋ ቀንጥሰህ፣ በምላጭ ድቅቅ አድርገህ ከትፈህ፣ ከገዛ አካላቷ በወጣ ቅቤ ለውሰህ በጥሬው ስጋዋን ስታመነጅክ ላየህ ፣ እንደ ቁላ ቆራጩ አረመኔና ሳቬጅ ሊያስብልህ ይችላል።

ኮማ ውስጥ ያለች ሚስቱን የአየር መተንፈሻ ቱቦ ዘግቶ የሚገድል ባህል እንዳለ ሁሉ፣ አብሬ ካልተቀበርኩ የሚልም ማህበረሰብ አለ። በአደባባይ ሴትና ወንድ በግልፅ የፆታ ግንኙነት የሚደረግበት እንዲሁም ባልና ሚስት የሚለዋወጡበት ‘የሰለጠነ’ ባህል እንዳለ ሆኖ ፣ መወሸም የተለመደበትም ሀገር አለ። አብሮ መብላት የመልካም ምግባር መገለጫ የመሆኑን ያህል፣ እንደነውር የሚቆጠርበትም ባህል አለ። ካቲካላና በርበሬ የማይወድ እንደ ደካማ የሚቆጠርበት፣ ጫት ደግሞ ማመንጀክ እንደጌጥ የሚታይበትም ባህል አለ።

ወንጀሉንና ጎጂ ባህሉን አውጣና፣ ሌላውን ባህል እንዴታባክ አድርገህ ነው የምታበላልጠው።

Horus wrote:
20 Oct 2022, 20:33
አበረ፣
ይህ በጣም የቆየ ክርክር ነው፤ ክሪቲካል ቲኦሪ የሚባል መጥቶ ሄዷል ። ካልቸራል ሬላቲቪዝምም እንዲሁ። እነዚህ ስለ ካልቸር ቅኝት የተደረገባቸው ርዕዮተ አለሞች ናቸው ። ካልቸር የሚለው ቃል ልክ እግዚአብሄር (ጎድ) እንደ ሚለው ቃል በ1001 ስም የሚታወቅ፣ የተለያዩ የቲኦሪና ፍልስፍና ት/ቤቶች የየራሳቸው ኮንሴፕቿላይዜሽና ፍሬም የሚያደርጉት ጽንሰ ነገር ነው ።

በአንድ እስኩል ኦፍ አንትሮፕሎጂ (ገርጥዝ) ካልቸር የትርጉም ወይም የሚኒግ ሲስተም ነው ይለዋል ። አንተ ያልከው ከዚህ የሚጠጋው ካልቸር ያንድ ሕዝብ ወይም ቡድን ቫልዩ ሲስተም ወይም ለነገሮች ዋጋ መስጫ ሲስተም ነው የሚለው ነው ። ቫልዩ እራሱ ውስብስብ ኮንሴፕት ቢሆንም ቁልፍ ይዘቱ መፈለግ ማፍቀር መውደድ ነው ። ስለዚህ ቁላ መቁረጥ እንደ አንድ ተፈላጊ ተወዳጅ ቫልዩ ዋጋ ያለው ነገር ነው ለዚያ ሕዝብ ። ስለዚህ አንድ ሕዝብ በደረሰበት የማሰብ ደረጃ መሰረት የወደደውን ነገር ማንም ትክክል አይደለም ሊል አይችልም የሚለው ድሮ ሁላችንም ያደረግነው አይዲዮሎጂካል ክርክር ነው ።

ግን እኔ በማደርገው ውይይት ውስጥ ቁልፍ ሃሳቡ ያ አይደለም ። አንዱ ትልቁ የካልቸር ምንነት ሶሺያል ፕራክቲስ ነው ። ይህም ማለት የተባለው ሁሉ ተብሎ የታመነው ሁሉ ታምኖ መጨረሻ ላይ የምናገኘው የካልቸር ይዘትና ትክክለኛ መገልለጭ ተግባር ነው፣ ድርጊት ነው ፣ ቢሄቪየር ነው ። ቁላ መቁረጥ ተግባር ነው። ለዚያ ተግባር የምንሰጠውን የተለያየ ትርጉም ወይም ሚኒግ ትተን ማለት ነው ።

ተግባር ማለትም በተደጋጋሚ ልማድ ሆኖ እንደ ሪቿልና ከስተም የምንተገብረው ተግባር ነው የካልቸር ዋና ጭብጥ! ተግባር የሚለካ፣ የሚታወቅ፣ የሚታይ፣ አላማና ውጤት ያለው የሰው የሕዝብ አክቲቪቲ ነው ። በዚህ የተነሳ ተግባር ይለካል፣ ይመዘናል፣ አንድ ተግባር ከሌላ ተግባር በጋራ ክራይቴሪያ ላይ ይነጻጸራል ። ይህም ስለሆነ ነው ታዳጊ ካልቸር ኋላ ቀር ካልቸር የሚባሉ እካልቸር አይነቶች ሊኖሩ የቻሉት ። ይህን መሰል የካልቸር መመልከቻ ሳትይዝ ቁላ የመቁረጥ ካልቸርን ልትነቅፍ አትችልም ። አንድ ሕዝብ ከፈለገ ማንኛውንም ተግባር እንደ ከስተም ቢፈጽም ሊገሰጽ አይቻልም ካልክ ወይም ያ ከሆነ ያንተ የካልቸር አረዳድ በምንም አይነት ቁላ መቁረጥ ክትፎ ከመብላት የሚያሳንሰው ነገር አይኖርም ።

በንደፈ ሃሳቦች ፎግ ጉም ውስጥ ለዘመናት ሙልጭልጭ የሆነ ካልቸር የሚባለው ጽንሰ ነገር መጀምሪያ ምን እንደ ሆነ ጥርት አድርገው ዲፋይን ካላደረጉት ማንኛውም ትርጉም የሚሰጠው ሳሙና ይሆናል ማለት ነው።

በሞራል ፊሎሶፊ ውስጥ ማለትም ቲኦሪ ኦፍ ቫልዩ ውስጥ ተግባር (ቢሄቪየር) የሚለካ የሚመዘን፣ ክፉና ደግ፣ ዉሸትና እውነት ተብሎ የሚለው ነገር ነው ። ስለሆነም ካልቸርም እንዲሁ ይለካል አንዱ ካንዱ ይለያል፣ በእድገት ሚዛን ላይ አንዱ ካንዱ ይበልጣል፣ ያንሳል ። ጥያቄው እድገት ዴቬሎፕመንት በሚባለው የማህበረሰብ ህይወት መለኪያ ላይ ስምምነት መደረስ አለበት ። ማለትም አንድ ኪሎ ክብደት ምን ይሁን፣ አንድ ማይል ርቀት ምን ያህል ነው በሚለው ስምምነት መኖር አለበት ።

ካልቸር መለኪያ የሌለው ሶሺያል ቢሂቨየር ነው የሚል ከሆነ ክርክሩ ያ ሙሉ በሙል የተለየ ሃሳብ ነው ። ማለትም ቁላ መቁረጥ በምን መለኪያ ነው የተሳሳተ ወይም መጥፎ ተግባር የሆነው? ያ ነው ጥያቄ ? ፊሎሶፊ ኦፍ አክሽን ያን ጥያቄ ይመልሳል? ሞራል ፊሎሶፊ ያን ጥያቄ ይመልሳል ።

Horus
Senior Member+
Posts: 42875
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 6 አይነት የካልቸር በሽታዎችና 4ቱ የካልቸር ኳሊቲ መለኪያዎች!

Post by Horus » 21 Oct 2022, 00:28

ተዕይንተ ልባሽ ምን ድን ነው?

ተዕይንተ ልባሽ ማለት ፋሽን ሾው ማለት ነው ። ስነልባሽ ወይም የፋሽን አርት ትልቅ ካልቸር ነው ። የሰው ልጅ ገላውን በቅጠል መሸፈን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እጅግ ግዙፍ ግዙፍ ኢንዱስትሪዎችን የፈጠረ፣ ስነቅርጽ (ዲዛይን) ፣ የስቀለም፣ ስነሽመና (ዊቪንግ)፣ ስነስፌት (ቴይለሪንግ)፣ የስነ ፎቶ፣ ምስል፣ ስዕል ሌላም ሌላም አስገራሚ የሰው ልጅ ካልቸሮችን ያፈለቀ ስነልባሽ ነው።

የሰው ልጅ ገላውን በልባሽ የሚሸፍነው ከብርድና ሙቀት ራሱን ለመከላከ ብቻ አይደለም። የአካለ መነመናነት ሃፍረቱን ለመሸፈን ብቻ አይደለም ።

ስነልባሽ የማንነት መገለጫ ነው ። ሰውና ሰው መጀምሪያ ሲገናኙ እራሳቸውን የሚገልጹት በውስጠ ፍጥረታቸው ሳይሆን በውጨ ሽፋናቸው ነው ፣ በፋሽናቸው ነው! ጎርጊስና ቡና የኳስ ቡድኖች የሚለዩት በማሊያቸው በመለያቸው ነው ። ስነልባሽ መለያ ዘዴ ነው፣ ብልሃት ነው! በወረደ ምንነቱ ግን ልባሽ ቴክኖሎጂ ነው ።

ስነልባሽ የስልጣን፣ የሃይል፣ የደረጃ፣ ምልክትና መለያ ነው ። የንጉስ ልባሽ ከፊታዋራሪ ይለያል። የጄኔራል ልባሽ ከሻለቃ ይለያል ።

ስነልባሽ የሃብታምነት ማስታወቂያ ነው ፣ ድሃና ሃብታም መለያ ነው ።

ስነልባሽ የክብር፣ የራስ ክብር፣ ለራስ ዋጋ መስጫ ምልክት ብቻ ሳይሆን ማክበሪያ መሳሪያ ነው ፣ አልባሳተ ቅዱሳን ፈጣሪንና አማልክትን ማክበሪያ የካልቸር ምርቶች ናቸው ።

ዝነኞች፣ ታዋቂዎች፣ ወሬና የዜና ትኩረት ሳቢዎች መለያና ማድነቂያ ስነልባሽ ነው ።

እጅግ ከፍተኛው የሰው ልጅ የደረሰበት የስልጣኔ ደረጃ ስነዉበት ያለው ፍልስፍና ኤስተቲክስ ነው ። ዛሬ ላይ ለሴትም ሆነ ወንድ ካልቸራል ዉበት፣ ባህላዊ ዉበት ማስጌጫው ስነልባሽ ነው ።

ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ እያበበ ያለ ይህ የካልቸር መስክ፣ ስነልባሽ ወይም የፋሽን ካልቸር ነው!!!

ሆረስ ነኝ ያማውቴው ጭልፊት

Abere
Senior Member
Posts: 15468
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: 6 አይነት የካልቸር በሽታዎችና 4ቱ የካልቸር ኳሊቲ መለኪያዎች!

Post by Abere » 21 Oct 2022, 10:22

ሆረስ፥

____የስነ-ሰብዕ እና የባህል ጥናት እረጅም ቆይታ ያለው ከመሆኑ አንጻር በቅርብ ከተጀመሩት የአካዳሚ መስኮች የተሻለ የበለጸገ ንድፈ ሃሳብ እና በድግግሞሽ የተፈተሹ እውነቶች ይኖሩታል የሚል ግምት አለኝ። በእርግጥ ትልቁ የማህበራዊ ሳይንሶች ቁልፍ ችግር የሚዳስሡት ሃቅ እንደ ጥጥር የሳይንስ መስኮች ፊዚካላዊ ባለመሆኑ በስሌት እና በቀመር (model) ሙሉ በሙሉ ማስቀመጥ አይችሉም። ተለዋዋጭ ናቸው - የሚለዋወጡት ደግሞ ከጊዜ እና ከቦታ አንጻር ነው። ስለዚህ በዘመኑ እንደ ሚኖረው ሰው ወይም አገር/ቦታ/ ነው የሚመዘኑት። ምሳሌ የማስታውሰ ነገር አሜርካን አገር ካልተሳሳትኩኝ አንድ ኢትዮጵያዊ የሀረርጌ ሰው (አደሬ ሳይሆን አይቀርም) ጥቁር አሜሪካዊት አግቦቶ ሴት ልጅ ወለደ። የተወለደችው ልጅ ማደግ ጀመረች እርሱን ግን የሚያሳስበው ባለመገረዟ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ሚስቱ በለለችበት ልጁን እራሱ ገረዛት። የባህል ልዩነት ሰፊ በመሆኑ አሜሪካዊቱ ሚስቱ በህግ ከሳው ፍርድ ቤት ቀርቦ እስራት ተፈርዶበት እንደ ነበር አውቃለሁ። ይህ አንተ እንዳልከው ባህል ሰው ሰራሽ ሲሆን ባህርይ እና ስብዕና ይሆናል። መገረዝ ድርጊት ሆነ። ሰውየው ከኢትዮጵያ ወጥቷል (በአካል) በባህርይ ግን አልወጣም ነበር። ይህ ድርጊት በሀረር ትክክል ሲሆን በተፈጸመበት ቦታ ግን ወንጀል ነው።በተዘዋዋሪ ደግሞ በምዕራቡ አለም የጨዋታ ደንብ ወጥቶለት ነጻ ትግል ግብግብ እና በቡጢ በደም እስኪጨማለቅ ይደባደባል። ይህ በምዕራቡ አለም መዝናኛ ነው - ለአንድ የሀረርጌ ሰው ይህን የአውሬ ባህርይ ያየዋል። የሰለጠነ ወይም ያልሰለጠነ የሚያስብል ሁነኛ መስፈርት የለም። ለምሳሌ ብዙ 9 ሚስት በአንድ ቤት የሚነዳ አረብ አለ በሌላ መልኩ ደግሞ ወንድ ከወንድ ካልተጋባን ሙተን እነገኛለን የሚሉ በምዕራቡ አለም አለ።ይህ ለአገርቤቱ ለገጠር ሰው አበስ ገበርኩ እትፍ! እትፍ! ነው የሚለው።

____ዋናው ጉዳይ የሰው ልጅ አንድም ብዙም ነው። Humanity is one and diverse እንደት? አንድ አይነት የሚያደርጉት ምሳሌዎች ሁሉም የሰው ልጅ ስም ያወጣል(ስም የሌለው ሰው የለም)፥ ቤተሰብ ይመሰርታል/ጋብቻ፥ ያጌጣል፤ መጠልያ ይሰራል፤ ደስታ (ዘፈ) እና ሀዘን መግለጫዎች አሉት፤ ወዘተ። እነኝህ አንድ ያደርጉታል የሚለዩት ደግም ሁሉ እንደሚኖርበት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የተለያየ ዘይቤዎች ይጠቀማል - ከዚህ አንጻር የአዳም ልጆች የባህል ልዩንት ይታይባቸዋል።ባህል በአስተምሮ እንጅ በተፈጥሮ የሚገኝ ክህሎት አይደለም። ያአስተምሮ ሲሰርጽ ባህርይ ይሆናል። የሰውን ልጅ የህሌና ሚዛን ተጠቅሞ የእንሰሳነት ወይም አውሬነት ተፈጥሮውን እንድ ገድብ ያደርገዋል። Culture is a learned behavior. Nurture plays the largest role to govern our behavior.ስለዚህ ባልህ አንድ ግለሰብ አድርግ እና አታድርግ የሚሉ ግደታዎች ይጥልበታል። Do's and don'ts.ስለዚህ ባህል የሰው ልጆች የሚኖሩበትን አለም በጥበብ እንድኖሩ የሚያስችላቸውን መላ የዘየዱት ነው - እግዜር የተለየ አእምሮ ሰውን ስለሰጠው። አንድ ከባህል ያፈነገጠ ሰው እንደሚነቀፍ ያውቃል ስለዚህ መልካም ባህርይ ያሳያል መለት ነው። ባህል ደግሞ የሚዳሰስ ቁሳዊ አለ የማይዳሰስ አለ - ከዚህ አንጻር ሁለቱም በድርጊት ይገለጻሉ።

____አንተ ያነሳኸው ጉዳይ ለየት ያለ ነው። የባህል ጉዳይ ሳይሆን እንደሚመስለኝ የሰብዐዊ መብቶች ትንታኔ ነው።እርሱም የ cultural relativism and human right activists concept of universalism ፍጭት ነው።እንጅ ሳይንስ አይደለም ባይነኝ።Universalist የሚሉት ሁሉም ሰው አንድ ነው አንድ አይነት መስፍርት መኖር አለብት ይህ ደግሞ የሰብዐዊ መብት ለመጠበቅ ያስማማል የሚል ነው። ይህ ጽንሰ ሃሳብ ልክ አንድ ወጥ የኮምፒዩተር ሶፍትዌር ፕሮግራም በመላው ሰው ልጆች ላይ መጫን እንደማለት ነው። Just like installing Microsoft word on every human laptop machine. ትልቁ ችግር የሶፍትዌሩ ፕሮግራም ኮድ ከየት መጣ ነው? የስልጣኔ ማማ ወጥተናል የሚሉት አገሮች ናቸው፡እንኳን ባህል ቀርቶ በስነ-መንግስት እንኳን ኩረጃው አላዋጣም። ሁሉም የአለም መንግስታት ዲሞክራቲክ እያሉ ይለፍፋሉ ግን ዲሞክራሲ እራሷ እንኳን አንጻራዊ ናት እንኳን ውቅያኖስ የሆነው የሰው ልጆች ባህል። ድሞክራሲ ምንድን ነው ቢባል ማንም መተርጎም የሚችል አይመስለኝም - እንድሁ ማነብነብ ካልሆነ። በአንጻሩ ባህል ሰጥቶ በመቀበል ላይ የተመረኮዘ አካሄድ እንዳለ የሚተነትን ይመስለኛል። ይህ ማለት በጎውን ሰጥቶ በጎውን ከሌሎች መቅሰም። ስልጣኔ መጣ ብሎ የሸክላ ዲስት ሰብሮ ብረት ድስት ማምረት ወይም የላስቲክ ኩባያ ጠንካራ ነው ብሎ የቅል መጠጫ ( ሽክና/አቧሬ) ወይም ዋንጫ ማጥፋት ስህተት ሊሆን ይችላል። የሸክላ ድስት ሽሮ አማረኝ ማለት አይቻልም ወይም ቀዝቃዛ ውሃ በሽክና ይጣፍጣል ብሎ መናፈቅ። ከዚህ ላይ ነው ልዩነቱ። ከዚህ አንጻር ጎጅ ልማዶች መጥፋት አለባቸው በጠቃሚ መተካት አለባቸው። 10 ሺ ሰዎች በሚኖሩበት ዘመን የነበረ ወግ ሚልዮኖች በሚኖሩበት መተግበር ያስቸግራል።

____እንደ እኔ ባህላችንን በተጠና መልኩ መተግበር አለብን ባይ ነኝ። አንድ አገር ደግሞ ብሄራዊ የባህል እሳቤ አለው። ኢትዮጵያዊነት በእራሱ ስሙ ሲነሳ ባህላዊ ምስሉ ነው የሚጋረጠው በህሌናችን። ጠቃሚዎችሁ መያዝ፥ ከትውልድ እና ጊዜ አንጻር ደግሞ መሻሻል ያለባቸው ይሻሻላሉ። የእኛ ትልቁ ችግር በውጭ ባህል ፈጥነን የመወረር እና አሜን ብለን እንቀበላለን። መመርመር አለብን -በተለይ በዘመነ ሶሻል ሚድያ። ለማጠቃለያ ያህል ባህል መለኪያ ሚዛን የለውም። እንደየዘመኑ እና እንደ ቦታው ተለዋዋጭ ነው። Culture does not have standard metric unit like physicals quantities, it is vey much qualitative. Since humanity shares plenty of similarities and man is a rational being (knows right from wrong) , evolution of thinking continues to refine in the context of time.

Horus
Senior Member+
Posts: 42875
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: 6 አይነት የካልቸር በሽታዎችና 4ቱ የካልቸር ኳሊቲ መለኪያዎች!

Post by Horus » 21 Oct 2022, 13:16

አበረ፣
እኔ ካልቸር ፊዚካል ሳይንስ ነው አላልኩም። ባባዛኛው ያልከው ነገር እኔም ያልኩት ነው ። በመጀመሪያ የውይይትህ ክፍል ካልቸር ኮድ ኦፍ ኮንዳክት ነው ብለሃል፣ እኔም የምለው ያን ነው ። ኮድ ሕግ፣ ደምብ፣ ስርዓት ማለት ነው። ለዚህ ካልቸር የሰዎች ማህበራዊ ተግባር ስነስርዓት ነው ። ያ ማለት ደሞ ክፉና ደግ፣ ትክክልና ስህተት ባህሪያትን መለየት ማለት ነው ። ያ ማለት ካልቸር እስታንዳርድ አለው። ለዚህ ነው አንድ ተግባር ከሌላ ተግባር የሚለየው፣ አንዱ ትክክል አንዱ ስህተት የሚሆነው ። ሌላ ቦታ እንዳልኩት እነዚህ እስታንዳርዶች ማነው የሚያወጣቸው በምን ሞራል፣ ሊጋል፣ ወይም ፊሎሲፊካል መለኪያ የሚለው እንዳለ ሆኖ ማለት ነው ።

መጨረሻ ጥያቄውን አንተ መልሰሀዋል ። እኔ ከላይ የተጠቀምኩ ቃል ኳሊቲ ነው ። ኳንቲቲ ካፌ አለወጣም። ካልቸር የሚለካው በኳሊቲ ነው ። እጅግ ጥቂት ሶሺያል ሳይንሶች ወደ ቴክኖሎጂ የሚጠጉት በኳንቲቲ (አሃዝ) ይለካሉ ማለትም ይሰፈራሉ፣ ይቆጠራሉ፣ ይመዘናሉ፣ ይመተራሉ ። ለዚህ ተራ ማቲማቲክስ እንጠቀማለን። አንድ መሳት የሜለብህ ነገር ኳሊቲ (ያንድ ነገር ጥራት፣ ጽዳት፣ ተፈላጊነት፣ ወዘተ) እንዲሁ ይለካሉ ። ለዚህ ደሞ እጅግ የዳበሩ የስታጽቲክስና ፕሮባቢሊትይ ሳይንስ አለ ።

ባንድ ቃል ልልህ የምፈልገው መጥፎ ባህልና መልካም ባህል፣ ጠቃሚ ባህልና ጎጂ ባህል መለኪያ አላቸው፣ እሱም አንተ ያልከው ኳሊቴቲቭ ሜትድ ይብላል ። አይደለም የሰው ተግባር (ባህርይ) የሰው ፍላጎትም፣ ስሜት፣ ሞቲቬሽን ወዘተ ሳይኮሎጂያዊ ኤክስፐሪያሶች ሁሉ ይለካሉ በኢተርቪው ወዘተ። እነዚህ የኳሊቲ ልኬቶች እንደ ፊዚካል ኦብጀክት ኤግዛክት ሜዠርመንት እንዲኖራቸው አይጠበቅም ምክኛቱም ፊዚካል ኳንቲቲ ስላልሆኑ ።

ተግባር የምንለው ሪያሊቲ በጃችን ባንዳሠውም በአይናችን እናየዋለን (ቪዚብል አክሽን ምለት ነው)፣ ስለዚህ ቢሄቪየር ይለካል ከአካል ውጭ የሚፈጸም ንቅናቄ (ሙቭመንት ስለሆነ) ። ባንጎል ውስጥ ብቻ የሚኖር፣ በተግባር ያልተገለጸ ስሜት ኢሞሽን፣ ወይ ሃሳብ (ቶውት) ሰውዬን በመጠየቅ (ኢተርቪው ሜትድ) ሃሳቡ፣ ፍላጎቱ፣ ኢሞሽኑ በደረጃ በማሳየት ይለካል ። ስሌቱ ዉሃና ጨው እንደ መስፈር ኤግዛክት አይደለም። ነገር ግን ሁለት ሰዎች በውስጣቸው ያዘሉት የሃሳብና የስሜት ልዩነት ለማወቅ የሚያስችል ሌኬት እናደርጋለን ማለት ነው ። ይህ እንግዲህ ለሳይኮሎጂካል ፋክት ነው ። ለሰው ተግባር፣ ባህሪና ካልቸራል አክቲቪቲ እጅግ የላቀ መለኪያ ዘዴ አለን ። ተግባር የሚታይ ፋክት ስለሆነ ።

ስለዚህም ነውኮ አንድ የወንጀል ድርጊት በአይን ምስክር ተለክቶ ለቅጣት የሚያበቃው! ስለዚህ ካልቸር ይለካል፣ መለኪያ አለው ። አንድ ካልቸር ከሌላ ካልቸር መለያ መንገዱ ሁለቱን ለክቶ በማነጻጸር ነው ። አንድ ባህል ከሌላ ባህል ይሻላል የምንለው የሁለቱን ኳሊቲ በመለካት ነው ።

Selam/
Senior Member
Posts: 17918
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: 6 አይነት የካልቸር በሽታዎችና 4ቱ የካልቸር ኳሊቲ መለኪያዎች!

Post by Selam/ » 22 Oct 2022, 07:11

የሶሻል ሳይንቲስት ባለመሆኔ በጣም ደስ ይለኛል። ሽሜው ይኸንን ያህል በፍልስፍና ድሪቶ የምትድበሰበሰው፣ እኔ አንዱን ባህል ዝቅተኛ ሌላውን ደግሞ ከፍተኛ ነው ለማለት እችላለሁ የሚለውን ውሃ የማይቋጥር አቋምህን ሽፋን ለመስጠት ነው።

አንተ ማን ሆነህ ነህ ነው፣ የባህል ስታንዳርድ አውጭ የሆንከው? በጠባብ የዘር መነፅርህ፣ ጉራጌ ከሁሉ ከፍ ያለ ባህል አለው ነው እንጂ ሁልጊዜ የምትለው፣ በቀና መንፈስ የሚጎዳና የሚጠቅመውን ለማነጻጸር ቢሆን ኖሮማ ሀሳብህ፣ ከአንድ ጎጥ ቅርቃር ውስጥ ወጥተህ፣ የሌሎቹንም መልካም የኑሮ ዘይቤ ታንጸባርቅ ነበር፤ የራስህንም ጎጥ ደካማ ባህል ታሳየን ነበር። ጀግናው ግን፣ ጉራጌ ጉያ ውስጥ ተደብቀህ፣ ስለጉራጌ ረቂቅነት ብቻ እያወራህ፣ እራስህን ስታንዳርድ (standard) አውጭና ዳኛ አድርገህ ሾመህ ሌላውን ህብረተሰብ ለማሳነስ በፍልስፍና የጽሁፍ ጋጋት ለመሸፉፈን ብትሞክር፣ ራስ ወዳድና ግብዝ መሆንክን ብቻ ነው የምታስመሰክረው።

አንተ ላሟን እስከ ጥጃዋ ገድለህ፣ በጥሬዋ እንደምትበላው፣ ትንኝና እንቁራሪት ክሽን አድርጎ ጠብሶ የሚበላ ህዝብ አለ። በአንተ እይታ እነሱ ከጉራጌ ያነሱ ናቸው፤ በእነሱ እይታ ደግሞ አንተ የጅብ እኩያ ነህ። ታዲያ የትኛው አተያየት ነው ትክክል። ኒው ዮርክ ከተማ ወንድምህን አቅፈህ በመንገድ ላይ ብትታይ ጌይ ትባላለህ፤ እንድብር ውስጥ ግን የሰው ፍቅር ያለህ ታላቅ ወንድም እንደሆንክ ይቆጠርልሃል። ጥህሎ የትግራይ ምርጥ ምግብ ነው፣ መንዜ ግን እንዴት ሰው በሶ በወጥ አጣቅሶ ይበላል ይልሀል።

የዛሬ መቶ አመት ግን መንዜው ለቁርሱ ጥህሎ ይበላ ይሆናል፣ አንተም ኢንሴክት (insect) ጠብሰህ ለዲዘርት ትበላ ይሆናል በህይወት ብትኖር። ወንድ ለወንድ መጋባታም እንድብርም ይጀምር ይሆናል።

Horus wrote:
21 Oct 2022, 13:16

Post Reply